ምዕራፍ ፪
አብርሐም ከዑር ወጥቶ ወደ ከነዓን ሄደ—ሀራን ውስጥም ያህዌህ ተገለጠለት—የወንጌል በረከቶችም ሁሉ ለዘሮቹና በዘሩም በኩል ለሁሉም ቃል ተገብተዋል—ወደከነዓንና ወደ ግብፅ ሄደ።
፩ አሁን በዑር ውስጥ ጌታ አምላክ ረሀቡ በጣም ፅኑ እንዲሆን አደረገ፣ በዚህም ምክንያት ወንድሜ ሀሀራንም ሞተ፤ አባቴ ለታራን ግን በከለዳ ሃገር ዑር ውስጥ መኖር ቀጠለ።
፪ እና እንዲህ ሆነ እኔ አብርሐም ሀሦራን አገባሁ፣ እናም ወንድሜ ለናኮር የሃራን ሴት ልጅ ሚልካን አገባ።
፫ አሁን ጌታ እንዲህ ሀአለኝ፥ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
፬ ስለዚህ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ የከለዳውያን ሀዑር ምድር ትቼ ሄድኩኝ፤ እና የወንድሜን ልጅ ሎጥንና ሚስቱን እናም ሚስቴን ሦራን ይዤ ሄድኩኝ፤ እና ለአባቴም ሃራን ብለን ወደጠራነው ምድርም ተከተለኝ።
፭ ረሀቡም ቀነሰ፤ እናም ብዙ መንጋዎች በሀራን ስለነበሩ አባቴም በዚያ ቆየ፤ እና አባቴ ሀጣኦቶችን ወደማምለክ ተመለሰ፣ ስለዚህ በሀራን ውስጥ መኖር ቀጠለ።
፮ ነገር ግን እኔ አብርሐምና የወንድሜ ልጅ ሀሎጥ ወደ ጌታ ጸለይን፣ እና ጌታም ለእኔ ለተገልጦ እንዲህ አለኝ፥ ተነሳ፣ እና ሎጥን ከአንተ ጋር ውሰድ፤ አንተን ከሄራን ለማውጣት እና ለዘርህ፣ ድምጼን ሲያደምጡ፣ ለዘለአለም እንዲወስዱ ለምሰጠው እንግዳ ሐምድር ውስጥ መስሜን የምትሸከም አገልጋይ አደርግህ ዘንድ እንድትሄድ አላማ አለኝ።
፯ እኔ ጌታ አምላክ ነኝና፤ በሰማይም እኖራለሁ፤ ምድርም የእግሬ ሀማረፊያ ነች፤ እጄን በባህር ላይ እዘረጋለሁ፣ እና በድምጼም ይታዘዛል፤ ንፋሱን እሰራለሁ እና እሳትን ለሰረገላዬ አድርጌአለሁ፤ ለተራሮች—ከዚህ ሂዱ—እላለሁ እና እነሆ፣ በታላቅ አውሎንፋስ ወዲያውም ይወሰዳሉ።
፰ ስሜ ሀያህዌህ ነው፣ እና መጨረሻውን ከመጀመሪያው ለአውቀዋለሁ፤ ስለዚህ እጄም በአንተ ላይ ይሆናል።
፱ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፣ እና አብዝቼም ሀእባርክሀለሁ፣ እና ስምህንም ከህዝቦች መካከል ታላቅ አደርገዋለሁ፣ እና ከአንተ በኋላ ለሚመጡ ዘሮች በረከት ሆነህ፣ እጆቻቸው ይህን አገልግሎትና ለክህነትን ለሁሉም ህዝቦች ይዘው ይሄዳሉ፤
፲ እና በስምህ በኩልም እባርካቸዋለሁ፤ ይህን ሀወንጌል የተቀበሉት ሁሉ በአንተ ስም ይጠራሉ፣ እና እንደ አንተ ለዘር ይቆጠራሉ፣ እና እንደ ሐአባታቸው ተነስተው ይባርኩሀል፤
፲፩ የሚባርኩህንም ሀእባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ በአንተ (ይህም ማለት በክህነትህ በኩል) እናም ለበዘርህ (ይህም ማለት በክህነትህ)፣ እና ከአንተም በኋላ በዘርህ (ይህም ማለት የራስህ ዘር ወይም የሰውነትህ ፍሬዎች) በኩል ይህ ሐመብት ይቀጥላል፣ ሁሉም የምድር ቤተሰቦች በደህንነት በረከቶች፣ እንዲሁም የዘለአለም ህይወት በሆኑት የወንጌል በረከቶች ይባረካሉ ብዬ ቃል ኪዳን ሰጥቼሀለሁ።
፲፪ አሁን ጌታ ከእኔ ጋር መናገሩን ከጨረሰ በኋላና ፊቱንም ከእኔ ከወሰደም በኋላ፣ በልቤ እንዲህ አልኩ፥ አገልጋይህ በትኩረት ሀፈልጎህ ነበር፤ አሁን አገኘሁህ፤
፲፫ ከኤልከናኽ አማልክቶችም እኔን ሀለማዳን መላእክትህን ላክ፣ እና ድምፅህን ባደምጥ ለእኔ ጥቅም ይሆናል፣ ስለዚህ አሁን ባሪያህም ይነሳ እና በሰላም አሰናብተው።
፲፬ ስለዚህ እኔ አብርሐም ጌታ እንዳለኝ ተነስቼ ሄድኩ፣ ሎጥም ከእኔ ጋር፤ እና እኔ አብርሐምም ከካራን ስሄድ ሀስልሳ ሁለት አመቴ ነበር።
፲፭ እና በከላውዴዎ ሀበዑር ውስጥ እያለሁ ያገባኋት ለሦራን እና የወንድሜ ልጅ ሎጥን፣ እና የሰበሰብናቸውን ነገሮች፣ እና በካራን ውስጥ ሐያገኘናቸውን ነፍሳት ወሰድኩ፣ እና ወደ መከነዓንም ምድር ገባን፣ እና ስንጓዝም በድንኳን ውስጥ ኖርን፤
፲፮ ስለዚህ፣ ከካራን ተጉዘን በጀርሸን በኩል ወደ ከነዓን ምድር ስንመጣም፣ ዘለአለምዊውም ከለላችን ሀአለታችንና መድሀኒታችን ነበር።
፲፯ አሁን እኔ አብርሐም ሀመሰዊያ በጀርሸን ምድር ውስጥ ሰራሁ፣ እና ለጌታም መስዋዕትን አቀረብኩ፣ እና እንዳይሞቱም ከአባቴ ቤት ለረሀቡ ጋብ እንዲል ጸለይኩ።
፲፰ ከዚያም እስከ ሴኬም ድረስ ከጀርሸን ምድሪቱ ዘልቀን አልፈን ሄድን፤ ይህም በሞሬ ሜዳ ውስጥ የነበረ ነው፣ እና ሀበከነዓናውያን ድንበርም ደርሰን ነበር፣ እናም በባእድ አምላኪዎች ምድር ውስጥ ስለገባን፣ በሞሬ ሜዳ አካባቢም ለመስዋዕትን አቀረብኩ፣ ጌታንም በመንፈሳዊ ነገር ተግቼ ጠራሁት።
፲፱ እናም ጌታ ጸሎቴን ለመመለስ ተገለጠልኝ፣ እና እንዲህም አለኝ፥ ይህችን ሀምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።
፳ እና እኔ አብርሐም ለጌታ ከሰራሁት መሰዊያ ተነሳሁ፣ ሀበቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራም ሄድኩ፣ እና ቤቴልን በምዕራብ፣ ለጋይን በምስራቅ ሆኖ ድንኳኔን በዚያ ተከልኩ፤ እና በዚያም ለጌታ ሌላ መሰዊያን ሰራሁ፣ እና ደግሜም የጌታን ስም ሐጠራሁ።
፳፩ እና እኔ አብርሐም ወደ ደቡብ መጓዝን ቀጠልኩ፤ በዚያም ምድር ውስጥ ረሀብ ይበረታ ነበር፤ እና እኔ አብርሐም ረሀቡ ፅኑ ስለነበር፣ ወደ ግብፅ ለመሄድ፣ እና ወደዚያም ለመጓዝ ወሰንኩ።
፳፪ ግብፅ ለመግባት እየቀረብኩ ስመጣም፣ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ እነሆ፣ ሚስትህ ሀሦራ ለመመልከት መልከ መልካም ሴት ነች፤
፳፫ ስለዚህ እንዲህ ሆነ ግብጻውያን እርሷን በሚያዩበት ጊዜ ይህች ሚስቱ ናት ይላሉ፤ እና ይገድሉሀል፣ እርሷን ግን በህይወት ይተውአታል፤ ስለዚህ እንዲህ አድርግ።
፳፬ ለግብጻውያኑ እህትህ እንደሆነች ትንገራቸው፣ ነፍስህም ትድናለች።
፳፭ እንዲህም ሆነ እኔ አብርሐም ጌታ የነገረኝን ሁሉ ለሚስቴ ሦራ ነገርኳት—ለአንቺም ደህንነት፣ እና በአንቺም ምክንያት ነፍሴ ትድን ዘንድ፣ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ እንግዲህ እህቴ እንደሆንሽ እንድትነግሪያቸው እለምንሻለሁ።