Scripture Stories
እስማኤል እና ቤተሰቡ


“እስማኤል እና ቤተሰቡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

1 ኔፊ 7

እስማኤል እና ቤተሰቡ

ወደ ቃል ኪዳን ምድር እየተደረገ ያለውን ጉዞ መቀላቀል

ምስል
በጀንበር ስትጠልቅ ኔፊ እና ወንድሞቹ በወንዝ ዳር እየተጓዙ

የሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ በምድረበዳ ውስጥ ብቻቸውን ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን፣ ጌታ ሌሂ ልጆቹን ላማንን፣ ልሙኤልን፣ ሳምን እና ኔፊን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲልክ ነገረው። እስማኤልንና ቤተሰቡ ከእነርሱ ጋር ይቀላቀሉ ዘንድ እንዲጠይቋቸው ተልከው ነበር። በጋራ ቤተሰቦቻቸው በቃል ኪዳን ምድር ልጆችን ማሳደግ ይችላሉ።

1 ኔፊ 7፥1–3

ምስል
ኔፊ ከእስማኤል ቤተሰብ ጋር ሲነጋገር

እስማኤል እና ቤተሰቡ ጌታን መከተል ፈለጉ። ጌታ ከሌሂ እና ሳርያ ቤተሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ እንደሚፈልግ አመኑ። ኢየሩሳሌምን ለመልቀቅ እና ሌሂን በምድረበዳ ውስጥ ለመገናኘት መረጡ።

1 ኔፊ 7፥4–5

ምስል
ላማን እና ልሙኤል ሲነጋገሩ

በመንገዳቸው ላይ፣ አንዳንድ ሰዎች ታዛዥ ለመሆን አልፈለጉም። ወደ ቤታቸው ለመመለስ ፈለጉ። በጌታ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ኔፊ ጠየቃቸው።

1 ኔፊ 7፥6–13

ምስል
ኔፊ በዛፍ ላይ ታስሮ

እምነት ካላቸው ጌታ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደሚችል ኔፊ ነገራቸው። ነገር ግን ላማን እና ልሙኤል ተናደዱ። ኔፊን አስረው በምድረበዳ ሊተውት ፈለጉ።

1 ኔፊ 7፥12፣ 16

ምስል
የእስማኤል ሴት ልጅ ኔፊን ስትከላከል

ኔፊ እርዳታ ለማግኘት ጸለየ። ገመዱ ተፈታ፣ እና ኔፊ ተነስቶ ቆመ። ነገር ግን ላማን እና ልሙኤል አሁንም ሊጎዱት ፈለጉ። ከእስማኤል ሴት ልጆች አንዷ ኔፊን ተከላከለችው። በተጨማሪም እናቷ እና ከወንድሞቿ አንዱ እርሱን ተከላከሉት። ላማን እና ልሙኤል እነርሱን ያሉትን ሰሙ እንዲሁም ኔፊን ለመጉዳት መሞከራቸውን አቆሙ።

1 ኔፊ 7፥17–19

ምስል
ላማን እና ልሙኤል በኔፊ ፊት ተንበርክከው

ላማን እና ልሙኤል ስላደረጉት ነገር አዘኑ። ኔፊን ይቅር እንዲላቸው ጠየቁት። ኔፊ ወንድሞቹን ይቅር አለ። ከዚያም ላማን እና ልሙኤል ጸለዩ እና ጌታ ይቅር እንዲላቸው ጠየቁት።

1 ኔፊ 7፥20–21

ምስል
ሌሂ እና እስማኤል ቤተሰቦቻቸውን እየተመለከቱ

ሁሉም ጉዟቸውን ቀጥለው ወደ ሌሂ እና የሳርያ ድንኳን ደረሱ። በመጨረሻም ሁለቱ ቤተሰቦች አብረው ነበሩ። እግዚአብሔርን አመሰገኑት እንዲሁም አመለኩት።

1 ኔፊ 7፥21–22