የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፲፪


ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፲፪፥፩–፲፯።ራዕይ ፲፪፥፩–፲፯ ጋር አነጻፅሩ

ዮሐንስ የሴቷን፣ የልጅ፣ የብረት በትርን፣ የዘንዶውን፣ እና የሚካኤልን ምሳሌዎች ገለጻቸው። በሰማይ የተጀመረው ጦርነት በምድር ቀጥሏል። በጆ.ስ.ት. ውስጥ የአንቀጾች ተከታታይነት እንዴት እንደተቀየረ ተመልከቱ።

በምድር ላይ ነገሮች እንዳሉት የሚመሳሰል ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።

እርስዋም ፀንሳ ነበር ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።

በብረት በትር ሁሉንም ህዝቦች የሚገዛ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ ልጇም ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ዙፋኑ ተወሰደ።

ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ። ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ዘንድ በፊቷ ቆመ።

ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ አመታት በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ከሚካኤል ጋር ተዋጋ፤

ዘንዶውም ሚካኤልን፣ ወይም ሕጻኑን፣ ወይም የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሆነችውን፣ ከስቃዮዋ የዳነችውን፣ እና የእኛ እግዚአብሔርንና የክርስቶስን መንግስት ያመጣችውን ሴት አላሸነፈም።

ከዚያም ወዲያ ለተጣለው፣ ዲያብሎስ እና ደግሞም ሰይጣን ለሚባለው የድሮው እባብ፣ አለምን ሁሉ ላታለለው ለታላቁ ዘንዶ በሰማይ ስፍራ አልተገኘለትም፤ ወደምድርም ተጣለ፤ መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል ሰማሁ፣ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን መጣ።

ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

፲፩ እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም አልወደዱምና፣ ምስክራቸውን ግን እስከ ሞት ድረስ ጠበቁ። ስለዚህ፣ ሰማያትና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፣ ደስ ይበላችሁ።

፲፪ ከእነዚህ ነገሮች በኋላ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፣ ለምድር ለሚኖሩትና፣ አዎን፣ እናም በባሕር ደሴቶች ለሚያድሩት ወዮላቸው! ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።

፲፫ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ በማየቱ ምክንያት፣ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳትና።

፲፬ ስለዚህ፣ ከእባቡም ፊት ተሰድዳ አንድ ዘመን፣ ዘመናትም፣ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።

፲፭ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተኋላዋ አፈሰሰ።

፲፮ ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፣ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።

፲፯ ስለዚህ፣ ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ።