ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፳


ምዕራፍ ፳

ጌታ ዓላማውን ለእስራኤል ገለጠ—እስራኤልም በመከራ እቶን ተመረጠች፣ እናም ከባቢሎን ትወጣለች—ኢሳይያስ ፵፰ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ እናንተ ከይሁዳ ውኃ ይሁን ከጥምቀት ውኃ የወጣችሁ፣ በጌታ ስም የምትምሉ፣ በእውነት ሳይሆን፣ በፅድቅ ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ የያዕቆብ ቤት ሆይ ይህን ስሙ እናም አድምጡ።

ይሁን እንጂ በቅድስት ከተማ ስም እራሳቸውን ይጠራሉ፣ ነገር ግን የሰራዊት ጌታ በሆነው በእስራኤል አምላክ ላይ አይደገፉም፤ አዎን፣ የሰራዊት ጌታ የእርሱ ስም ነው።

እነሆ የቀድሞውን ነገሮች ከጥንት ጀምሮ ተናግሬአለሁ፤ ከአፌም ወጥተዋል፣ አሳይቼአቸዋለሁ። በድንገትም አሳየኋቸው።

እናም ይህንን ያደረግሁት አንተ እልከኛ፣ አንገትህም የብረት ጅማት፣ ግንባርህም ናስ እንደሆነ ስለማውቅ ነው፤

እናም ጣኦቴ ይህን አድርጓል፣ የተቀረፀው ምስሌ፣ ቀልጦ የተሰራው ምስሌ እነዚህን አዘዘኝ እንዳትል ፈርቼ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፤ ሳይሆንም አስተምሬህ ነበር።

ይህን ሁሉ ተመልክተሀልና ሰምተሀል፤ እናም አንተ አትናገራቸውምን? አዲስ ነገሮች፣ እንዲሁም የተደበቁትንም ነገሮች፣ ከዚህ ጀምሮ አሳይቼህ ነበር፣ እና አንተ አላወቅሀቸውም።

እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት ጀምሮ አልተፈጠሩም፣ አንተም እነሆ፥ አውቄአቸዋለሁ እንዳትል ስለእነዚህ ከመስማትህ በፊት ለአንተ ተገልጠውልህ ነበር።

አዎን እናም አልሰማህም፣ አዎን አላወቅህም፤ አዎን ጆሮህም በዚያን ጊዜ አልተከፈተም፣ ምክንያቱም አንተ ፈፅሞ ወንጀለኛ እንደሆንክ ከማህፀንም ጀምሮ ህግን ተላላፊ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።

ይሁን እንጂ ስለስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፣ ስለምስጋናዬም ስል እንዳላጠፋህ ዘንድ እለይሃለሁ።

ምክንያቱም እነሆ አንጥሬሀለሁ፣ በመከራም እቶን መርጬሀለሁ።

፲፩ ስለእኔ አዎን ስለራሴ ይህን አደርገዋለሁ፣ ምክንያቱም ስሜ እንዲነቀፍ አልፈቅድም፣ እናም ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም

፲፪ ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ ስሙኝ፣ ምክንያቱም እኔ ነኝና፤ እኔ የፊተኛው እናም ደግሞ እኔ መጨረሻው ነኝ።

፲፫ እጄም ደግሞ የምድርን መሰረት መስርታለች፣ ቀኝ እጄም ሰማያትን ዘርግታለች። ጠራኋቸው እናም በአንድ ላይ ቆሙ።

፲፬ እናንተ ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስባችሁ አድምጡ፤ ከእነርሱ እነዚህን ነገሮች ያወጀላቸው ማን ነው? ጌታ እርሱንም ወድዶታል፤ አዎን እርሱም በእነርሱ የተናገረውን ቃል ይፈፅማል፣ እርሱም እንደሚያስደስተው በባቢሎን ላይ ያደርጋል፣ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።

፲፭ ደግሞም ጌታ እንዲህ ይላል፤ እኔ ጌታ አዎን እኔ ተናገርኩ፤ አዎን እርሱን እንዲያውጅ ጠራሁት፣ አምጥቼውማለሁ፣ መንገዱንም ቀና ያደርጋል።

፲፮ ወደ እኔ ቅረቡ፣ እኔ በስውር አልተናገርኩም፤ ከጥንት ጀምሮ፣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ እኔ ተናገርኩ፣ እናም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

፲፯ እናም መዳኒትህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እንዲህ ይላል፤ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ፣ በምትሄድበትም መንገድ የሚመራህ እኔ ጌታህ እግዚአብሔር ልኬዋለሁ።

፲፰ አቤቱ ትዕዛዛቴን ብትሰማ ኖሮ ሰላምህ እንደወንዝ፣ ፅድቅህም እንደባህር ሞገድ ይሆን ነበር።

፲፱ ዘርህም ደግሞ እንደ አሸዋ በሆነ ነበር፤ የሆድህም ትውልድ እንደባህር ጠጠር በሆነ ነበር፤ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋ ወይም ባልፈረሰ ነበር።

ከባቢሎን ውጡ፣ ከከለዳውያንም ኮብልሉ፣ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፣ ይህንም ተናገሩ እስከምድር ዳርቻ ድረስ አውሩ፤ ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል በሉ።

፳፩ እናም አልተጠሙም ነበር፤ በበረሃ ውስጥ መራቸው፤ ውሃውንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፤ ዓለቱንም ደግሞ ሰነጠቀውና ውኃው ፈለቀ።

፳፪ እናም ይህንን ሁሉና፣ ደግሞ ታላቅ ነገር ቢያደርግም፣ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል ጌታ።