የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪


ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪፥፳፪።ራዕይ ፪፥፳፪ ጋር አነጻፅሩ

ክፉዎች ወደገሀነም ይጣላሉ።

፳፪ እነሆ፣ በገሀነም ላይ እጥላታለሁ፣ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤

ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪፥፳፮–፳፯።ራዕይ ፪፥፳፮–፳፯ ጋር አነጻፅሩ

የክርስቶስ ትእዛዛትን በማክበር አለምን የሚያሸንፉ በሚመጣው አለም መንግስቶችን በእምነት፣ በእኩልነት፣ በፍትህ ይገዛሉ።

፳፮ ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ትእዛዛቴን ለጠበቀው፣ በብዙ መንግስትቶች ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥

፳፯ እርሱም በእግዚአብሔር ቃል ይገዛቸዋል፤ እናም እነርሱም በእጁ ውስጥ ጭቃወ እቃ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ይሆናሉ፤ እናም በእምነት፣ በእኩልነት፣ እና በፍትህ፣ እንዲሁም እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ ይገዛቸዋል።