የአልማ ለልጁ ለሔለማን የሰጠው ትዕዛዛት
ምዕራፍ ፴፮ እስከ ፴፯ አጠቃሎ የያዘ።
ምዕራፍ ፴፮
አልማ ለሔለማን መላዕክቱን ከተመለከተ በኋላ ስለመለወጡ መሰከረ—ለተኮነነ ነፍስ ስቃይን ተሰቃየ፤ የኢየሱስን ስም ጠራ፣ እናም ከእግዚአብሔር ተወለደ—ጣፋጩ ደስታ ነፍሱን ሞላው—እግዚአብሔርን የሚያወድሱ ብዛት ያላቸው መላዕክትን ተመለከተ—ብዙ የተለወጡ ቀምሰውታል እናም እርሱ እንደተመለከተው መንፈሳዊውን ነገር ተመልክተውታል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ ሀልጄ ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስከጠበቅህ ድረስ በምድሪቱ ላይ እንደምትበለፅግ ለአንተ እምላለሁ።
፪ የአባቶቻችንን ምርኮ በማስታወስ እኔ እንዳደረግሁት እንድታደርግ እፈልጋለሁ፤ ሀበምርኮ ስለነበሩ ለከአብርሃም አምላክና፣ ከይስሀቅ አምላክ፣ እናም ከያዕቆብ አምላክ በስተቀር ማንም ሊያስለቅቃቸው አይችልም፤ እርሱ በእርግጥ ከስቃያቸው አስለቅቋቸዋል።
፫ እናም አሁን፣ ልጄ ሔለማን ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ወጣት ነህ፣ እናም ስለዚህ፣ ቃሌን እንድትሰማና ከእኔም እንድትማር እለምንሃለሁ፤ እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ ሀበፈተናቸውና፣ በችግራቸው፣ እናም በስቃያቸው እንደሚደገፉና፣ በመጨረሻው ቀን ለከፍ እንደሚደረጉ አውቃለሁ።
፬ እናም በራሴ ሀእንደማውቀው እንድታስብ አልፈልግም—በጊዜያዊው ሳይሆን ነገር ግን በመንፈሳዊው፣ ለበስጋዊ አዕምሮዬ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው።
፭ እንግዲህ፣ እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፥ ሀከእግዚአብሔር ባልወለድ ኖሮ እነዚህን ነገሮች ለባላወቅሁ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር፤ በቅዱስ መልአኩ አንደበት፣ እኔ ሐብቃት ያለኝ በመሆኔ ሳይሆን፣ እነዚህን ነገሮች እንዳውቅ አድርጎኛል፤
፮ ከሞዛያ ልጆች ጋር የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ሀለማጥፋት በመፈለግ እሄድ ነበርና፤ ነገር ግን እነሆ እግዚአብሔር በመንገዳችን እኛን እንዲያቆመን ቅዱስ መልአኩን ላከ።
፯ እናም እነሆ፣ የነጎድጓድ ድምፅ በሚመስልና፣ ምድር ሁሉ በስራችን ሀእስክትንቀጠቀጥ ተናገረን፤ እናም የጌታ ለፍርሃት ስለመጣብን በመሬት ላይ ወደቅን።
፰ ነገር ግን እነሆ፣ ድምፁ እንዲህ አለኝ፥ ተነስ። እናም ተነሳሁና ቆምኩ፣ መልአኩንም ተመለከትኩ።
፱ እናም እርሱ እንዲህ አለኝ፥ ራስህን ለማጥፋት ከፈለግህም፣ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት አትፈልግ።
፲ እናም እንዲህ ሆነ በመሬት ላይ ወደቅሁ፤ እናም ሀለሶስት ቀንና ሌሊት አፌን ለመክፈትም፣ ሆነ ክንዶቼን ለመጠቀም አልቻልኩም።
፲፩ እናም መልአኩ ወንድሞቼ ያዳመጡትን፣ ነገር ግን እኔ ላዳምጠው ያልቻልኩትን ከዚህ የበለጡ ነገሮች ተናገረኝ፤ ራስህን ለማጥፋት ከፈለግህም፣ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ከእንግዲህ ለማጥፋት አትፈልግ የሚለውን ቃሉን ስሰማ፣ በታላቁ ፍርሃትና መገረም እጠፋለሁ ብዬ በመፍራቴ፣ በመሬት ላይ ወደቅሁ፣ እናም ሌላ ምንም አልሰማሁም።
፲፪ ነገር ግን በስቃይ ሀለዘለዓለም ተጨንቄ ነበር፣ ነፍሴ በታላቅ ደረጃ ተጨንቃ፣ እናም በኃጢአቶቼ ሁሉ ተሰቃይታ ነበርና።
፲፫ አዎን፣ በሲኦል ህመም ሀየተሰቃየሁባቸውን፣ ኃጢአቶቼን እናም ክፋቶቼን ሁሉ አስታውሳለሁ፤ አዎን፣ በአምላኬ ላይ ማመፄን፣ እናም ቅዱሳን ትዕዛዛቱን አለመጠበቄን ተመልክቻለሁ።
፲፬ አዎን፣ እናም ብዙዎቹን ልጆቹን ገድያለሁ፣ ይልቁንም ወደጥፋትም እንዲመሩ አድርጌአለሁ፤ አዎን፣ እናም በአጠቃላይ ክፋቶቼ ታላቅ ስለነበሩ፤ ወደ አምላኬ በፊቱ ለመቅረብ ያለኝ ሀሳብ በሚያስቸግር ስቃይ ነፍሴን እንድትሰቃይ አደረጋት።
፲፭ ሀበስራዬም ሊፈረድብኝ በአምላኬ ፊት እንዳልቆ ም ዘንድ፣ ለተወግጄ እና በነፍስና በስጋዬ ለመጥፋት እንደምችል አስብበት ነበር።
፲፮ እናም አሁን፣ ለሶስት ቀንና ለሶስት ሌሊት ሀበተኮነነች ነፍስ ህመምም እንኳን ተሰቃየሁ።
፲፯ እናም እንዲህ ሆነ በጭንቀት በተሰቃየሁ ጊዜ፣ በኃጢአቶቼ ብዛትም በትውስታ ሀበተሰቃየሁ ጊዜ፣ እነሆ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተባለው፣ የዓለምን ኃጢያት ለመክፈል ስለሚመጣው፣ የአባቴን ትንቢት መስማቴን አስታወስኩኝ።
፲፰ እንግዲህ፣ አዕምሮዬ በዚህ ሀሳብ ላይ በተያዘበት ጊዜ፣ በልቤ እንዲህ በማለት አለቀስኩ፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው ኢየሱስ ሆይ፣ ሀለተማረርኩት፣ እና በዘለዓለማዊው የሞት ለሰንሰለት ለተከበብኩት፣ ምህረትህ በእኔ ላይ አድርግልኝ።
፲፱ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ይህንን ባሰብኩ ጊዜ፣ ህመሜን ደግሞ ለማስታወስ አልቻልኩም፤ አዎን፣ ከእንግዲህም ወዲያ በኃጢአቴ ትውስታ ሀአልተሰቃየሁም።
፳ እናም አቤቱ፣ እንዴት ያለ ሀደስታ ተሰማኝ፤ እናም ምን ዓይነት አስደናቂ ብርሃንን አይቻለሁ፤ አዎን፣ ነፍሴ በህመም እንደተሰቃየች ሁሉ ታላቅ በሆነም ደስታ ተሞላች!
፳፩ አዎን፣ ልጄ እንዲህ እልሃለሁኝ፥ እንደ እኔ ህመም ሀያልና መሪር የሆነ ምንም ሊኖር አይችልም። አዎን፣ እናም በድጋሚ ልጄ እንዲህ እልሃለሁ፥ በሌላ መልኩ፣ እንደ እኔ ደስታ ሀያልና ጣፋጭ ሊሆን የሚችል ምንም የለም።
፳፪ አዎን፣ አባታችን ሀሌሂ እንደተመለከተው እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ ለአምላካቸው በመዘመር እናም በማወደስ ላይ ባሉት ስፍር ቁጥር በሌላቸው መላዕክት ተከቦ የተመለከትኩ መሰለኝ፤ አዎን እናም ነፍሴ በእጅጉ በዚያ ስፍራ መሆንን ናፈቀች።
፳፫ ነገር ግን እነሆ፣ እጆቼና እግሮቼ ሀብርታትን በድጋሚ አገኙ፣ እናም በእግሬ ቆምኩና፣ ለህዝቡም ለከእግዚአብሔር መወለዴን ገለፅኩ።
፳፬ አዎን፣ እናም ከዚያን ጊዜ እስከአሁን ድረስ እንኳን፣ ነፍሳትን ወደ ንስሃ አመጣ ዘንድ፣ እኔ ወደ ሀቀመስኩት ታላቅ ደስታ እነርሱንም እንዲቀምሱ አመጣቸው ዘንድ፣ እነርሱም ከእግዚአብሔር እንዲወለዱ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ለይሞሉ ዘንድ ሳላቋርጥ ሠርቻለሁ።
፳፭ አዎን፣ እናም አሁን እነሆ ልጄ ሆይ፣ ጌታ በስራዬ ፍሬም እጅግ ታላቅ የሆነ ደስታን ይሰጠኛል።
፳፮ እኔ እንዳውቀው ባደረገው ሀቃል የተነሳ፣ እነሆ ብዙዎች ከእግዚአብሔር ተወልደዋልና፣ እኔ የቀመስኩትን ቀምሰዋል፤ እናም እኔ የተመለከትኩትን ተመልክተዋል፤ ስለዚህ የተናገርኳቸውን ነገሮች እኔ እንደማውቅ ያውቃሉ፤ እናም ያለኝ እውቀት ከእግዚአብሔር ነው።
፳፯ እናም በሁሉም ዓይነት ፈተናና፣ መከራ፣ አዎን፣ በሁሉም ዓይነት ስቃይ ተደግፌአለሁ፤ አዎን፣ እግዚአብሔር ከወህኒ፣ ከእስራትና፣ ከሞት አድኖኛል፤ አዎን፣ እናም እምነቴን በእርሱ አደርጋለሁ፣ አሁንም እኔን ሀያድነኛል።
፳፰ እናም ሀበክብር ከእርሱ ጋር እንድኖር በመጨረሻው ቀን ለእንደሚያስነሳኝ አውቃለሁ፤ አዎን አባቶቻችንን ከግብፅ ሐስላስወጣና፣ መግብፃውያን በቀይ ባህር እንዲሰምጡ ስላደረገ እርሱን ለዘለዓለም አወድሳለሁ፤ እናም በኃይሉ ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር መርቷቸዋል፤ አዎን፣ እናም በተለያዩ ጊዜያት ከባርነትና ከምርኮ አስለቅቋቸዋል።
፳፱ አዎን፣ እናም ደግሞ አባቶቻችንን ከኢየሩሳሌም ምድር አስወጥቷል፤ ደግሞም በዘለዓለማዊው ኃይሉ እነርሱን ሀከባርነትና ከምርኮ፣ በየጊዜው እስከ አሁን ድረስም እንኳን፣ አስለቅቋል፤ እናም እኔም ሁልጊዜ ምርኮአቸውን አስታውሳለሁ፤ አዎን፣ እናም ደግሞ አንተም ምርኮአቸውን እኔ እንደአደረግሁት ማስታወስ ይገባሀል።
፴ ነገር ግን እነሆ፣ ልጄ፣ ይህ ብቻም አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስከጠበቅህ ሀድረስ በምድሪቱ እንደምትበለፅግ እኔ እንደማውቀው ማወቅ አለብህ፤ እናም ደግሞ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስካልጠበቅህ ድረስ ከፊቱ እንደምትወገድ ማወቅ አለብህ። እንግዲህ ይህ በእርሱ ቃል መሰረት ነው።