Scripture Stories
ወጣቱ አልማ


“ወጣቱ አልማ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“ወጣቱ አልማ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

ሞዛያ 25–28አልማ 36

አልማ ወጣቱ

ትልቅ ለውጥ

ምስል
ሞዛያ እና ትልቁ አልማ

ንጉስ ሞዛያ፣ አልማ በዛራሔምላ ያለችውን ቤተክርስቲያን እንዲመራ ሀይል ሰጠው። አልማ ህዝቡ ንስሀ እንዲገቡ እና በጌታ እምነት እንዲኖራቸው አስተማራቸው።

ሞዛያ 25፥19–2426

ምስል
ወጣቱ አልማ

አልማ፣ ስሙ አልማ የተባለ ወንድ ልጅ ነበረው። ወጣቱ አልማ አባቱ ያስተምረው የነበረውን አያምንም ነበር።

ሞዛያ 27፥8

ምስል
ወጣቱ አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች ከሰዎች ጋር እየተነጋገሩ

ሞዛያ በጌታ የማያምኑ ወንድ ልጆችም ነበሩት። እነርሱም ከወጣቱ አልማ ጋር ጓደኞች ነበሩ። ሁሉም፣ ሰዎች ቤተክርስቲያኗን እንዲክዱ ይፈልጉ ነበር። አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚቃረኑ ነገሮችን ወደማድረግ መሯቸው።

ሞዛያ 27፥9–10አልማ 36፥6

ምስል
ወጣቱ አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች መልአኩን እየፈሩ

አንድ ቀን፣ ጌታ እንዲያቆሙ የሚያደርጋቸው መልአክ ላከ። መልአኩ ቤተክርስቲያኗን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ሙከራ እንዲያቆሙ ነገራቸው። አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች በጣም ፈርተው ስለነበረ መሬትም ላይ ወደቁ።

ሞዛያ 27፥11–18አልማ 36፥6–9

ምስል
ወጣቱ አልማ በሕመም ላይ እያለ

አልማ ለሶስት ቀናት እና ለሶስት ምሽቶች መናገር እና መነቃነቅ አልቻለም ነበር። አድርጓቸውበነበሩት ትክክል ያልሆኑ ነገሮች የተነሳ መጥፎ ሥሜት ተሰምቶት ነበር። ደግሞም ብዙ ሰዎችን ጌታን ወደመካድ ስለመራቸው ተጨንቆ ነበር።

ሞዛያ 27፥19አልማ 36፥10–16

ምስል
ወጣቱ አልማ ተንበርክኮ

አልማ በኃጢያቱ ምክንያት ብዙ ተሰቃየ። ከዚያም አባቱ ስለ እግዚአብሔር ልጅ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ይናገር የነበረውን አስታወሰ።

አልማ 36፥17

ምስል
ወጣቱ አልማ ደስተኛ ሆኖ

አልማ፣ ኢየሱስ ይምረው ዘንድ ጸለየ። ከጸለየ በኋላ፣ ስቃዩን አያስታውስም ነበር። ጌታ ይቅር እንዳለው አወቀ። ከዚያ በኋላ ስለሃጢያቶቹ መጥፎ ሥሜት አልተሰማውም። በምትኩ፣ አልማ ደስተኛ ናበረ።

ሞዛያ 27፥24፣ 28–29አልማ 36፥18–22

ምስል
ወጣቱ አልማ እና ሞዛያ ወንድ ልጆች አንድን ሰው እየረዱ

አልማ ጥንካሬውን አገኘ። እርሱ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች ንስሀ ለመግባት እና የተከሰቱትን ስቃዮች ሁሉ ለማስተካከል ወሰኑ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሌሎችም ንስሀ እንዲገቡ በመርዳት ጌታን አገለገሉ። ሞዛያ ያስተዳድረው በነበረው ምድር በሙሉ በመጓዝ ህዝብን ሰለኢየሱስ አስተማሩ።

ሞዛያ 27፥20–24፣ 32–37አልማ 36፥23–26

ምስል
የሞዛያ ወንዶች ልጆች እየሄዱ

አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች በህይወታቸው ውስጥ ደስታ ያመጣውን የኢየሱስ ትምህርት ለማካፈል ፈለጉ። ጌታን እና ሕዝቡን ለማገልገል ጠንክረው ሰሩ። የሞዛያ ወንድ ልጆች ካሉበት ለመሄድ እና ላማናውያንን ስለኢየሱስ ለማስተማር መረጡ። አልማ ባለበት ለመቆየት እና ኔፋውያንን በማስተማር ለመቀጠል መረጠ።

ሞዛያ 27፥32–3728፥1–1029፥42–43