Scripture Stories
አልማ እና ቆሪሆር


“አልማ እና ቆሪሆር፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 30

አልማ እና ቆሪሆር

እግዚአብሔር እውን እንደሆነ ማመን

ምስል
በተጨናነቀ መንገድ ላይ ቆሪሆር አብሮት ከሚሄድ አንድ ሰው ጋር በፈገግታ እየተነጋገረ

ቆሪሆር የሚባል ሰው ወደ ዛራሔምላ ምድር መጣ። እግዚአብሔርና ኢየሱስ ክርስቶስ እውን እንዳልሆኑ ለሰዎች ተናገረ።

አልማ 30፥6፣ 12፣ 37–38፣ 45

ምስል
ቆሪሆር ላዘነ ልጅ ፈገግታ እያሳየ

ቆሪሆር ሰዎች አንድን ነገር ማወቅ የሚችሉት ካዩት ብቻ ነው አለ። በኢየሱስ ባመኑ ሰዎችን ላይ አሾፈ።

አልማ 30፥13–16

ምስል
ቆሪሆር በፈገግታ ከብዙ ሰዎች ጋር እየተነጋገረ

ቆሪሆር፣ ሰዎች የእግዚአብሔር ትእዛዛት እንደማያስፈልጓቸው ተናገረ። ሰዎች የፈለጉትን ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላሉ አለ። ብዙ ሰዎች አመኑት። መጥፎ ነገሮችን ለማድረግም ወሰኑ።

አልማ 30፥17–18

ምስል
ቆሪሆር ታስሮ በወታደሮች ከመንደር እየወጣ

ቆሪሆር አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎችን ለማስተማር ሞከረ፣ ነገር ግን እነሱ አላመኑትም። አስረው አባረሩት። በምትኩ ወደ ጌዴዎን ምድር ሄደ። በዚያም ያሉት ሰዎች አሰሩት። ወደ አልማ ላኩት።

አልማ 30፥19–29

ምስል
ቆሪሆር በፈገግታ ወደ አልማ እያሳየ

ቆሪሆር እግዚአብሔር የለም በማለት ለአልማ ነገረው። አልማ እና ሌሎች ካህናት ለህዝቡን እየዋሹ ነው አለ። ቆሪሆር ህዝቡ የማይረባ ባህል እንዲከተል እያደረጉ እንደሆነ ተናገረ። ከህዝቡም ገንዘብ እየወሰዱም ነው አለ። አልማ ይህ እውነት እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። በእግዚአብሔርና በኢየሱስ እምነት አለው።

አልማ 30፥30–40

ምስል
አልማ ከብዙ ሰዎች ጋር እያወራ፣ ቆሪሆር ደግሞ ከበስተጀርባ እጆቹን አጣምሮ ተቀምጦ

አልማ ነቢያት እና በምድር ላይ ያለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዳለ ሰዎች እንዲያውቁ ይረዳል አለ። ቆሪሆር ተጨማሪ ማረጋገጫ ፈለገ። አልማ ለቆሪሆር ማስረጃ እንደሚሰጥ ተናገረ። እግዚአብሔር ቆሪሆር መናገር እንዳይችል እንደሚያደርግ ተናገረ። አልማ ይህን እንደተናገረ ቆሪሆር መናገር አቃተው።

አልማ 30፥41–50

ምስል
ቆሪሆር በጣም አዝኖ በላዩ ላይ የተጻፈበት ወረቀት ላይ እያመለከተ፣ ብዙ ሰዎች ደግሞ ከእሱ ሸሽተው ሲሄዱ

ቆሪሆር እግዚአብሔር መኖሩን እንደሚያውቅ ጻፈ። ሁልጊዜም ያውቅ ነበር። ሰይጣን እንዳታለለውም ጻፈ። ሰይጣን ቆሪሆር ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ ውሸት እንዲያስተምር ነግሮት ነበር። ሕዝቡ ስለ ቆሪሆር እውነቱን ሲያውቁ አስተምሮቱን ማመን አቆሙ። ንስሐ ገብተው ኢየሱስን እንደገና መከተል ጀመሩ።

አልማ 30፥52–53፣ 57–58