ምዕራፍ ፳፱
አልማ በመለኮታዊ ቅንዓት ንስሃን ለመጮህ ፈለገ—ጌታ ለሁሉም ሀገር አስተማሪዎችን ሰጠ—አልማ በጌታ ስራ፣ እናም በአሞንና በወንድሞቹ ስኬታማነት ተደሰተ። በ፸፮ ም.ዓ. ገደማ።
፩ አቤቱ፣ እንድሄድ እናም ምድሪቱን በሚያንቀጠቅጠው ድምፅ፣ በእግዚአብሔር መለከት እናገር ዘንድና ለማንኛውም ሰው ንስሃን እናገር ዘንድ፣ መልዓክ በሆንኩና የልቤም መሻት በሞላልኝ!
፪ አዎን፣ ንስሃ እንዲገቡና ሀወደአምላካችን እንዲመጡ፣ በምድሪቱ ገፅ ላይም ከዚህ የበለጠ ሀዘን እንዳይኖር፣ እንደነጎድጓድም ድምፅ ለማንኛውም ነፍስ ንስሃን እናም የቤዛነትን ዕቅድ አውጅ ነበር።
፫ ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ሰው ነኝ፤ እናም በፍላጎቴ ኃጢያትን እሰራለሁ፤ ምክንያቱም ጌታ በሰጠኝ ነገሮች መረካት ይገባኛልና።
፬ ጠንካራ የሆነውን ፍትሀዊውን የአምላክ አዋጅ በፍላጎቴ መለወጥ አይገባኝም፣ ምክንያቱም ለህይወታቸውም ይሁን ለሞታቸው ሀእንደፍላጎታቸው እርሱ እንዲሰጣቸው አውቃለሁ፤ አዎን ለሰዎች እንደ ለፈቃዳቸው ለደህንነትም ይሁን ለጥፋት መደብ፣ አዎን መለወጥ የማይችል አዋጅ በማወጅ እንደሚሰጣቸው አውቃለሁ።
፭ አዎን፣ እናም መልካምና መጥፎ የሆነው በሰዎች ሁሉ ፊት እንደመጣ አውቃለሁ፤ መልካሙን ከመጥፎው የማያውቅ እንከን የለሽ ነው፤ ነገር ግን መልካምና መጥፎውን ሀለሚያውቅ ለእርሱ እንደፍላጎቱ፣ ፍላጎቱ መልካምም ይሁን መጥፎ፣ ህይወትም ይሁን ሞት፣ ደስታም ይሁን ለየህሊና ፀፀት ይሰጠዋል።
፮ እንግዲህ፣ እነዚህን ነገሮች ማወቄን በመመልከት፤ ከተጠራሁበት የበለጠ ስራስ ለማከናወን ለምን እፈልጋለሁ?
፯ ለምንስ መልአክ ሆኜ እስከምድር ዳርቻ መናገር እስከምችል እመኛለሁ?
፰ እነሆም ጌታ ሀለሀገሮች ሁሉ ቃሉን በጥበብ፣ አዎን፣ ሊኖራቸው ለየሚገባውን ነገር ሁሉ እንዲያስተምሩ የራሳቸውን ሀገር እና ሐቋንቋ ሰጥቷል፤ ስለዚህ ጻድቅና እውነት በሆነው መሰረት ጌታ በጥበቡ እንደሚመሰክር እንመለከታለን።
፱ ጌታ ያዘዘኝን አውቃለሁ፣ እናም በዚህም እደሰታለሁ። በራሴ ሀአልኮራም፣ ነገር ግን ጌታ እኔን ባዘዘኝ በዚያ እኮራለሁ፤ አዎን፣ ይህም ምናልባት ጥቂት ነፍሳትን ወደ ንስሃው በማምጣት በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ እሆን ዘንድ በዚህ እመካለሁ፤ እናም ይህም የእኔ ደስታ ነው።
፲ እናም እነሆ፣ ብዙዎቹ ወንድሞቼ በእውነት ንስሃ መግባታቸውን፣ እና ወደጌታ አምላካቸው መምጣታቸውን በተመለከትኩ ጊዜ፣ ከዚያም ነው ነፍሴ በደስታ የተሞላችው፤ በዚያም ሀጌታ ምን እንዳደረገልኝ፣ አዎን፣ ፀሎቴንም እንኳን እንደሰማልኝ ለማስታወስ እችላለሁ፤ አዎን በዚያም የምህረት ክንዶቹ በእኔ ላይ መዘርጋታቸውንም አስታውሳለሁ።
፲፩ አዎን፣ እናም ደግሞ የአባቶቻችንን ምርኮ አስታውሳለሁ፤ ሀጌታ ከባርነት እንደለቀቃቸው በእርግጥ አውቃለሁ፣ እናም በዚህም ቤተክርስቲያኗን አቋቁሟል፤ አዎን፣ ጌታ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሀቅ አምላክ፣ እንዲሁም የያዕቆብ አምላክ ከባርነት ለቋቸዋል።
፲፪ አዎን፣ የአባቶቻችንን ምርኮ ሁልጊዜም አስታውሳለሁ፤ እናም ከግብፃውያን እጅ ሀያስለቀቃቸው አምላክ ከባርነት እነርሱንም አስለቅቋል።
፲፫ አዎን፣ እናም ይኸው አምላክ ቤተክርስቲያኗን በመካከላቸው አቋቁሟል፤ አዎን፣ ይኸውም አምላክ ቃሉን ለህዝቡ እንድሰብክ በቅዱሱ ጥሪው ጠራኝ፤ እናም ብዙ ድልም ሰጠኝ፤ በዚህም ሀደስታዬ የተሞላ ነው።
፲፬ ነገር ግን በራሴ ስኬታማነት ብቻ አልደሰትም፣ ነገር ግን በኔፊ ምድር በነበሩት ወንድሞቼ ሀስኬታማነት ደስታዬ ይበልጥ ሙሉ ነው።
፲፭ እነሆ፣ እነርሱ እጅግ ሰሩም፣ በርካታ ፍሬን አምጥተዋልም፤ እናም ደመወዛቸው እንዴት ታላቅ ይሆናል!
፲፮ አሁን፣ የእነዚህን የወንድሞቼን ስኬት ባሰብኩ ጊዜ ነፍሴ ከስጋዬ እንደተለየች ያህል ትወሰዳለች፣ በመሆኑም ደስታዬም ታላቅ ነው።
፲፯ እናም አሁን እግዚአብሔር ለወንድሞቼ በእግዚአብሔር መንግስት እንዲቀመጡ ለእነርሱ ይፈቀድላቸው፤ አዎን፣ እናም ደግሞ የስራቸው ውጤት የሆኑት ሁሉ ከእንግዲህ እንዳይሄዱባቸው፤ ነገር ግን ለዘለዓለም እርሱን ያወድሱት። እናም እኔ እንደተናገርኩት እንደቃሌም እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን። አሜን።