የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፬


ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፬፥፩–፯።መዝሙር ፲፬፥፩–፯ ጋር አነጻፅሩ

መዝሙረኛው በመጨረሻዎቹ ቀናት እውነቶች እንደሚጠፉ ተመለከተ እናም የፅዮን በዳግም መመስረትን በጉጉት ጠበቀ።

ሰነፍ በልቡ አምላክን ያየ ማንም ሰው የለም ይላል። ለእኛ እራሱን ስለማያሳይ፣ አምላክ የለም። እነሆ፣ የረከሱ ናቸው፤ የሚያስጸይፍ ስራዎች ሰርተዋል፣ እና ማንኛቸውም በጎ ነገርን አይሰሩም።

እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለክቷልና፣ እና በድምጹም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔር የሚገባቸው ማንኛቸውም እንዳሉ ከሰዎች ልጆች መካከል ፈልጉ። እና እርሱም አፉን ወደጌታ ከፈተ፣ እናም አለ፣ እነሆ፣ ይህን የሚሉ ሁሉ የአንተ ናቸው።

ጌታም መለሰ፣ እና አለ፣ ሁሉ ዐመፁ፣ በአንድነትም የረከሱ ናቸው፣ በጎ ነገርን የሚሠራ እንደሌለም ታያለህ፤ አንድም ስንኳ የለም።

ለአስተማሪ ያላቸው ሁሉ የርኩስ ሰራተኞች ናቸው፣ እና በውስጣቸውም ምንም እውቀት የለም። እነርሱም ህዝቦቼን የሚበሉት ናቸው። እንጀራን ይበላሉ እና ጌታንም አይጠሩትም።

በታላቅ ፍርሀት ውስጥ ናቸው፣ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልዶች መካከል ይኖራልና። እርሱም የደሀዎች አማካሪ ነው፣ ምክንያቱም በክፉዎች አፍረዋል፣ እና ለመሸሸጊያቸውም ወደ ጌታ ይሸሻሉ።

በደሀ ምክር ያፈሩ ናቸው ምክንያቱም ጌታ መሸሸጊያው ነውና።

ኦ ፅዮን፣ የእስራኤል መድሀኒት፣ ከሰማይ ብትመሰረት ኖሮ። አቤቱ ጌታ፣ ፅዮንን መቼ ትመሰርታለህ? ጌታ ህዝቡን ከባርነት መልሶ ሲያመጣ፣ ያዕቆብ ይደሰታል፣ እስራኤልም ደስተኛ ትሆናለች።