ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፲፫


ምዕራፍ ፲፫

ኔፊ በአህዛቦች መካከል የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን መቋቋምን፣ የአሜሪካ መገኘትና ቅኝ መያዝን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ብዙ የተከበሩና ግልፅ ክፍሎች መጥፋትን፣ የእዚህም ውጤት የሆነውን የአሕዛብ ክህደት ሁኔታን፣ የወንጌል መመለስን፣ የኋለኛው ቀን ቅዱስ መፅሐፍት መምጣትን፣ እና የፅዮንን ግንባታ በራዕይ አየ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረኝ—ተመልከት! እናም እኔ ብዙ ሀገሮችንና መንግስታትን ተመለከትኩ።

መልአኩም ምን አየህ? አለኝ፣ እናም ብዙ ሀገሮችና መንግስታትን ተመለከትኩ አልኩት።

እናም እርሱ እነዚህ የአህዛብ ሀገሮችና መንግስታት ናቸው አለኝ።

እናም እንዲህ ሆነ በአሕዛብ ሀገሮች መካከል ትልቅ ቤተክርስቲያን ሲቋቋም አየሁ።

መልአኩም አለኝ፣ ከሌሎች ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በላይ የርኩሰቱን ቤተክርስቲያን አመሰራረት ተመልከት፣ ይኸውም የእግዚአብሔርን ቅዱሳን የሚገድለውን፣ አዎን፣ ያስራቸዋልም፣ ያሰቃያቸዋልም፣ በብረት ቀንበርም ይጠምዳቸዋል፣ በኃይልም ይማርካቸዋል።

እናም እንዲህ ሆነ ይህን ታላቋና የርኩሰቱን ቤተክርስቲያን ተመለከትኩ፤ መስራቹም ዲያብሎስ እንደሆነም አየሁ።

ደግሞም ወርቅ፣ ብር፣ ሐርና፣ ቀይ ግምጃዎች እናም የተፈተለ ጥሩ በፍታ፣ እንዲሁም ሁሉም አይነት የከበሩ ልብሶችን አየሁ፤ ብዙ ጋለሞታዎችንም አየሁ።

መልአኩም እንዲህ ሲል ተናገረኝ—እነሆ ወርቁና፣ ብሩና፣ ሐሩና፣ ቀይ ግምጃዎችና፣ የተፈተለ ጥሩ በፍታን፣ እንዲሁም የከበሩት ልብሶችና ጋለሞታዎች፣ የዚህ ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን ፍላጎቶች ናቸው።

እናም ደግሞ ለዓለም ምስጋና ሲሉ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ያጠፋሉ፣ ወደ ምርኮም ያመጧቸዋል።

እናም እንዲህ ሆነ እነሆ ተመለከትኩና ብዙ ውኃዎችን አየሁ፤ እናም እነርሱም አህዛቦችን ከወንድሞቼ ዘር ያለያያሉ።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ አለኝ፣ እነሆ የእግዚአብሔር ቁጣ በወንድሞችህ ዘር ላይ ነው።

፲፪ እናም ከወንድሞቼ ዘር በብዙ ውሀዎች ተለይተው ከነበሩ አህዛብ መካከል አንድ ሰው አየሁና ተመለከትኩ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ወርዶ በሰውየው ላይ ሲሰራም አየሁ፤ እናም የወንድሞቼ ዘር ወዳለበት ወደ ቃልኪዳኑ ምድር እንኳን በብዙ ውኃዎች ላይ ሄደ።

፲፫ እናም እንዲህ ሆነ የእግዚአብሔርን መንፈስ በሌሎች አህዛቦች ላይ እንደሰራ ተመለከትኩ፣ እናም እነርሱ ከምርኮ ወጥተው በብዙ ውኃዎች ላይ ተጓዙ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ከአህዛብ ብዙ ሰዎችን በቃልኪዳኑ ምድር ላይ ተመለከትኩ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በወንድሞቼ ዘር ላይ እንደነበረ ተመለከትኩ፣ እነርሱም በአህዛቦች ፊት የተበተኑ፣ እና የተመቱም ነበሩ።

፲፭ እናም የጌታ መንፈስ በአህዛቦች ላይ እንደነበረ ተመለከትኩ፣ እነርሱም በለፀጉ፣ ምድሪቱንም ለርስታቸው ያዙ፤ እነርሱም የነጡና ልክ ከመገደላቸው በፊት እንደነበሩት እንደ ህዝቦቼ እጅግ ያማሩ እንደነበሩ ተመለከትኩ።

፲፮ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ ከምርኮ ወጥተው የሄዱት አህዛቦች በጌታ ፊት እራሳቸውን እንዳዋረዱ ተመለከትኩ፣ እናም የጌታ ኃይልም ከእነርሱ ጋር ነበር።

፲፯ እናም የአህዛቦች እናት ሀሮች በውኃዎቹ ላይ እንዲሁም ደግሞ በምድሩ ላይ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ተሰብስበው እንደነበር አየሁ።

፲፰ እናም የእግዚአብሔር ኃይል ከእነርሱ ጋር እንደነበር፣ ደግሞም የእግዚአብሔር ቁጣ እነርሱን ለመዋጋት በአንድ ላይ በተሰበሰቡት ላይ ሁሉ እንደነበር ተመለከትኩ።

፲፱ እናም እኔ ኔፊ ከምርኮ የወጡት አህዛብ ከሌሎች ሀገሮች እጆች በእግዚአብሔር ኃይል የዳኑ እንደሆነ አየሁ።

እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ በምድሪቱ እነርሱ በልፅገው አየሁ፣ እናም መጽሐፍን አየሁ፤ በመካከላቸውም ይዘውት እየሄዱም ነበር።

፳፩ እናም መልአኩ እንዲህ አለኝ—የመፅሐፉን ትርጉም ታውቃለህን?

፳፪ እናም አላውቀውም አልኩት።

፳፫ እርሱም አለ—እነሆ ይህ ከአይሁድ አፍ የወጣ ነው። እኔ ኔፊም ተመለከትኩ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ—አንተ ያየኸው መፅሐፍ የአይሁዶች መዝገብ ነው፤ ይህም እርሱ ከእስራኤል ቤት ጋር ያደረገውን የጌታን ቃልኪዳኖች የያዘ ነው፤ እናም ደግሞ የቅዱሳን ነቢያትን ብዙ ትንቢቶች የያዘ ነው፤ ይህም ብዙ ትንቢቶች ካለመኖራቸው በስተቀር ልክ በነሀስ ሰሌዳዎች ላይ እንደተቀረፁት አይነት መዝገብ ነው፤ ሆኖም ጌታ ለእስራኤል ቤት የገባውን ቃልኪዳኖች ይዘዋል፤ ስለዚህ እነርሱ ለአህዛብ ታላቅ ዋጋ አላቸው።

፳፬ የጌታ መልአክም አለኝ—ከአይሁድ አፍ የወጣውን መፅሐፍ ተመልክተሀል፤ እናም ከአይሁድ አፍ በወጣ ጊዜ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት የመሰከሩለትን የጌታን ወንጌል ሙሉነት ይዟል፤ እነርሱም በእግዚአብሔር በግ ውስጥ ባለው እውነታ መሰረት መሰከሩ።

፳፭ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ውስጥ ባለው እውነታ መሰረት ከአይሁዶች ወደ አህዛብ በንፅህና ይተላለፋሉ።

፳፮ እናም ከአይሁዶች ወደ አህዛብ በአስራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት እጆች ከተላለፈ በኋላ ከሌሎች ሁሉ ቤተክርስቲያኖች በላይ የበለጠ የረከሰውን ታላቋና የርኩሰቱን ቤተክርስቲያን መመስረት ተመልክተሀል፤ እነሆም እነርሱ ከበጉ ወንጌል ግልፅና እጅግ የከበሩትን ብዙ ክፍሎች ወስደዋል፤ ደግሞም ብዙ የጌታን ቃል ኪዳኖች አጥፍተዋል።

፳፯ እናም ይህን ሁሉ ነገር ያደረጉት የጌታን መንገድ ያጣምሙ ዘንድ፣ የሰው ልጆች ዐይናቸውን ያሳውሩና፣ ልባቸውን ያጠጥሩ ዘንድ ነበር።

፳፰ ስለዚህ መፅሐፉ በታላቋና በርኩሰቱ ቤተክርስቲያን እጆች ውስጥ ካለፉ በኋላ የእግዚአብሔር በግ መፅሐፍ ከሆነው መፅሐፍ ውስጥ ብዙ ግልፅና የከበሩ ነገሮች መወሰዳቸውን ተመልክተሀል።

፳፱ እናም እነዚህ ግልፅና የከበሩ ነገሮች ከተወሰዱ በኋላ ወደ አህዛቦች ሀገሮች ሁሉ ተወሰዷል፤ ለሁሉም የአህዛብ ሀገሮች፣ አዎን፣ እንዲሁም በብዙ ውኃዎች አቋርጠው ሲሄዱ አንተ ካየሀቸው ከምርኮ ከወጡት ከአህዛብ ጋር ከተወሰደ በኋላ—ይኸውም በእግዚአብሔር በግ ውስጥ በሆነው ግልፅነት መሰረት ለሰው ልጆች ግንዛቤ ግልፅ የነበሩት ብዙ ግልፅና የከበሩ ነገሮች ከመፅሐፉ በመወሰዳቸው ምክንያት—ከበጉ ወንጌል እነዚህ ነገሮች በመወሰዳቸው ምክንያት እጅግ ታላቅ ብዙዎችም፣ አዎን፣ ሰይጣንም እንኳን በእነርሱ ላይ ትልቅ ኃይል እስኪያገኝ ድረስ ተሰናከሉ።

ሆኖም ከምርኮ የወጡትን አህዛብ ጌታ እግዚአብሔር ከአባትህ ጋር ዘሮቹ የርስት ምድር ይኖራቸው ዘንድ ቃል ኪዳን የገባለት ምድር በሆነው፣ ከሌሎች ምድር ሁሉ በላይ በመረጠው የምድር ገፅ ላይ በእግዚአብሔር ሀይል ከሌሎች ሀገሮች ሁሉ በላይ ጠንካራ እንደተደረጉ ተመልክተሃል፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር ከወንድሞችህ ዘሮች ጋር የተቀላቀሉትን ያንተን ዘሮች አህዛብ ፈፅሞ እንዲያጠፏቸው አንደማይፈቅድም አይተሀል።

፴፩ አህዛብም የወንድሞችህን ዘር እንዲያጠፉ እርሱ አይፈቅድም።

፴፪ ጌታ እግዚአብሔር አህዛብ፣ ይኸውም የነበሩበትን እንደተመለከትከው፣ ግልፅና እጅግ የከበረው የበጉ ወንጌል ክፍል ሲሰራ ባየኸው በርኩሰቱ ቤተክርስቲያን ወደኋላ በመያዛቸው ምክንያት፣ በዚያ አስቃቂ በሆነው እውርነት ለዘለዓለም እንዲቀሩም አይፈቅድም።

፴፫ ስለዚህ የእግዚአብሔር በግ አለ—የእስራኤልን ቤት ቅሪት በታላቅ ፍርድ በመጎብኘት ለአህዛብ ምህረትን አደርጋለሁ።

፴፬ እናም እንዲህ ሆነ የጌታ መልአክ እንዲህ ሲል ተናገረኝ—እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ፣ የእስራኤልን ቤት ቅሪት ከጎበኘኋቸው በኋላ፤ እናም እኔ የተናገርኩት ይህ ቅሪት የአባትህ ዘር ነው—ስለዚህ እነርሱንም በፍርድ ከጎበኘኋቸው በኋላና በአህዛብም እጅ ከመታኋቸው በኋላ፣ እንዲሁም ይበልጥ ግልፅና የከበሩ የበጉ ወንጌል ክፍሎችን የጋለሞታዎች እናት በሆነችው የርኩሰት ቤተክርስቲያን በመወሰዳቸው ምክንያት አህዛብ እጅግ ከተሰናከሉ በኋላ ይላል በጉ፤ በዚያን ቀን ለአህዛብ መሀሪ እሆናለሁ፣ በዚህም ለእነርሱ በእኔ ኃይል ግልፅና የከበረ የሚሆነውን ብዙውን ወንጌሌን ለእነርሱ አመጣለሁ ይላል በጉ።

፴፭ እነሆም በጉ አለ—እኔ ራሴን ለዘሮችህ እገልፃለሁ፣ እነርሱም የማስተምረውን ግልፅና የከበሩ ነገሮች ይፅፋሉ፣ የአንተም ዘሮች ከጠፉና እምነት በማጣት ከመነመኑ በኋላ፣ ደግሞም የወንድሞችህ ዘሮች እምነት በማጣት ከመነመኑ በኋላ፣ እነሆ እነዚህ ነገሮች ለአህዛብ በበጉ ስጦታና ኃይል ይገለጡ ዘንድ ይደበቃሉ።

፴፮ እናም በጉ በእነዚህ ነገሮች ውስጥ የእኔ ወንጌልናአለትና ደህንነት ይጻፋሉ አለ።

፴፯ በእዚያም ቀን የእኔን ፅዮን ለማምጣት የፈለጉት የተባረኩ ናቸው፣ እነርሱም የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስጦታ ይኖራቸዋልና፤ እንዲሁም እስከ መጨረሻ የሚፀኑ ከሆነ በመጨረሻው ቀን ከፍ ይደረጋሉ፣ በዘለአለማዊው የበጉ መንግስት ውስጥ ይድናሉም፤ እናም ሰላምን የሚያወሩ፣ አዎን የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገሩ፣ በተራሮች ላይ እንዴት ያማሩ ይሆናሉ።

፴፰ እናም እንዲህ ሆነ የወንድሞቼ ዘር ቅሪት የሆኑትን እናም ደግሞ ከአይሁድ አንደበት የወጣው የእግዚአብሔር በግ መጽሐፍን፣ ይህም ለወንድሞቼ ዘር ቅሪት ከአህዛብ እንደመጣ ተመለከትኩ።

፴፱ እናም ይህም ለእነሱ ከመጣ በኋላ፣ አህዛብን፣ የወንድሞቼን ዘር ቅሪት፣ ደግሞም በምድር ገፅ ላይ የተበተኑት አይሁዶችን ሁሉ፣ የነቢያት መዝገቦችና የበጉ አስራ ሁለት ሐዋርያት እውነት እንደሆኑ ለማሳመን በበጉ ኃይል ከአህዛብ ለእነሱ ሌሎች መጽሐፎች ሲመጡ አየሁ።

እናም መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረኝ—ከአህዛቦች መካከል ያየሀቸው እነዚህ የመጨረሻው መዝገቦች፣ ከበጉ አስራ ሁለት ሐዋርያት የሆኑትን የመጀመሪያውን እውነት ያረጋግጣሉ፤ ከእነርሱ የተወሰዱትን ግልፅና የከበሩ ነገሮች እንዲታወቁም ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርም በግ የዘለአለማዊው አባት ልጅና የአለም አዳኝ እንደሆነ፣ እንዲሁም ሁሉም ሰዎች ወደ እርሱ መምጣት እንዳለባቸው ወይም መዳን እንደማይችሉ ለሁሉም ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝቦች እንዲታወቁ ያደርጋሉ።

፵፩ እናም እነርሱ በበጉ በተመሰረቱት ቃላት መሰረት መምጣት አለባቸው፣ የበጉም ቃላት በአንተ ዘሮች መዝገቦች ውስጥ፣ እንዲሁም በአስራ ሑለቱ የበጉ ሐዋሪያት መዝገቦች ውስጥ ይታወቃሉ፤ ስለዚህ ሁለቱም በአንድነት ይመሰረታሉ፤ በምድር ላይ ሁሉ አንድ አምላክ እና አንድ እረኛ አለና።

፵፪ እናም ለሁሉም ሀገር፣ ለአይሁዶችና ደግሞ ለአህዛብ፣ እራሱን የሚገልጥበት ጊዜ ይመጣል፣ እርሱም እራሱን ለአይሁዶችና ደግሞ ለአህዛብ ከገለፀ በኋላ እራሱን ለአህዛብና ደግሞ ለአይሁዶች ይገልፃል፣ እንዲሁም የኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።