ምዕራፍ ፲
የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይመጣል—ለታማኞች የመንፈስ ስጦታዎች ይሰጣቸዋል—መንፈሳዊው ስጦታዎች ዘወትር እምነትን ይከተላል—የሞሮኒ ቃላት ከምድር ይናገራሉ—ወደ ክርስቶስ ኑ፤ በእርሱም ፍፁማን ሁኑ፣ እናም ነፍሳችሁን አንፁ። ፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ አሁን እኔ ሞሮኒ፣ መልካም የመሰለኝን በመጠኑ እፅፋለሁ፤ ለወንድሞቼ ሀለላማናውያንም እፅፋለሁ፤ እናም ስለክርስቶስ መምጣት ምልክት ከተሰጠ አራት መቶ ሃያ ዓመት ማለፉን እንዲያውቁ እፈልጋለሁ።
፪ እናም እናንተን በጥብቅ በመምከር ጥቂት ከተናገርኳችሁ በኋላ እነዚህን መዛግብት ሀአትማቸዋለሁ።
፫ እነሆ፣ እነዚህን ነገሮች በምታነቡበት ጊዜ፣ ይህን እንድታነቡ በእግዚአብሔር ጥበብ ከሆነ፣ ጌታም ለሰው ልጆች ከአዳም መፈጠር ጀምሮ እነዚህን ነገሮች እስከምትቀበሉአቸው ጊዜ ድረስ ምን ያህል መሃሪ እንደነበረ እንድታስታውሱ በጥብቅ እመክራችኋለሁ፣ እናም ሀበልባችሁ ይህን ለአሰላስሉ።
፬ እናም እነዚህንም ነገሮች በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እነዚህ ነገሮች ሀሀሰት እንደሆኑ ዘለዓለማዊ አብ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም ለእንድትጠይቁት አጥብቄ እመክራችኋለሁ፤ እናም ሐበቅን ልባችሁ፤ መከእውነተኛ ፍላጎት፣ በክርስቶስ ሠአምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ረእውነቱን ሰይገልፅላችኋል።
፭ እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሁሉንም ነገር ሀእውነታ ለታውቁታላችሁ።
፮ እናም መልካም የሆነ ማንኛውም ነገር ጻድቅ እና እውነተኛ ነው፤ ስለሆነም፣ መልካም የሆነ ማንም ክርስቶስን አይክድም፤ ነገር ግን እርሱ መሆኑን ያረጋግጣል።
፯ እናም እርሱ መሆኑንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታውቃላችሁ፤ ስለሆነም፣ የእግዚአብሔርን ኃይል እንዳትክዱ በጥብቅ እመክራችኋለሁ፤ ምክንያቱም እርሱ፣ በሰው ልጆች እምነት ሀመሰረት፣ በኃይሉ ዛሬም እንዲሁም ነገም፣ እናም እስከዘለዓለም በአንድ አይነት ይሰራልና።
፰ እናም በድጋሚ ወንድሞቼ፣ የእግዚአብሔር ሀስጦታዎች እንዳትክዱአቸው አጥብቄ እመክራችኋለሁ፣ ብዙ ናቸውና፤ እና እነርሱም የሚመጡት ከአንድ እግዚአብሔር ነው። እናም እነዚህ ስጦታዎች የሚገለጡበት ለየተለያዩ መንገዶች አሉ፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ የሚያደርገው እግዚአብሔር አንድ ነው፤ እናም ለሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መገለጥ ለጥቅሙ ይሰጠዋል።
፱ እነሆም፣ ለአንዱ የጥበብን ቃል ሀያስተምር ዘንድ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ለይሰጠዋል።
፲ እናም ለሌላው፣ ለእርሱም በዚያው መንፈስ የእውቀትን ቃል ያስተምር ዘንድ ይሰጠዋል።
፲፩ እናም ለሌላው እጅግ ታላቅ ሀዕምነት፤ ለሌላውም በዚያው መንፈስ ለየመፈወስ ስጦታ ይሰጠዋል፤
፲፪ እናም በድጋሚ፣ ለሌላው፣ ታላላቅ ሀተአምራትን ያደርግ ዘንድ ይሰጠዋል፤
፲፫ እናም በድጋሚ፣ ለሌላው ስለሁሉም ነገሮች ትንቢት እንዲናገር ይሰጠዋል፤
፲፬ እናም በድጋሚ፣ ለሌላው፣ መላዕክትን የማየት እናም የመንፈስ አገልጋይነት ይሰጠዋል፤
፲፭ እናም በድጋሚ፣ ለሌላው ሁሉንም ዓይነት ልሳን ይሰጠዋል፤
፲፮ እናም በድጋሚ፣ ለሌላው፣ ሀቋንቋዎችን እናም የተለያየ ዓይነት ልሳን የተነገሩትን መተርጎም ይሰጠዋል።
፲፯ እናም እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች የሚመጡት በክርስቶስ መንፈስ አማካኝነት ነው፤ እናም እነርሱም ለእያንዳንዱ ሰው ለብቻው እያካፈለ እንደፈቃዱ ይመጣሉ።
፲፰ እናም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ መልካም ስጦታ ሀሁሉ ከክርስቶስ እንደሚመጣ እንድታስታውሱ አጥብቄ እመክራችኋለሁ።
፲፱ እናም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እርሱ ዛሬም እናም ነገም እናም ለዘለዓለም ሀአንድ አይነት እንደሆነ፣ እናም የተናገርኳቸው መንፈሳዊ የሆኑት እነዚህ ስጦታዎች በሙሉ ምድር እስካለች የሰው ልጆች ለእምነት ካላጡ በስተቀር ፈፅሞ መኖራቸውን እንደማያቆሙ እንድታስታውሱ አጥብቄ እመክራችኋለሁ።
፳ ስለሆነም፣ እምነት ሊኖር ይገባል፤ እናም ሀእምነት ካለ ተስፋም ደግሞ ሊኖር ይገባል፤ እናም ተስፋም ደግሞ ካለ ልግስና መኖር አለበት።
፳፩ እናም እናንተ ሀልግስና ከሌላችሁ በእግዚአብሔር መንግስት በምንም መንገድ ልትድኑ አይቻላችሁም፤ ወይም እምነት ከሌላችሁ በእግዚአብሔር መንግስት ለመዳን አትችሉም፤ ወይም ተስፋም ከሌላችሁ ለመዳን አይቻላችሁም።
፳፪ እናም ተስፋ ከሌላችሁ በተስፋ መቁረጥ ላይም መሆን አለባችሁ፣ እናም ተስፋ መቁረጥም የሚመጣው በክፋት ነው።
፳፫ እናም ክርስቶስ ለአባቶቻችን በእውነት እንዲህ ሲል ተናግሯቸዋል፥ እናንተም ሀእምነት ካላችሁ ለእኔ አስፈላጊ የሆነውን ለማድረግ ይቻላችኋል።
፳፬ እናም አሁን እስከአለም ጫፍ ላሉት ሁሉ እንዲህ ስል እናገራለሁ—የእግዚአብሔር ኃይልና ስጦታ በእናንተ መካከል መሆኑን የሚያቆምበት ቀን ከመጣ፣ ይህም የሚሆነው ሀእምነት በማጣት ለምክንያት ነው።
፳፭ እናም እንዲህ ከሆነ ለሰው ልጆች ወዮላቸው፤ ከእናንተ መካከል አንድም እንኳን ቢሆን መልካም የሚሰራ ሀምንም የለምና። ከመካከላችሁ መልካምን የሚያደርግ አንድ እንኳን ቢኖር፣ እርሱም በእግዚአብሔር ኃይልና ስጦታ ይሰራል።
፳፮ እናም እነዚህን ነገሮች ለሚያስወግዱት እናም ለሚሞቱ ወዮላቸው፣ ምክንያቱም ሀከነኃጢአታቸው ለይሞታሉ እናም በእግዚአብሔር መንግስት አይድኑምና፤ እናም እኔም የተናገርኩት በክርስቶስ ቃል መሰረት ነው፤ እናም ሀሰትን አልተናገርኩም።
፳፯ እናም እነዚህን ነገሮች እንድታስታውሱ አጥብቄ እመክራችኋለሁ፤ እኔ ሀሰት እንዳልተናገርኩ የምታውቁበት ቀን በፍጥነት ይመጣል፣ በእግዚአብሔር ፍርድ ወንበርም ታዩኛላችሁና፤ እናም ጌታ አምላክ እንዲህ ሲል ይናገራችኋል፥ ከሙታን ሀእንደሚጮህ፣ አዎን፣ አንድ ሰው ለከመሬት እንደሚናገር በዚህ ሰው የተፃፉትን ሐቃላት ለእናንተ አላወጅኩላችሁምን?
፳፰ ትንቢቶች ይፈፀሙ ዘንድ እነዚህን ነገሮች ለእናንተ አውጄአለሁ። እናም እነሆ፣ እነርሱም ከዘለዓለማዊው አምላክ አንደበት ይወጣሉ፤ እናም ቃሉም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሀያፏጫል።
፳፱ እናም እግዚአብሔርም የፃፍኩት እውነት እንደሆነ ያሳያችኋል።
፴ እናም በድጋሚ ወደ ክርስቶስ ሀእንድትመጡ፣ እናም እያንዳንዱን መልካሙን ስጦታ እንድትይዙ፣ እናም ክፉውን ስጦታ ወይም እርኩስን ነገር ለእንዳትነኩ አጥብቄ እመክራችኋለሁ።
፴፩ እናም እስራኤል ሆይ ሀንቂ ከመሬት ተነሽ፤ አዎን፣ እናም አቤቱ ለየፅዮን ሴት ልጅ፣ የሚያምረውን መጎናፀፊያሽን ልበሺ፤ እናም ከዚህም በኋላ ሐእንዳትቀላቀሊ፣ የዘለዓለማዊ አባት ለአንቺ፣ አቤቱ የእስራኤል ቤት፣ የገባው ቃል ኪዳን ይሟላም ዘንድ መካስማዎችሽን ሠአጥብቂ እናም ወሰንሽንም ለዘለዓለም አስፊ፤ ከእንግዲህም አታፍሪም።
፴፪ አዎን፣ ወደ ክርስቶስ ሀኑ፣ እናም በእርሱም ለፍፁማን ሁኑ፣ እናም ኃጢአተኝነትን በሙሉ ለእራሳችሁ ካዱ፤ እናም ለራሳችሁ ኃጢአተኝነትን በሙሉ ከካዳችሁ፣ እናም በሙሉ ኃይላችሁ፣አዕምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እግዚአብሔርን ሐከወደዳችሁ፣ ፀጋው ለእናንተ ይበቃችኋል፣ በፀጋውም በክርስቶስ ፍፁም ትሆናላችሁ፤ እናም በእግዚአብሔር መፀጋ በክርስቶስ ፍፁም ከሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርን ኃይል በምንም መልኩ አትክዱትም።
፴፫ እናም በድጋሚ፣ በእግዚአብሔር ፀጋ በክርስቶስ ፍፁማን ከሆናችሁ፣ እናም ኃይሉን ካልካዳችሁ፣ በእግዚአብሔር ፀጋ፣ ለኃጢአታችሁ ሀስርየት አብ በገባው ቃል ኪዳን ውስጥ ባለው በክርስቶስ ለደም መፍሰስ ያለ እንከን ሐቅዱስ ትሆኑ ዘንድ በክርስቶስ መትቀደሳላችሁ።
፴፬ እናም አሁን ሁላችሁንም እሰናበታችኋለሁ። ሀመንፈስና ስጋዬም በአንድነት ለእስኪገናኝ፣ እናም ለህያዋን እና ለሙታን ዘለዓለማዊ ሐዳኛ በሆነው በታላቁ መያህዌህ ሠአስደሳቹ የፍርድ ወንበር ፊት እናንተን ለመገናኘት ድል አድርጌ ወደ ረሰማይ እስከምመጣ ድረስ፣ በቅርብ ወደ እግዚአብሔር ሰገነት ሸለማረፍ እሄዳለሁ። አሜን።
ተፈፀመ