Scripture Stories
ኔፊ እና የነሐስ ሰሌዳዎች


“ኔፊ እና የነሐስ ሰሌዳዎች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

1 ኔፊ 4–5

ኔፊ እና የነሐስ ሰሌዳዎች

መንፈስን መከተልን መማር

ምስል
ኔፊ ወደ ህንፃው እየቀረበ እና ወንድሞች እየተመለከቱ

ላማን፣ ልሙኤል፣ ሳም እና ኔፊ በሌሊት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ወንድሞቹ ከከተማው ውጭ ተደብቀው ሳለ ኔፊ ወደ ላባን ቤት ሄደ።

1 ኔፊ 4፥4–5

ምስል
ኔፊ፣ ላባንን መሬት ላይ ሳለ ሲመለከተው

ኔፊ መንፈሱ እንዲመራው ፈቀደ። ምን ማድረግ እንደሚገባው አላወቀም ነበር፣ ነገር ግን ጌታ የነሐስ ሰሌዳዎቹን ማምጣት እንዲችል እንደሚረዳው ያውቅ ነበር።

1 ኔፊ 4፥6

ምስል
ኔፊ የላባንን ጎራዴ ይዞ

ኔፊ ወደ ላባን ቤ ሲቀርብ፣ ላባንን መሬት ላይ ወድቆ አገኘው። ላባን ሰክሮ ነበር። ኔፊ የላባንን ጎራዴ አየና አነሳው።

1 ኔፊ 4፥7–9

ምስል
ኔፊ ከላባን ዞር ሲል

ኔፊ ሰይፉን ሲመለከት፣ መንፈስ ላባንን እንዲገድለው ነገረው። ኔፊ ግን ሊገድለው አልፈለገም። የኔፊ ቤተሰብ ያለቅዱሳት መጻህፍት ከሚቀሩ ላባን ቢሞት የተሻለ እንደሚሆን መንፈስ ለኔፊ ነገረው። እነርሱ በነሐስ ሰሌዳዎቹ ላይ የተጻፉት የእግዚአብሔር ትእዛዛት ያስፈልጓቸው ነበር።

1 ኔፊ 4:10–11፣ 13–17

ምስል
ኔፊ እየጸለየ

ኔፊ ላባን ሊገድለው እንደሞከረ ያውቃል። በተጨማሪምላባን ንብረታቸውን ሰርቋል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አያከብርም።

1 ኔፊ 4፥11

ምስል
ኔፊ የላባንን ልብስ ለብሶ

መንፈስ፣ ላባንን እንዲገድል እንደገና ለኔፊ ነገረው። ጌታ የነሐስ ሰሌዳዎችን ለማምጣት እንዲችል መንገድ እንዳዘጋጀለት ኔፊ አወቀ። መንፈሱን ለመታዘዝ መረጠ። ኔፉ ላባንን ገደለው እንዲሁም የላባንን ልብስ ለበሰ።

1 ኔፊ 4፥12–13፣ 17–19

ምስል
ኔፊ ከዞራም ጋር ሲነጋገር

ኔፊ ከዚያም ወደ ላባን ግምጃ ቤት ሄደ እና ከላባን አገልጋይ ዞራም ጋር ተገናኘ። ኔፊ በሚያደርገው እና በሚናገረው እንደ ላባን አስመሰለ።

1 ኔፊ 4፥20–23፣ 35

ምስል
ዞራም የነሐስ ሰሌዳዎቹን ይዞ

ኔፊ የነሐስ ሰሌዳዎቹን እንደሚፈልግ ለዞራም ነገረው። ከዚያም ኔፊ ዞራም ከእርሱ ጋር እንዲመጣ ነገረው። ዞራም፣ ኔፊ ላባን መሰለው፣ ስለዚህ ኔፊ እንደጠየቀው አደረገ።

1 ኔፊ 4፥24–26

ምስል
ወንድሞቹ ከኔፊ ሲሸሹ

ኔፊ እና ዞራም ከከተማው ሲወጡ፣ ኔፊ ለላማን፣ ለልሙኤል እና ለሳም ላባን መሰላቸው። ፈርተው ስለነበር መሸሽ ጀመሩ።

1 ኔፊ 4፥28

ምስል
ወንድማማቾቹ ሲነጋገሩ እና ዞራም ወደ ኋላ ሲመለከት

ኔፊ ወንድሞቹን ጠራቸው። ኔፊ መሆኑን ሲያውቁ መሮጥ አቆሙ። ከዚያም ግን ዞራም ፈራ እና ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ሞከረ።

1 ኔፊ 4፥29–30

ምስል
ኔፊ ከዞራም ጋር ሲነጋገር

ኔፊ ዞራምን አስቆመው። ጌታ ሰሌዳዎቹን እንዲያመጡ እንዳዘዛቸው ለዞራም ነገረው። ዞራም ከእነርሱ ጋር ወደ ቃል ኪዳን ምድር እንዲሄድ ጋበዘው። ዞራም ሰራተኛ ሳይሆን ነጻ ሰው ለመሆን እንደሚችል አወቀ፣ እናም ከኔፊ እና ቤተሰቦቹ ጋር አብሮ ለመሄድ ቃል ገባ።

1 ኔፊ 4፥31–37

ምስል
ኔፊ እና ወንድሞቹ እንዲሁም ዞራም ለሳርያ እና ለሌሂ ሰላምታ ሲያቀረቡ

ወደ ሌሂ እና ሳርያ ተመለሱ። ሌሂ እና ሳርያ ልጆቻቸውን በማየታቸው በጣም ተደስተው ነበር። ሳርያ ልጆቿ እንደሞቱ አስባ ነበር። ጌታ የልጆቿን ደህንነት ስለጠበቀ፣ አሁን ቤተሰቦቻቸው ከኢየሩሳሌም እንዲወጡ እንደታዘዙ አመነች። ሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ ጌታን ለማመስገን መስዋዕቶችን አቀረቡ።

1 ኔፊ 4፥385፥1–9

ምስል
ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር የነሐስ ሰሌዳዎቹን ሲያነብ

ሌሂ የነሐስ ሰሌዳዎቹን አነበበ። ሰሌዳዎቹ የነቢያት ትምህርቶችን እንደያዙ አየ። በተጨማሪም ከቅድመ አያቶቹ አንዱ ወንድሞቹ ከረጅም ጊዜ በፊት በግብፅ ሸጠውት የነበረው ዮሴፍ እንደሆነ ተረዳ። ሌሂ የንሐስ ሰሌዳዎቹ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ያውቅ ነበር። ጌታ ቤተሰቡ ተእዛዛቱ እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ያውቅ ነበር።

1 ኔፊ 5፥10–22