ምዕራፍ ፵
ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ትንሣኤ እንዲሆን አደረገ—ፃድቃን ሆነው የሞቱት ወደገነት ይሄዳሉ፣ እናም ኃጢአተኛ ሆነው የሞቱት እስከትንሳኤው ቀን ለመጠበቅ ወደ ድቅድቅ ጨለማ ይሄዳሉ—በትንሣኤ ሁሉም ነገር ወደ ተገቢው እናም ፍፁም ወደሆነው ቅርፅ ይመለሳል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እንግዲህ ልጄ፣ ለአንተ በተጨማሪ የምለው ነገር ይህ ነው፤ ምክንያቱም አዕምሮህ ስለሙታን ትንሣኤ ተጨንቋልና።
፪ እነሆ፣ እንዲህ እልሃለሁ፣ ትንሣኤ የለም፣ ወይም በሌላ አነጋገር እንዲህ እላለሁ፣ ክርስቶስ ከመምጣቱ ሀበኋላ ድረስ ይህ የሚሞተው ለወደማይሞተው፣ ይህ የሚበሰብሰው ወደማይበሰብሰው ሐአይለወጥም።
፫ እነሆ፣ እርሱ የሙታን ትንሣኤ እንዲሆን ያደርጋል። ነገር ግን እነሆ፣ ልጄ፣ ሀትንሳኤው ገና ነው። እንግዲህ፣ ሚስጥሩን እገልፅልሃለሁ፤ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር እራሱ ካልሆነ በቀር ማንም የማያውቃቸው ብዙ በአምላክ ለየተደበቁ ሐሚስጥሮች አሉ። ነገር ግን እግዚአብሔርን አውቀው ዘንድ በትጋት የጠየቅሁትን አንድ ነገር ለአንተ አሳይሃለሁ፤ እርሱም ትንሣኤን በተመለከተ ነው።
፬ እነሆ፣ ሁሉም ከሙታን እንዲነሱበት የተወሰነ ጊዜ አለ። እንግዲህ ይህ ሀየምመጣበትን ጊዜ ማንም አያውቅም፤ ነገር ግን የተወሰነውን ጊዜ እግዚአብሔር ያውቃል።
፭ እንግዲህ የመጀመሪያዎቹም ሆኑ ሀሁለተኛዎቹ፣ እንዲሁም ሦስተኞቹ ከሞት የሚነሱበት ጊዜ መኖሩ ልዩነት የለውም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለያውቃልና፤ እናም ይህ እንደሚሆን—ሁሉም ከሞት የሚነሱበት የተወሰነ ጊዜ እንዳለ ማወቅ ለእኔ ይበቃኛል።
፮ እንግዲህ በሞት እናም በትንሳኤ መካከል ጊዜ መኖሩ አስፈላጊ ነው።
፯ እናም እንግዲህ እንዲህ ብዬ እጠይቃለሁ፥ የሰው ሀነፍስ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ለትንሣኤው እስከተወሰነበት ጊዜ ድረስ ምን ይሆናል?
፰ እንግዲህ ሰዎች እንዲነሱ የተወሰነላቸው ጊዜ ከአንዴ የበለጠ ቢሆን ምንም ልዩነት አያመጣም፤ ምክንያቱም ሁሉም በአንዴ አይሞቱምና፣ እናም ይህም ምንም አይደለም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉም እንደ አንድ ቀን ነው፤ እናም ጊዜ በሰዎች ብቻ ይለካል።
፱ ስለዚህ፣ ሰዎች ከሞት የሚነሱበት ቀን ተወስኗል፤ እናም በሞትና በትንሣኤ መካከል ጊዜ አለ። እናም እንግዲህ፣ ይህን ጊዜ በተመለከተም፣ የሰዎች ነፍስ ምን ይሆናል ብዬ ጌታን በትጋት የጠየቅሁት ይህን ነገር ነው፤ እናም የማውቀው ነገር ይህን ነው።
፲ እናም ሁሉም ከሞት የሚነሱበት ጊዜው ሲደርስ፤ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተወሰነውን ሀጊዜ በሙሉ ማወቁንም ያውቃሉ።
፲፩ እንግዲህ፣ ሀበሞትና በትንሣኤ መካከል የነፍስ ሁኔታን በተመለከተ—እነሆ፣ የሰዎች መንፈስ ሁሉ ከዚህ ሟች ከሆነው ሰውነታቸው እንደተለየ፣ አዎን፣ የሰዎች መንፈስ ሁሉ፣ መልካምም ይሁኑ መጥፎ፣ ህይወትን ወደ ሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር ለእንደሚወሰድ በመልአኩ አማካኝነት እንዳውቀው ተደረገ።
፲፪ እናም እንዲህ ሆነ የፃድቃኖች መንፈስ፣ ከሁሉም ችግር፣ ውጣ ውረድና ሀዘን ወደሚያርፉበት፣ ሀገነት ተብላ ወደምትጠራው፣ ለየእረፍት ቦታ፣ ሐየሰላም ቦታ ውስጥ ወደ መደስታ ሁኔታ ይገባሉ።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ የኃጢአተኞች መንፈስ፣ አዎን፣ ክፉዎች የሆኑትም—እነሆም፣ የጌታ መንፈስ ፈንታም ሆነ ድርሻ የላቸውም፤ እነሆም፣ ከመልካሙ ስራ ይልቅ መጥፎውን መርጠዋልና፤ ስለዚህ የዲያብሎስ መንፈስ በውስጣቸው ገብቷል፣ ቤታቸውንም የእርሱ አድርጎታል—እናም እነኚህ ወደ ሀድቅድቅ ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያም ለልቅሶና ዋይታ እናም የጥርስ ማፏጨት ይኖራል፣ ይህም በክፋታቸው የተነሳ፣ በዲያብሎስ ፈቃድም በምርኮ ስለተመሩ ይሆናል።
፲፬ እንግዲህ ይህ ሀየክፉዎች የነፍሳቸው ሁኔታ ነው፤ አዎን፣ በጨለማ ውስጥ እናም በእራሳቸው ላይ የእግዚአብሔር ሀይለኛ ንዴት ቁጣ በመጠበቅ አሰቃቂውና ለበአስፈሪውም በሆነ በእንደዚህም አይነት ሁኔታ ሲቆዩ፣ ፃድቃኖችም እስከትንሳኤው ድረስ በገነት ይቆያሉ።
፲፭ እንግዲህ፣ ከትንሳኤው በፊት እንደዚህ ዓይነቱን የነፍስ ደስታን እና መከራን የመጀመሪያው ትንሳኤ ነው በማለት የሚረዱት ጥቂት ሰዎች አሉ። አዎን፣ በተነገሩት ቃላት መሠረት የነፍስ ወይንም የመንፈስ መነሳትንና በደስታ ወይንም በችግር መሰየም ምናልባት ትንሳኤ ተብሎ ሊጠራ እንደሚችል እቀበለዋለሁ።
፲፮ እናም እነሆ፣ በድጋሚ በክርስቶስ ከሙታን መነሳት ድረስ የነበሩት፣ ወይንም ያሉት ወይንም የሚኖሩት ሁሉ ትንሣኤ፣ ሀየፊተኛው ለትንሳኤ እንዳለም ተነግሯል።
፲፯ አሁን፣ በዚህ ሁኔታ የተነገረው ይህ የመጀመሪያው ትንሳኤ፣ የነፍስ ትንሳኤ እንዲሁም የደስታቸው ወይም የሥቃያቸው ሀስያሜ ሊሆን እንደሚችል አልገመትንም። ይህ ትርጉሙ ይሆናል ብለህ መገመትም አትችልም።
፲፰ እነሆ፣ እንዲህ እልሃለሁ፣ አይደለም፤ ነገር ግን ይህ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሀክርስቶስ ትንሣኤ ድረስ ለነበሩት የነፍስ እና የስጋ ውህደት ማለት ነው።
፲፱ እንግዲህ ቀድሞ የተነናግርኩባቸው ኃጥአንም ሆነ ፃድቃን ነፍሳቸው ከስጋቸው ጋር በአንድ ጊዜ ይዋሃዳል ብዬ አልናገርም፤ ሁሉም ይነሳሉ ማለቴ ብቻ በቂ ነው፤ ወይም በሌላ አነጋገር፣ ትንሣኤአቸው ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ ከሞቱት ሀበፊት ይሆናል።
፳ እንግዲህ፣ ልጄ፣ ትንሣኤያቸው በክርስቶስ ትንሣኤ ይመጣል አላልኩሁም፤ ነገር ግን እነሆ፣ በክርስቶስ ትንሣኤ እንዲሁም ወደ ሰማይ ሀባረገበት ጊዜ የፃድቃኖች ነፍስ ከስጋቸው ጋር መዋሃዱን አስተያየቴን እሰጣለሁ።
፳፩ ነገር ግን በትንሣኤውም ሆነ ከትንሣኤውም በኋላ እንደዚህ አልልም፤ ነገር ግን ይህንን ያህል እናገራለሁ፣ ሙታን እንደሚነሱ፣ ነፍስም ከስጋ ዳግም እስከሚገናኝ እንዲሁም በእግዚአብሔር በተወሰነላቸው ቀን እንደስራቸው በእግዚአብሔር ፊት ሀበመቆም እስከሚፈረድባቸው ድረስ በሞትና በአካል ትንሳኤ መካከል ለጊዜ፣ እናም ነፍስ ሐበደስታ ወይም መበስቃይ የሚገኝበት ጊዜ አለ።
፳፪ አዎን፣ ይህም በነቢያት አንደበት የተነገሩትን ነገሮች በሙሉ ዳግሞ መመለስን ይመጣል።
፳፫ ሀነፍስ ወደ ለስጋ፣ ስጋም ወደ ነፍስ ሐበዳግም ይመለሳል፤ አዎን፣ እናም ማንኛውም እጅና እግር እንዲሁም መገጣጠሚያ ወደ ቀድሞ ቦታው ይመለሳል፤ አዎን፣ የራስ ፀጉርም ቢሆን አይጠፋም፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር ወደ ተገቢው እናም ትክክለኛ አቋሙ ይመለሳል።
፳፬ እናም እንግዲህ፣ ልጄ፣ ይህ በነቢያት አንደበት ሀየተነገረው ዳግሞ መመለስ ነው—
፳፭ እና ከእዚያም ፃድቃኖች በእግዚአብሔር መንግስት ያበራሉ።
፳፮ ነገር ግን እነሆ፣ አሰቃቂው ሀሞት በኃጢአተኞች ላይ ይሆናል፤ ፅድቅ ለሆኑት ነገሮች ሞተዋልና፤ ምክንያቱም እነርሱ ንፁህ አይደሉምና፣ እናም ምንም ለእርኩስ ነገር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርስ አይችልም፤ ነገር ግን መጥፎ የሆኑትን የስራቸውን ውጤት እንዲካፈሉ ይጣላሉ፣ እናም መራራውን አተላ ይጎነጫሉ።