ምዕራፍ ፮
[ህዳር–ታህሳስ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
የአዳም ዘር የመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ—ጻድቅ ዝርያዎቹ ንስሐን ሰበኩ—እግዚአብሔር ለሔኖክ ራሱን ገለጠ—ሔኖክ ወንጌሉን ሰበከ—የደህንነት እቅድም ለአዳም ተገልጦ ነበር—ጥምቀትንና ክህነትን ተቀበለ።
፩ እናም ሀአዳም የእግዚአብሔርን ድምጽ አደመጠ፣ እና ልጆቹን ንስሐ እንዲገቡ ጠራቸው።
፪ እናም አዳም ሚስቱን እንደገና አወቃት፣ እናም እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች፣ እርሱም ስሙን ሀሴት ብሎ ጠራው። እና አዳምም የእግዚአብሔርን ስም አከበረ፤ እንዲህም አለ፥ ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ዘር ሰጠኝ።
፫ ለሴትም እግዚአብሔር እራሱን ገለጠ፣ እና ሴትም አላመጸም፣ ነገር ግን እንደ ወንድሙ አቤል አይነት ተቀባይነት ያለው ሀመስዋዕትን አቀረበ። ለእርሱም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ እና ስሙንም ሄኖስ አለው።
፬ ከዚያም እነዚህ ሰዎች የጌታን ስም ሀመጥራት ጀመሩ፣ እና ጌታም ባረካቸው።
፭ እናም በአዳም ቋንቋ የተጻፈበት ሀየመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚጠሩት ሁሉም በመንፈስ እንዲፅፉ ለለመነሳሳት ተሰጥቷቸዋልና።
፮ ንፁህና ያልተበላሸ ቋንቋ ስለነበራቸው፣ ልጆቻቸውም በእነርሱ መጻፍና ማንበብን ተምረዋል።
፯ አሁን ይህም በመጀመሪያ የነበረው ሀክህነት እስከ አለም መጨረሻም ይኖራል።
፰ አሁን ሀበመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሳም ይህን ትንቢት አዳም ተናገረ፣ እና የእግዚአብሔር ለልጆች ሐየትውልድ መዝገብም ተጠብቋል። እና ይህም የአዳም የትውልድ መሐረግ መፅሐፍ ነበር፣ እንዲህም ይላል፥ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረበት ቀን በራሱ በእግዚአብሔር አምሳል አበጀው፤
፱ በእርሱ ሰውነት ሀአምሳል ወንድና ሴት አድርጎ ለፈጠራቸው፣ እናም ባረካቸው፣ እናም በእግዚአብሔር ሐየእግሩ ማረፊያ በሆነው ምድር ላይ በተፈጠሩበትና ህያው መነፍሶች በሆኑበት ቀንም ሠስማቸውን አዳም ብሎ ጠራቸው።
፲ ሀአዳምም አንድ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፣ ልጅንም በአምሳያው እንደ ለመልኩ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።
፲፩ አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፣ እና ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
፲፪ አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፲፫ ሴትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፣ ሄኖስንም ወለደ፣ እናም በእድሜዎቹ በሙሉ ተነበየ፣ እናም ልጁን ሄኖስን ስለእግዚአብሔር መንገድ አስተማረው፤ ስለዚህ ሄኖስም ተነበየ።
፲፬ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፣ ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
፲፭ በምድር ገጽ ላይም የሰው ልጆች ቁጥር በጣም ብዙ ነበር። በእነዚህ ጊዜዎችም ሰይጣን በሰዎች መካከል ታላቅ ሀስልጣን ነበረው፣ በልባቸውም ቁጣን አነሳሳ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም ጦርነትቶችና ደም መፋሰስ ሆነ፤ እና ለበሚስጥር ስራዎች ምክንያት፣ ሀይል በመፈለግ፣ የሰው እጅም በግድያ በወንድሙ ላይ ነበር።
፲፮ ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፲፯ ሄኖስ መቶ ዘጠና አመት ኖረ፣ ሀቃይናንንም ወለደ። ሄኖስና የቀሩት የእግዚአብሔር ሕዝቦችም ሹሎን ከሚባለው አገር ወጡ፣ እና ቃይናን ብሎ በልጁ ስም በጠራበት በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ ኖሩ።
፲፰ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ፣ ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሄኖስ የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፲፱ ቃይናንም ሰባ ዓመት ኖረ፣ መላልኤልንም ወለደ፤ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ አርባ ዓመት ሆነ፣ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፳ መላልኤልም ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ፣ ያሬድንም ወለደ፤ መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፳፩ ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፣ ሀሔኖክንም ወለደ፤ ያሬድም ሔኖክን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ያሬድም ለሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በሙሉ አስተማረው።
፳፪ ይህም የእግዚአብሔር ሀልጅ የነበረውና እግዚአብሔር ራሱም ያነጋገረው የአዳም ልጆች ትውልድ መዝገብ ነው።
፳፫ እነዚህም የጽድቅ ሀሰባኪ ነበሩ፣ እና ተናገሩም ለተነበዩም፣ እና በሁሉም ስፍራ ያሉትን ሰዎች ሐንስሀ እንዲገቡ ጠሩአቸው፤ ለሰው ልጆችም መእምነትን አስተማሩ።
፳፬ እንዲህም ሆነ ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፳፭ ሔኖክም መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ፣ ሀማቱሳላንም ወለደ።
፳፮ እንዲህም ሆነ ሔኖክ በሕዝቦቹ መሀከል በሀገሩ ተጓዘ፤ እየተጓዘም ሳለ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ ወርዶ አረፈበት።
፳፯ እናም ከሰማይ እንዲህ የሚልን ድምጽ ሰማ፥ ልጄ ሔኖክ፣ ለእነዚህ ህዝቦች ተንብይና እንዲህ በላቸው—ንስሀ ግቡ፣ ጌታ እንዲህ ብሏልና፥ በዚህ ህዝብ እኔ ሀተቆጥቼአልሁ፣ እናም ሀያሉም ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ተቀጣጥላለች፤ ልቦቻቸው ጠጥረዋል፣ ለጆሮዎቻቸውም ደንቁረዋል፣ እናም አይኖቻቸውም ወደሩቅ ሐአያዩም፤
፳፰ ከፈጠርኳቸው ጊዜ ጀምሮም ብዙ ትውልዶችም ከእኔ ሀዞር ብለው ሄደዋል፣ እና እኔንም ክደዋል፣ እና በጭለማም የራሳቸውን ምክር ፈልገዋልና፤ ግድያንም በራሳቸው ፅያፍ ፈጥረዋል፣ እና ለአባታቸው አዳም የሰጠሁትን ትእዛዛትም አላከበሩም።
፳፱ ስለዚህ፣ ራሳቸው በሀሰት ምለዋል፣ እና ሀበመሀላቸውም ሞትን በራሳቸው ላይ አምጥተዋል፤ እና ንስሀ ባይገቡ ለሲኦልን አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
፴ እና ይህንንም አዋጅ ከምድር መጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ፣ ከመሰረቱ ጀምሮ፣ በራሴ አንደበትና በአገልጋዮቼ በአባቶቻችሁ አንደበት አውጄዋለሁ፣ እንዲሁም እስከ አለም መጨረሻ ጊዜ ድረስም ወደአለም ይላካል።
፴፩ ሔኖክ እነዚህን ቃላት ሲሰማም፣ በጌታ ፊት ወደመሬት ወደቀ፣ እና በጌታ ፊትም እንዲህ በማለት ተናገረ፥ ለምንድን ነው በፊትህ ሞገስን ያገኘሁት፣ እኔም ገና ልጅ ነኝ፣ እና ህዝቦች ሁሉ አይወዱኝም፤ አፌ ሀኰልታፋ ነውና፤ ስለዚህ እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ?
፴፪ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ ሂድና እንዳዘዝኩህ አድርግ፣ እናም ማንም አይጎዳህም። ሀአፍህን ክፈት፣ እናም ይሞላል፣ እኔም የምትናገረውን እሰጥሀለሁ፣ ሁሉም ስጋ ለባሽ በእጄ ላይ ነውና፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርጋለሁ።
፴፫ ለእነዚህ ሕዝብ እንዲህ በል፥ የፈጠራችሁን እግዚአብሔር አምላክን ታገለግሉ ዘንድ ዛሬ ሀምረጡ።
፴፬ እነሆ መንፈሴ በአንተ ላይ አርፏል፣ ስለዚህ ቃላትህን ሁሉ አጸድቃለሁ፤ ሀተራሮችም ከአንተ ፊት ይሸሻሉ፣ እናም ለወንዞችም ከሚሄዱበትም ይዞራሉ፤ አንተም ከእኔ ጋር ሁን፣ እና እኔም ከአንተ ጋር፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ሐተራመድ።
፴፭ እና ጌታ ለሔኖክ ተናገረ፣ እንዲህም አለ፥ አይኖችህን በሸክላው ቀባቸው፣ እጠባቸውም፣ እና ታያለህ። እርሱም ይህን አደረገ።
፴፮ እና እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ሀመንፈሶች አየ፤ እና ለበተፈጥሮ አይኖች የማይታዩትን ነገሮች ሁሉ ደግሞ አየ፤ እናም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ የሚል አባባል በምድር ውስጥ ነበር፥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሐባለራዕይ አስነስቷል።
፴፯ እናም እንዲህ ሆነ ሔኖክ በሃገሩ ውስጥ ከሕዝቦቹ መሀከል በመሄድ፣ በታላቅ ስፍራዎችና በተራሮች ላይ በመቆም፣ በደመቀ ድምፅ ስለ መጥፎ ሰራቸው በእነርሱ ላይ መሰከረ፤ እና ሁሉም ሰዎች በእርሱ ምክንያት ሀተቀይመው ነበር።
፴፰ እና ወደታላቅ ስፍራዎች በመሄድ፣ ለድንኳን ጠባቂዎች እንዲህ በማለት፣ እርሱን ለመስማት መጡ፥ ባለራእዩን ለማየት ወደዚያ ስፍራ ስንሄድ እዚህ ቆዩና ድንኳኖችን ጠብቁ፣ እየተነበየ ነውና፣ እና በሀገሩም የተለየ ነገር አለ፤ በመካከላችንም የዱር ሰው መጥቷል።
፴፱ እንዲህ ሆነ በሰሙትም ጊዜ ማንም ሰው እጆቻቸውን አላሳረፉበትም፤ የሰሙት ሁሉ ፍርሀት መጣባቸው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ይራመዳልና።
፵ እናም ማሂጃ የሚባል ሰውም ወደ እርሱ መጣና እንዲህ አለው፥ ማን እንደሆንክ እና ከየት እንደመጣህ በግልፅ ንገረን?
፵፩ እርሱም እንዲህ አላቸው፥ እኔ ከአባቶቼ ምድር፣ እስከዛሬ ድረስ ጻድቅ ከሆነው ሀገር ከቃይናን ነው የመጣሁት። አባቴም የእግዚአብሔርን መንገድ በሙሉ አስተምሮኛል።
፵፪ እንዲህም ሆነ፣ ከቃይናን ሀገርም በምስራቅ ባህር ስጓዝ፣ ራዕይ ታየኝ፤ እና አስተውሉ፣ እነሆ ሰማይን አየሁ፣ ጌታም አነጋግሮኝ፣ ትእዛዝም ሰጠኝ፤ ስለዚህ፣ ለዚህ ምክንያት፣ ትእዛዝን ለማክበርም እነዚህን ቃላት እናገራለሁ።
፵፫ ሔኖክም ንግግሩን ቀጥሎ እንዲህ አለ፥ እኔን ያናገረኝ ጌታም የሰማይ እግዚአብሔር ነው፣ የእኔ አምላክ፣ እና የእናንተም አምላክ ነው፣ እና እናንተም ወንድሞቼ ናችሁ፣ እና ለምን የራሳችሁን ሀምክር ትሰማላችሁ፣ እና የሰማይ እግዚአብሔርንስ ትክዳላችሁ?
፵፬ ሰማያትን ሰራ፤ ሀምድርም ለየእግሩ ማረፊያ ናት፤ የዚህም መሰረት የእርሱ ነው። እነሆ፣ እርሱም ሰርቶታል፣ የሰውንም ሰራዊት በምድርም ፊት አምጥቷል።
፵፭ ሞትም በአባቶቻችን ላይም መጥቷል፤ ይህም ቢሆን እናውቃቸዋለን፣ እና ልንክዳቸው አንችልም፣ እና ከሁሉም የመጀመሪያውን፣ እንዲሁም አዳምን፣ እናውቃለን።
፵፮ በእግዚአብሔር ጣት በተሰጠን ምሳሌ መሰረት ሀየመታሰቢያ መጻህፍትን በመካከላችን ፅፈናል፤ እና ይህም በራሳችን ቋንቋ የተሰጠን ነው።
፵፯ እና ሔኖክ የእግዚአብሔርን ቃላት ሲናገር፣ ሰዎቹም ተንቀጠቀጡ፣ እና በእርሱ ፊትም መቆም አልቻሉም።
፵፰ እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ያ አዳም ሀስለወደቀ፣ እኛም አለን፤ በእርሱም ውድቀትም ለሞት መጣ፤ እና በጉስቁልና በዋይታ ተካፋዮችም ሆነናል።
፵፱ እነሆ ሰይጣን በሰው ልጆች መካከል መጣ፣ እና እንዲያመልኩትም ሀፈተናቸው፤ እናም ሰዎችም ለስጋዊ፣ ሐስሜትዊና፣ ዲያብሎሳዊ ሆነዋል፣ እና ከእግዚአብሔር ፊትም መተከልክለዋል።
፶ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ሁሉም ሰዎች ንስሀ መግባት እንዳለባቸው አስታውቋቸዋል።
፶፩ ወደ አባታችን አዳምንም በድምጹ ጠርቶ እንዲህ ብሏል፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አለምንና ስጋ ከመልበሳቸው ሀበፊት ለሰዎችን የፈጠርኩኝ እኔ ነኝ።
፶፪ ደግሞም እንዲህ አለው፥ ወደእኔ ብትመለስ፣ እና ድምጼንም ብታደምጥ፣ እና ብታምን፣ እና ለተላለፍካቸውም ነገሮች ንስሀ ብትገባ፣ እና ለሰው ልጆች ሀደህንነትን ለማምጣት በሚችለው ከሰማይ በታች በሚሰጠው ለበጸጋና እውነት በተሞላበት አንድያ ልጄ ሐስም፣ እንዲሁም መበኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በውሀ ሠብትጠመቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ይሰጥሀል፣ እና ሁሉንም ነገሮችን በእርሱ ስም ጠይቅ፣ እና የምትጠይቀው ማንኛውም፣ ይህም ይሰጥሀል።
፶፫ አባታችን አዳምም ለጌታ ተናገረ፣ እና እንዲህም አለው፥ ለምንድን ነው ሰዎች ንስሀ መግባትና በውሀ መጠመቅ ያለባቸው? እና ጌታም ለአዳም እንዲህ አለው፥ ከዔድን ገነት ውስጥ ለተላለፍከው ሀይቅርታን ሰጥቼሀለሁኝ።
፶፬ በዚህም ምክንያትም ከህዝቦቹም መካከል ይህም አባባል መጣ፣ ሀየእግዚአብሔር ልጅ ለቀደመው ለኃጢአት ስርያትን አድርጎላቸዋል፣ በዚህም የወላጆች ኃጢአት ሐበልጆች ራስ ላይ አይመለስም፣ እነርሱም ከአለም መሰረት ጊዜ ጀምሮ ከኃጢአት ንጹህ ናቸውና።
፶፭ እና ጌታም ለአዳም እንዲህ ብሎ ተናገረ፥ ልጆች ሀበኃጢአት እስከተጸነሱ ድረስ፣ ሲያድጉም እንዲህ ነው፣ ኃጢአት በልባቸው ይጸነሳል፣ እና የመልካሙን ነገር ሽልማት ያውቁ ዘንድ፣ ለመራራውንም ይቀምሳሉ።
፶፮ መልካሙን ከክፉው ያውቁ ዘንድ ተሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ ለራሳቸው ሀሃላፊዎች ናቸው፣ እና ለአንተም ሌላ ህግና ትእዛዝ ሰጥቼሃለሁ።
፶፯ ስለዚህ በየትም ያሉ ሁሉም ሰዎች ሀንስሀ መግባት እንደሚገባቸው ልጆችህን አስተምራቸው፣ አለዚያም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ በምንም አይችሉም፣ ምንም ለእርኩስ ነገር በዚያ ወይም በእርሱ ፊት ሐመኖር አይችልምና፤ በአዳም ቋንቋ ስሙ መየቅድስና ሰው ነውና፣ እና የአንድያ ልጅ ስምም ሠየሰው ልጅ፣ በመካከለኛው ዘመን የሚመጣው የፅድቅ ረዳኛ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና።
፶፰ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች በነጻ ሀለልጆችህ እንድታስተምር እንዲህ በማለት ትእዛዝን እሰጥሀለሁ፤
፶፱ በመተላለፍ ምክንያት ውድቅት መጥቷል፣ ያም ውድቀት ሞትን አምጥቷል፣ እና በምድር በውሃ፣ በደምና፣ በፈጠርሁት ሀመንፈስ እንደተወለድክም ሁሉ፣ ለበአፈርም ህያው ነፍስ ሆንህ፣ እንዲሁም ወደ መንግስተ ሰማያት ሐበውሃ፣ በመንፈስ መበድጋሚ መወለድ አለብህ፣ በደምም እንዲሁም ከኃጢአት በሚያነጻህ በአንድያ ልጄ ደም መንጻት አለብህ፤ እና ከሁሉም ኃጢአት እንድትጸዳ፣ እና በዚህ አለም የዘለአለም ህይወት ሠቃላትን፣ እና በሚመጣው አለም የዘለአለም ህይወት፣ እንዲሁም የማይሞት ረክብርን፣ ሰትደሰትበት ዘንድ ነው፤
፷ ሀበውሀው ትእዛዝን ታከብራለህና፤ በመንፈሱም ለትጸድቃለህ፣ እናም ሐበደሙም መነጽተሀል፤
፷፩ ስለዚህ ይህም የሰማይ መዝገብ፤ ሀአጽናኝ፣ የማይሞተው ክብር ሰላም ነገሮች፤ የሁሉም ነገሮች እውነት፤ ለሁሉም ነገሮች ህይወትን የሚሰጥ፣ ሁሉንም ነገሮች እንዲኖሩ የሚያደርገው፤ ሁሉንም ነገሮች የሚያውቅ፣ እና በጥበብ፣ በርህራሄ፣ በእውነት፣ በፍትህ፣ እናም በፍርድ አማካይነት ሁሉም ሀይል ያለው በውስጥህ እንዲኖር ተሰጥቶሀል።
፷፪ አሁንም እነሆ፣ እልሀለሁ፥ ይህ በመካከለኛው ዘመን በሚመጣው ሀአንድያ ልጄ ደም አማካይነት የሚከናወነው የሰው ሁሉ ለየደህንነት እቅድ ነው።
፷፫ እና እነሆ፣ ሁሉም ነገሮች ተማሳሌት አሏቸው፣ እና መንፈሳዊውም ይሁን አለማዊ ነገሮች፣ ሁሉም ነገሮች የፈጠርኳቸውና የሰራኋቸው ስለእኔ ሀእንዲመሰክሩ ነው፤ በሰማይ የሚገኙም ነገሮች፣ እና በምድር ላይ የሚገኙት ነገሮች፣ እና በምድር ውስጥያሉት ነገሮች፣ እና ከምድር በታች ያሉት፣ ከታችም እና ከላይም፥ ሁሉም ነገሮች ስለእኔ ይመሰክራሉ።
፷፬ እንዲህም ሆነ፣ ጌታ ከአባታችን ከአዳም ጋር ሲናገር፣ አዳምም ወደ ጌታ ጮኸ፣ እና በጌታ ሀመንፈስም ተነጥቆ ተወሰደ፣ እና ወደ ለውሀ ውስጥም ተወሰደ፣ እና በውሀ ውስጥም ተኛ፣ ከእዚያም ወዲያው ከውሀው ወጣ።
፷፭ እንዲህም ተጠመቀ፣ እና የጌታ መንፈስ በእርሱ ላይ አረፈበት፣ እና እንዲህም በመንፈስ ሀተወለደ፣ እና በውስጥ ለሰውነቱም ህይወት ተሰጠው።
፷፮ እና ከሰማይ ድምጽ እንዲህ ሲል ሰማ፥ በእሳት፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ፣ ሀተጠምቀሃል። ይህም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለአለም የአብ፣ እና የወልድ ለመዝገብ ነው።
፷፯ አንተም ከዘለአለም እስከ ዘለአለም፣ ለቀናቱ የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ከሌለው ከእርሱ ሀስርዓትም ሆነሀል።
፷፰ እነሆ፣ አንተ በእኔ ሀአንድ ነህ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ፤ እና እንደዚህ ሁሉም የእኔ ለልጆች መሆን ይችላሉ፣ አሜን።