የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ጴጥሮስ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ጴጥሮስ ፫፥፫–፲፫።፪ ጴጥሮስ ፫፥፫–፲፫ ጋር አነጻፅሩ

በመጨረሻው ቀናት፣ ብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ይከዳሉ። ሲመጣም፣ ብዙ የፍጥር መዓቶች ይደርሳሉ። በጻድቅነት ከጸናን፣ አዲስ ምድር እንቀበላለን።

በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ።

እነርሱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመካድ፣ እና የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ሁሉም ነገሮች እንዳሉ መቀጠል አለባቸው፣ እናም ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና ይላሉ።

ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውኃ ተጋጥማ በውኃ መካከል ወጥታ እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤

እናም በእግዚአብሔር ቃል፣ በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤

አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።

የጌታ መምጣትን በሚመለከት ግን፣ እናንተ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ እና መምጣት ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እኛ ይታገሣል።

የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፣ እናም ምድር ደግሞም ትንቀጠቀጣለች ተራራዎችም ይቀልጣሉ፣ በታላቅ ድምጽም ያልፋሉ፣ ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይሞላል፣ ምድርም ትሞላለች፣ በእርስዋም ላይ የተደረገው እርኩስ ስራ ሁሉ ይቃጠላል።

፲፩ እነዚህ ሁሉ የሚደመሰሱ ከሆኑ፣ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል፣

፲፪ የሰማያት የተረከሱት ነገሮች ተቃጥለው፣ በሚቀልጡበት፣ ተራራዎች በትልቅ ትኵሳት በሚቀልጡበት፣ የጌታ መምጣት ቀን ስትጠብቁና ስትዘጋጁም?

፲፫ ነገር ግን፣ ከጸናን፣ እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን። ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንጠብቃለን።