የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯፥፳፩። ከሉቃስ ፲፯፥፳–፳፩ ጋር አነጻፅሩ

የእግዚአብሔር መንግስት አስቀድማ መጥታለች።

፳፩ ደግሞም እንኋት በዚህ ወይም እንኋት በዚያ አይሉአትም፣ እነሆ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።

ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯፥፴፮–፵። ከሉቃስ ፲፯፥፴፯ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ስለኋለኛው ቀናት መሰብሰብ ለመግለጽ የንስርን ምሳሌ ተናገረ።

፴፮ መልሰውም ጌታ ሆይ፣ ወዴት ይወሰዱ? አሉት።

፴፯ እርሱም ሥጋ ወዳለበት፣ ወይም በሌላ ቃላቶች፣ የትም ቅዱሳን በተሰበሰቡበት፣ በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ፣ ወይም በዚያ የሚቀሩትም አብረው ይሰበሰባሉ አላቸው።

፴፰ ይህን የተናገረው የቅዱሳንን መሰብሰብ በሚመለከት ነው፤ እና መላእክቶች ወርደው የሚቀሩትን ስለመሰብሰባቸው ነው፤ አንዱን ከመኝታ፣ ሌላን ከወፍጮ፣ እና ሌላን ከሜዳ፣ የትም ከሚፈልግበት።

፴፱ በእውነትም ጻድቅ የሚኖርበት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ይኖራሉ።

፵ እና ምንም እርኩስ ነገር አይገኝበትም፤ ምድርም አሮጌ፣ እንዲሁም እንደ ልብስ፣ ሆና ብከላም ተጨምሮባታልና፣ ይህም ቢሆን ይህም ይጠፋል፣ እና የእግር መርገጫም፣ ከኀጥያት ጸድታ፣ በቅድስና ትቀራለች።