የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፬–፮። ከማቴዎስ ፪፥፬–፮ ጋር አነጻፅሩ

ነቢያት ቤተ ልሔም መሲህ የሚወለድበት ቦታ እንደሆነ አቅድመው ተናገሩ።

፬ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ በማለት ጠየቃቸው፥ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ በነቢያት የተጻፈበት ቦታ የት ነው? ምክንያቱም ታላቅ ፍርሀት ነበረው፣ ግን በነቢያት አያምንም ነበር።

፭ እነርሱም በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና፣ በይሁዳ ቤተ ልሔም ይወለዳል፣ እንደዚህ ብለዋልና አሉት፣

፮ የጌታ ቃል ወደ እኛ እንዲህ በማለት መጣ፣ እናም አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ በአንቺ ውስጥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ ታናሽ ያልሆነ መስፍን ይወለዳል፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚያድን መስፍን ከአንቺ ይወጣልና።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፳፬–፳፮። ከማቴዎስ ፪፥፳፫ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ አደገ እናም አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ጌታን ጠበቀ።

፳፬ እና እንዲህ ሆነ ኢየሱስ ከወንድሞቹ ጋር አደገ፣ እና ጠነከረ፣ እና የአገልግሎቱ ጊዜ እስከሚመጣም ጌታን ጠበቀ።

፳፭ እና ከአባቱ በታች አገለገለ፣ እና እንደ ሌሎች ሰዎች አልተናገረም፣ ወይም ሊማርም አልቻለም፤ ምንም ሰው እንዲያስተምረው አላስፈለገውምና።

፳፮ እና ከብዙ አመቶች በኋላ፣ የአገልግሎቱ ሰዓት ቀረበ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፴፬–፴፮። ከማቴዎስ ፫፥፰–፱ ጋር አነጻፅሩ

የመጥምቁ ዮሐንስ መልእክትን የማይቀበሉ ክርስቶስን አይቀበሉም። እግዚአብሔር ከእስራኤል ያልሆኑን የቃል ኪዳን ህዝቦች ለማድረግ ይችላል።

፴፬ እግዚአብሔር ራሱ የላከውን ስብከት ለምንድን ነው የማትቀበሉት? ይህብ በልባችሁ ካልተቀበላችሁ፣ እኔን አትቀበሉም፤ እናም እኔን ካልተቀበላችሁ፣ እኔ እንድመሰክርበት የተላኩትን አትቀበሉም፤ እናም ለኃጢያቶቻችሁ ምንም መሸፈኛ የላችሁም።

፴፭ እንግዲህ፣ ንስሀ ግቡ፣ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤

፴፮ በልባችሁም የአብርሐም ልጆች ነን እና ወደ አባታችን አብርሐም ፍሬ እናምጣ በማለት አታስቡ፤ እላችኋለሁና፣ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፴፰–፵። ከማቴዎስ ፫፥፲፩–፲፪ ጋር አነጻፅሩ

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ለመጥመቅ ሀይል እንዳለው መስክሯል።

፴፰ እኔስ ንስሐ ከገባችሁ በኋላ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ እናም ስለእርሱ ምስክር የምሰጠው፣ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ፣ (ወይም ቦታውን ለሞምላት የማልችለው) ሲመጣ፣ እንዳልኩት፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አጠምቃችኋለሁ፣ እርሱ ሲመጣም በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል።

፴፱ እና የምመሰክርበት፣ መንሹም በእጁ የሆነው እርሱ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት በጊዜው ሙላት ያቃጥለዋል።

፵ በዚህም ዮሐንስ በዮርዳኖች ወንዝ በመስበክ እና በመጥመቅ መጣ፤ ከእርሱም በኋላ የሚመጣው መንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ለመጥመቅ ሀይል እንዳለው እየመሰከረም።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፵፫–፵፮። ከማቴዎስ ፫፥፲፭–፲፯ ጋር አነጻፅሩ

ዮሐንስ ኢየሱስን በማጥለቅ አጠመቀ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ሲወርድ አየ፣ እናም የአብን ድምፅ ሰማ።

፵፫ እና ኢየሱስም መልሶ፣ በአንተ እንድጠመቅ ፍቀድልኝ፣ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።

፵፬ እና ዮሐንስ ወደ ውሀው ገባ እና አጠመቀው።

፵፭ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ ዮሐንስም አየ፣ እና አስተዋለ፣ ሰማያት ተከፍተውለት ነበር፣ እና የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በኢየሱስ ላይም ሲመጣ አየ፤

፵፮ አስተዋለም፣ ከሰማይም ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፣ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው። አድምጠው።