ምዕራፍ ፲፭
የሌሂ ዘሮች በኋለኛው ቀናት ከአህዛብ ወንጌልን ይቀበላሉ—የእስራኤልም መሰባሰብ የተፈጥሮ ቅርንጫፎቹ መልሰው እንደሚጣበቁ የወይራ ዛፍ ጋር ይመሳሰላል—ኔፊ የህይወት ዛፍን ራዕይ ተረጎመ እናም እግዚአብሔር ኃጢአተኛን ከፃድቅ ስለሚለያይበት ፍትህ ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ፣ በመንፈስ ከተወሰድኩና እነዚህን ሁሉ ነገሮች ካየሁ በኋላ ወደአባቴ ድንኳን ተመለስኩ።
፪ እናም እንዲህ ሆነ ወንድሞቼን ተመለከትኩ፣ እነርሱም አባቴ ለእነርሱ የተናገራቸውን ነገሮች በተመለከተ እርስ በእርሳቸው እየተከራከሩ ነበር።
፫ ሰው ጌታን ካልጠየቀ በቀር ሀለመረዳት የሚያስቸግሩ ብዙ ታላቅ ነገሮችንም ነበር በእውነት ለእነርሱ ነግሯቸዋልና፤ እነርሱ በልቦቻቸው መጠጠር የተነሳ ማድረግ እንደነበረባቸው ወደጌታ አልተመለከቱም።
፬ እናም አሁን እኔ ኔፊ በልባቸው ጠጣርነት፣ ደግሞም ባየሁአቸው ነገሮች ምክንያትና በሰዎች ልጆች ታላቅ ኃጢያት ምክንያት ሊወገዱ በማይችሉ መምጣት እንዳለባቸው ስላወቅሁ እጅግ አዘንኩ።
፭ እናም እንዲህ ሆነ በራሴ ሀዘን ምክንያት ተሸነፍኩ፣ ምክንያቱም ውድቀታቸው እንዴት እንደሚሆን ስለተመለከትኩ፣ በህዝቤ ሀጥፋት ምክንያት የእኔ ለሀዘን ከማንኛውም በላይ ታላቅ እንደነበር ተሰማኝ።
፮ እናም እንዲህ ሆነ ሀጥንካሬን ካገኘሁ በኋላ ወንድሞቼን የክርክራቸው ምክንያት ምን እንደነበር ለማወቅ ተናገርኳቸው።
፯ እናም እነሆ የተፈጥሮ ወይራ ዛፍን ቅርንጫፎችና፣ ደግሞም አህዛብን በተመለከተ አባታችን የተናገራቸውን ነገሮች ለመረዳት አንችልም አሉ።
፰ እናም እንዲህ አልኳቸው፥ እናንተ ጌታን ሀጠይቃችኋልን?
፱ እናም እንዲህ አሉኝ—አልጠየቅንም፣ ምክንያቱም ጌታ እኛን እንዲህ ያሉ ነገሮችን አያሳውቀንም።
፲ እነሆ እነርሱን አልኳቸው—እንዴት ነው እናንተ የጌታን ትዕዛዝ የማትጠብቁት? እንዴት ነው በልባችሁ ሀጠጣርነት የተነሳ የምትጠፉት?
፲፩ ጌታ የተናገራቸውን ነገሮች አታስታውሱምን?—ልባችሁን ባታጠጥሩ እናም መልስ እንደምታገኙም በማመን ትዕዛዛቴን ለመጠበቅ በመትጋት በእምነት ሀብትጠይቁኝ፣ በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ግልፅ ይሆናሉ።
፲፪ እነሆ እላችኋለሁ የእስራኤል ቤት ከወይራው ዛፍ ጋር የተመሳሰለው በአባታችን ውስጥ በነበረው በጌታ መንፈስ ነበር፤ እናም እነሆ እኛ ከእስራኤል ቤት የተሰበርን አይደለንምን? ደግሞስ የእስራኤል ቤት ሀቅርንጫፎች አይደለንምን?
፲፫ እናም አሁን በአህዛብ ሙላት የተፈጥሮ ቅርንጫፎች መጣበቅ በተመለከተ አባታችን የተናገረው ነገር በኋለኛው ቀናት ዘሮቻችን እምነት በማጣት ሀሲመነምኑ፣ አዎን፣ ለብዙ ዓመታት፣ እንዲሁም ለመሲሁ ለሰዎች ልጆች እራሱን ከገለፀ ከብዙ ትውልዶች በኋላ፣ ከዚያም የመሲህ ሐወንጌል ሙሉነት መለአህዛብ፣ ከአህዛብም ወደ ዘሮቻችን ቅሪት ይመጣል—
፲፬ እናም በዚያ ቀን ሀየዘሮቻችን ቅሪት ከእስራኤል ቤት መሆናቸውን፣ እነርሱም የጌታ ለየቃል ኪዳን ህዝቦች መሆናቸውን ያውቃሉ፤ ከዚያም እነርሱ ቅድመ አባቶቻቸው ወደማወቅ፣ ደግሞም በእርሱ አባቶቻቸው የተማሩትን የመድኃኒታቸውን ወንጌል ያውቃሉም፣ ሐለእውቀትም ይደርሳሉ፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ መድኃኒታቸው እውቀትና፣ ወደእርሱ እንዴት እንደሚመጡና እንደሚድኑ ያውቁ ዘንድ ወደ ትምህርቱ እያንዳንዱ ነጠቦች በእውቀትም ይደርሳሉ።
፲፭ በዚያም ቀን አይደሰቱምን እና ሀአለታቸውና አዳኛቸው ለሆነው ለዘለአለማዊው አምላክ ምስጋናን አያቀርቡምን? አዎን፣ በዚያ ቀን እነርሱ ከእውነተኛው ለወይን ጥንካሬንና ጥቅም አያገኙምን? አዎን፣ ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር በረት አይመጡምን?
፲፮ እነሆ እላችኋለሁ፣ አዎን፣ እነርሱ በድጋሚ በእስራኤል ቤት መካከል ይታወሳሉ፤ ምክንያቱም የወይራ ዛፍ የተፈጥሮ ቅርንጫፎች በመሆናቸው ከእውነተኛው የወይራ ዛፍ ጋር ሀይጣበቃሉና።
፲፯ አባታችንም ይህን ማለቱ ነው፤ እንዲሁም በአህዛብ እስከሚበተኑም ድረስ አይሆንም ማለቱ ነው፤ እና ማለቱም ጌታ ለአህዛብ ኃይሉን ያሳያቸው ዘንድ፣ ይህም በአህዛቦች አማካኝነት ይመጣል፣ ምክንያቱም በአይሁዶች ወይም እስራኤል ቤት ሀተቀባይነት አያገኝምና።
፲፰ ስለዚህ አባታችን ስለ እኛ ዘር ብቻ ሳይሆነ ነገር ግን ስለ እስራኤል ቤት ሁሉ ተናግሯል፣ በኋለኛው ቀን የሚፈፀመውን ቃል ኪዳን አመልክቷል፤ ይኸውም ጌታ ለአባታችን አብርሃም እንዲህ በማለት የገባው ቃል ኪዳን ነው፥ ሀበዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ።
፲፱ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ ለእነርሱ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ብዙ ተናገርኩ፤ አዎን፣ በኋለኛው ቀናት ስለአይሁዶች ሀበዳግም መመለስን በሚመለከትም ለእነርሱ ተናገርኩ።
፳ እናም ለእነርሱ ስለ አይሁዶች ወይም ስለ እስራኤል ቤት መመለስ ሀኢሳይያስ የተናገረውን ቃል፣ እንዲሁም እነርሱ ከተመለሱ በኋላ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እንደማይቀላቀሉ፣ በድጋሚም እንደማይበተኑ አስረዳኋቸው። እናም እንዲህ ሆነ ለወንድሞቼ እንዲረጋጉና በጌታ ፊት እራሳቸውን ለትሁት እንዲያደርጉ ብዙ ቃል ነገርኳቸው።
፳፩ እናም እንዲህ ሆነ በድጋሚ እንዲህ ሲሉ ተናገሩኝ—አባታችን በህልሙ ያየው ይህ ነገር ምን ማለት ነው? እርሱ ያየው ሀዛፍስ ምን ማለት ነው?
፳፪ እናም አልኳቸው—እሱ ሀየህይወት ዛፍ ምልክት ነበር።
፳፫ እናም እንዲህ አሉኝ—ወደዛፉ የሚመራን አባታችን ያየው ሀየብረት በትር ምን ማለት ነው?
፳፬ ይህም የእግዚአብሔር ሀቃል ነበር አልኳቸው፤ እናም የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙ ሁሉና፣ እርሱን አጥብቆ ለየያዘ በፍፁም አይጠፋም፤ ሐፈተናዎችና መየጠላት ክፉ ሠፍላፃ እነርሱን ወደጥፋት ለመውሰድ በማሳወር ሊያሸንፏቸው አይችሉም።
፳፭ ስለዚህ እኔ ኔፊ የጌታን ቃል በጥብቅ ሀእንዲያዳምጡ አበረታታኋቸው፤ አዎን፣ በውስጤ ባለው ኃይል ሁሉ እናም ባለኝ ችሎታ ሁሉ የጌታን ቃል በጥብቅ ያዳምጡ ዘንድ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች ሁል ጊዜ ትዕዛዛቱን በመጠበቅ እንዲያስታውሱት መከርኳቸው።
፳፮ እናም ተናገሩኝ—አባታችን የተመለከተው ሀየወንዙ ውሃ ምን ማለት ነው?
፳፯ እናም አባቴ ያየው ሀውኃ ለርኩሱን ነገር ነበር አልኳቸው፤ አእምሮውም ሌሎች ነገሮችን በማሰብ የተሞላ ስለነበር የውሀውን ርኩስነት ልብ አላለውም ነበር።
፳፰ እናም ኃጢአተኞችን ከህይወት ዛፍ፣ እናም ደግሞ ከእግዚአብሔር ቅዱሳን የሚለያይ አሰቃቂ ሀገደል ነበር አልኳቸው።
፳፱ እናም ይህ የአሰቃቂው ሀሲኦል ምልክት ነበር፣ እርሱም መልአኩ እንደነገረኝ ለኃጢኣተኞች የተዘጋጀ ነበር አልኳቸው።
፴ እናም አባታችን የእግዚእብሔር ሀፍትህ ደግሞ ኃጢአተኞችን ከፃድቃን እንደሚለይ እንዳየ፣ ድምቀቱም በመቀጠል ለዘለዓለም ወደ እግዚአብሔር እንደሚመጣና መጨረሻ እንደሌለው ልክ እንደነበልባል እሳት ደምቆ እንደነበር ነገርኳቸው።
፴፩ እናም እነርሱ ለእኔ አሉኝ—ይህ ነገር በምድር ሀየሙከራ ጊዜያችን በሟች የሰውነታችን ስቃይ ማለት ነው፣ ወይስ ይህ ከጊዜያዊው ሰውነት ለሞተ በኋላ የመጨረሻው የነፍስ ሁኔታ ማለት ነው፣ ወይስ የሚናገረው ነገር ጊዜያዊ ስለሆኑት ነገሮች ነው?
፴፪ እናም እንዲህ ሆነ እንዲህ አልኳቸው—ይህ ለጊዜያዊና ለመንፈሳዊ ነገሮች ምልክት ነበር፣ በስራዎቻቸው አዎን፣ እንዲሁም በሙከራ ጊዜያቸው በሟች ሰውነታቸው በተደረጉት ሀስራዎች፣ ሊፈረድባቸው ይገባል።
፴፫ ስለዚህ በኃጢኣታቸው ሀየሚሞቱ ከሆኑ፣ ከፅድቅነት ጋር ከተገናኙ መንፈሳዊ ነገሮች ለመገለል ደግሞ ይገባቸዋል፤ ስለዚህ ሐበስራቸው መእንዲፈረድባቸውም በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መምጣት አለባቸው፤ እናም ስራቸው የረከሰ ከሆነ እነርሱም ሠየረከሱ መሆን አለባቸው፤ የረከሱ ከሆኑም ደግሞ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ረመኖር አይችሉም፤ እንዲህም ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ደግሞ የረከሰ መሆን አለበት።
፴፬ ነገር ግን እነሆ እላችኋለሁ የእግዚአብሔር መንግስት ሀየረከሰ አይደለም፣ እናም ማንኛውም እርኩስ ነገር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም፤ ስለዚህ ርካሽ ለሆነው የተዘጋጀ የረከሰ ቦታ ሊኖር ይገባዋል።
፴፭ እናም የተዘጋጀ ቦታ፣ አዎን፣ እንዲሁም የተናገርኩት አሰቃቂው ሀገሀነም አለ፣ የዚህም አዘጋጅም ለዲያብሎስ ነው፤ ስለዚህ የሰዎች ነፍሶች የመጨረሻ ሁኔታ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር፣ ወይም በተናገርኩት ሐፍትህ ምክንያት ወደውጭ መጣል ነው።
፴፮ ስለዚህ ኃጢአተኞች ከፃድቃን ጋር እናም ደግሞ ፍሬው እጅግ ያማረና ከሌሎች ፍሬዎች በላይ እጅግ ሀተፈላጊ ከሆነው ለየህይወት ዛፍ ይለያሉ፤ አዎን፣ ይህ ከእግዚአብሔር ሐስጦታዎች ሁሉ መየበለጠ ነው። እንደዚህም ነበር ለወንድሞቼ የተናገርኩት። አሜን።