በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
አቢሽ


“አቢሽ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 17–19

አቢሽ

ህዝቦቿ በኢየሱስ እንዲያምኑ እየረዳች

አቢሽ በመንደር ውስጥ እየተራመደች

አቢሽ ላማናዊት ለነበረች ንግስት ትሰራ ነበር። አቢሽ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአባቷ ራእይ ተማረች። ለብዙ አመታት በኢየሱስ ታምን እና እርሱን ለመከተል ትፈልግ ነበር። ነገር ግን ለሌሎች ላማናውያን ገና አልነገረቻቸውም ነበር።

አልማ 19፥16–17

አቢሽ ንግሥቲቱን፣ ንጉሡን እና አሞንን እየተመለከተች

አንድ ቀን፣ ላማናውያንን ስለ ኢየሱስ እና ስለ እግዚአብሔር ለማስተማር አሞን የሚባል ኔፋዊ ወደ መንግስቱ መጣ። ንግስቲቱ እና ንጉሱ አሞን ያስተማረውን አመኑ። ንግስቲቱ እና ንጉሱ ኢየሱስ ወደ ምድር እንደሚመጣ እና በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ስርየትን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ አወቁ።

አልማ 17፥12–1318፥33–36፣ 39–4019፥9፣ 13

አቢሽ ሁሉም ሰው መሬት ላይ ወድቆ እያየች

ንግስቲቱ እና ንጉሱ መንፈስ ቅዱስ ተሰምቷቸው በጣም ደስ ስላላቸው በመሬት ላይ ወደቁ። አሞን እና አገልጋዮቹም ወደቁ። ቆማ የነበረችው አቢሽ ብቻ ነበረች።

አልማ 19፥6፣ 13–16

አቢሽ ብዙ ሰዎችን እያናገረች

አቢሽ ስለዚህ ተአምር ለሰዎች መናገር ፈለገች። ሰዎች የሆነውን ነገር ሲያዩ በእግዚአብሔር ኃይል እንደሚያምኑ ተስፋ አደረገች። ስለዚህ አቢሽ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ሮጠች። እግዚአብሔር በንግሥቲቱና በንጉሡ ላይ ያደረገውን ሄደው እንዲያዩ ለህዝቡ ነገረቻቸው።

አልማ 19፥17

ብዙ ሰዎች መሬት ላይ ያሉትን ሰዎችን እያዩ

ብዙ ሰዎች ወደ ንግሥቲቱ እና ንጉሱ ቤት መጡ። ንግስቲቱ፣ ንጉሱ እና አገልጋዮቻቸው ሁሉ የሞቱ ይመስሉ ስለነበር ተገረሙ።

አልማ 19፥18

ሰዎች እየተከራከሩ

ሰዎቹ ግራ ገብቷቸው ነበር። በንግሥቲቱ እና በንጉሱ ላይ ስለሆነው ነገር ተከራከሩ።

አልማ 19፥19–21

አቢሽ ተንበርክካ የንግሥቲቱን እጅ ይዛ

አቢሽ ስትመለስ ሰዎቹ ሲከራከሩ ተመለከተች። እነሱ የእግዚአብሔርን ኃይል ስላላዩ አዘነች። ከዚያም ንግስቲቱን በእጇ ይዛ አነሳቻት፣ ንግስቲቱም ቆማ ኢየሱስን አመሰገነች።

አልማ 19፥28–29

ንጉሡና ንግሥቲቱ ከአቢሽና ከአሞን ጋር ቆመው

ንግስቲቱ የባሏን እጅ ያዘች እሱም ቆመ። ንጉሡም ለህዝቡ ስለ ኢየሱስ ተናገረ። ከዚያም አሞን እና ሌሎች አገልጋዮችም ተነሱ። ሁሉም ኢየሱስ እንደቀየራቸው ለሕዝቡ ነገሩ። አሁን መልካም ነገር ብቻ ለመስራት ፈለጉ። ብዙ ሰዎችም አመኑዋቸው።

አልማ 19፥29–36

አቢሽ፣ ንግስቲቱ እና ንጉሱ ጥምቀትን እየተመለከቱ

አቢሽ ተስፋ እንዳደረገችው ሰዎች የእግዚአብሔርን ኃይል ተመለከቱ። ብዙ ሰዎች በኢየሱስ አመኑ እንዲሁም ተጠመቁ። የእግዚአብሔር መንፈስ ከእነሱ ጋር ነበረ። በምድራቸውም ቤተክርስቲያንን አቋቋሙ። ኢየሱስ ንስሐ የሚገባን እና በእርሱ የሚያምንን ሁሉ እንደሚረዳ ተመለከቱ።

አልማ 19፥17፣ 31፣ 35–36