የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ተሰሎንቄ ፪


ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ተሰሎንቄ ፪፥፪–፫፣ ፯–፱። ከ፪ ተሰሎንቄ ፪፥፪–፱ ጋር አነጻፅሩ

ሰይጣን መውደቅን ወይም ክህደትን ጌታ ከመመለሱ በፊት ያመጣል።

፪ ይህን ከእኛ በመንፈስም ይሁን በቃል እስካልተቀበላችሁ ድረስ፣ የክርስቶስ ቀን ደርሶአል ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ፣ በደብዳቤዎችም እንዳትደነግጡም።

፫ ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ይመጣል፣ እና የዓመፅ ሰው እርሱም እንደ ጥፋት ልጅ ይገለጣልና።

፯ የዓመፅ ሚሥጥር አሁን ይሠራልና፣ አሁንም ይህን የሚሰራው እርሱ ነው፣ እና ከመንገድ የሚወገድበት እስከሚሟላ ጊዜ ድረስ እንዲሰራም ክርስቶስ ፈቅዶለታል።

፰ በዚያም ጊዜ ጌታ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፣ በመመለሻው ብርሀን የሚሽረው ያ ዓመፀኛ ይገለጣል፤

፱ አዎን፣ ጌታ፣ እንዲሁም ኢየሱስ፣ በሰይጣን ሙሉ ሀይል፣ እና ምልክቶች፣ እናም በሀሰተኛ ድንቆችም አሠራር በኩል ክህደት እስከሚመጣ ድረስ መምጫው አይደርስም።