የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱። ከማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱ ጋር አነጻፅሩ፤ በሉቃስ ፬፥፪፣ ፭–፲፩ም እንደዚህ አይነት ቅያሬዎች ነበሩ

ኢየሱስ የተመራው በመንፈስ እንጂ በሰይጣን አይደለም።

፩ ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ይሆን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረበዳ ወሰደው።

፭ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅድስት ከተማ ተወሰደ፣ እና መንፈስ እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቆመው።

፮ ከእዚያም በኋላ ዲያብሎስ ወደእርሱ መጣ እና እንዲህ አለው፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፣ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።

፰ ደግሞም፣ ኢየሱስ በመንፈስ ውስጥ ነበር፣ እና ይህም ወደ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳየው።

፱ እና ዲያብሎስም ወደ እርሱ እንደገና መጣ፣ እና አለው፣ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፲፩። ከማቴዎስ ፬፥፲፩ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስን ለማገልገል መላእክት ላከ።

፲፩ አሁንም ኢየሱስ ዮሐንስ ወደ እስር ቤት እንደተጣለ አወቀ፣ እና እርሱም መላእክትን ላከ፣ እና እነሆ፣ እነርሱም መጡና አገለገሉት።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፲፰። ከማቴዎስ ፬፥፲፱ ጋር አነጻፅሩ

ብሉይ ኪዳን ነብያት ስለኢየሱስ ይናገራሉ።

፲፰ እርሱም በነብያት የተጻፈለት እኔ ነኝ፤ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፳፪። ከማቴዎስ ፬፥፳፫ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ በስሙ ካመኑት መካከል ህዝቦችን ፈወሰ።

፳፪ ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በስሙ በሚያምኑት ሕዝብም መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።