የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፫


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፫፥፴፱–፵፬።ማቴዎስ ፲፫፥፴፱–፵፪ ጋር አነጻፅሩ፤ ደግሞም ት. እና ቃ. ፹፮፥፩–፯ ተመልከቱ

ከአለም መጨረሻ (ከክፉዎች መደምሰስ) በፊት፣ ከሰማይ የተላኩ መልእክተኞች ጻድቅን ከክፉዎች መካከል ይሰበስባሉ።

፴፱ መከሩም የዓለም መጨረሻ፣ ወይም የክፉዎች መደምሰስ ነው።

አጫጆችም መላእክት፣ ወይም የሰማይ መልእክተኞች ናቸው።

፵፩ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ፣ ወይም በክፉዎች መደምሰስ እንዲሁ ይሆናል።

፵፪ ምክንያቱም የሰው ልጅ ከመምጣጡ ከዚያ ቀን በፊት፣ መላእክቱን እና የሰማይ መልእክተኞቹን ይልካል።

፵፫ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፣ በክፉዎች መካከልም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨትም ይሆናል።

፵፬ ምክንያቱም አለም በአቶነ እሳት ትነዳለችና።