የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፩


ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፩፥፩–፬። ከራዕይ ፩፥፩–፰ ጋር አነጻፅሩ

ሐዋርያው ዮሐንስ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ትንቢቶች ተቀበለ። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመልአክ ተጎበኘ።

፩ ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ፣ በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ ያመለከተው፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠው የእግዚአብሔር አገልጋይ የዮሐንስ ራዕይ፣

፪ እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ የመሰከረው።

፫ የጌታ መምጫ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነቡት የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና የሚረዳቸው፣ በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።

፬ አሁን ይህ ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ ቤተክርስቲያናት አገልጋዮች የሰጠው ምስክር ነው። ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፣ የሰባት ቤተክርስቲያናት ሰባት አገልጋሎች ለሆኑት እንደመሰክሩ በዙፋኑም ፊት መላእክቱን ከላከው፣ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

፭ ስለዚህ፣ እኔ፣ ዮሐንስ፣ ታማኝ ምስክር፣ ከመላእክ እና ከሙታንም በኵር እና የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነገሮች እመሰክራለሁ።

፮ ለወደደን፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፣ ለእግዚአብሔር ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፣ ክብር ይሁን። ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

፯ እነሆ፥ በደመና በመንግስት ውስጥ ካሉት አስር ሺህ ቅዱሳን ጋር፣ በአባቱ ክብር ተለብሶ ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ ያዩታል፤ እና የወጉትም፣ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። እንዲሁም ይሁን፣ አሜን።

፰ እንዲህም ብሏልና፣ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ።