Scripture Stories
የኢየሱስ መወለድ ምልክቶች


“የኢየሱስ መወለድ ምልክቶች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 ኔፊ 1

የኢየሱስ መወለድ ምልክቶች

በነቢይ ትምህርቶች ላይ እምነት

ምስል
እናት እና አባት ህፃን አቅፈው ከልጆች ጋር በከተማ ውስጥ እየሄዱ

ነቢዩ ሳሙኤል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት ምልክቶች ካስተማረ አምስት ዓመት አካባቢ ሆነው። ብዙ ሰዎች አምነው ምልክቱን ይጠብቁ ነበር። ሌሎች ሰዎች ሳሙኤል እንደተሳሳተ እና የምልክቶቹ ጊዜ እንዳለፈ ተናገሩ። ኢየሱስ አይመጣም በማለት በአማኞች ላይ ተሳለቁባቸው።

ሔለማን 14፥2–73 ኔፊ 1፥4–6

ምስል
ቤተሰብ እቤት ተቀምጦ እና አባት እየተናገረ

አማኞች ተጨንቀው የነበረ ቢሆንም እምነት ነበራቸው። ምልክቶቹን መጠባበቃቸውን ቀጥለው ነበር። አንዱ ምልክት የማይጨልምበት አንድ ሌሊት ነበር። ፀሐይ ከጠለቀች በኋላም እንኳን እንደ ቀን ብሩህ ይሆናል። ጨለማ የሌለበት ሌሊት ኢየሱስ በቀጣዩ ቀን በሌላ አገር እንደሚወለድ ምልክት ይሆናል።

ሔለማን 14፥2–43 ኔፊ 1፥7–8

ምስል
እየተጮኸበት በፍርሀት ውስጥ ያለ ቤተሰብ

ያላመኑ ሰዎች እቅድ አወጡ። አንድ ቀን መረጡ፣ ምልክቱ በዚያ ቀን ካልተከሰተም አማኞች ይገደላሉ አሉ።

3 ኔፊ 1፥9

ምስል
ኔፊ ሰዎች በቤተሰብ ላይ ክፉ ሲያደርጉ እየተመለከተ

በዚህ ጊዜ ኔፊ የሚባል ሰው ነቢይ ነበር። አንዳንድ ሰዎች አማኞችን ለመግደል በመፈለጋቸው በጣም አዘነ።

3 ኔፊ 1፥10

ምስል
ኔፊ ለመጸለይ ተንበርክኮ

ኔፊ መሬት ላይ ተደፍቶ በእምነታቸው ምክንያት ሊሞቱ ስለነበሩ አማኞች ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ቀኑን ሙሉ ጸለየ።

3 ኔፊ 1፥11–12

ምስል
ኔፊ እጆቹን ጨብጦ እየጸለየ

ለጸሎቱ መልስ፣ ኔፊ የኢየሱስን ድምጽ ሰማ። ኢየሱስ ምልክቱ በዚያ ሌሊት እንደሚሆን፣ ከዚያም ደግሞ በሚቀጥለው ቀን እንደሚወለድ ተናገረ።

3 ኔፊ 1፥12–14

ምስል
ሰዎች ሰማይን በመደነቅ እየተመለከቱ

በዚያች ሌሊት ፀሐይ ብትጠልቅም ጨለማ አልነበረም። የሳሙኤልን ቃል ያላመኑት ሰዎች በጣም ከመደነቃቸው የተነሳ በምድር ላይ ወደቁ። ባለማመናቸው ፈሩ። ያመኑት ሰዎች ሳይገደሉ ቀሩ።

3 ኔፊ 1፥15–19

ምስል
ቤተሰቦች ደማቅ ሰማያዊ የሆነን ሰማይ በአድናቆት እየተመለከቱ

በማግስቱ ፀሀይዋ እንደገና ወጣች፣ ሰማዩም ብሩህ ሆኖ ቆየ። ኢየሱስ የሚወለድበት ቀን ይህ እንደሆነ ሰዎቹ ሁሉ አወቁ።

3 ኔፊ 1፥19

ምስል
ሰዎች ወደ ሰማይ ቀና ብለው አዲስ ኮከብ እያዩ

ሰዎቹ ሌላ ምልክት አዩ። አዲስ ኮከብ በሰማይ ታየ። ሳሙኤል የተናገራቸው ምልክቶች በሙሉ ተፈጸሙ። ተጨማሪ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ አምነው ተጠመቁ።

ሔለማን 14፥2–73 ኔፊ 1፥20–23