Scripture Stories
ቴአንኩም እና ሞሮኒ


“ቴአንኩም እና ሞሮኒ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 62

ቴአንኩም እና ሞሮኒ

ታላቅ ድፍረትን ማሳየት

ምስል
አሞሮን ከላማናውያን ሠራዊት ጋር ሆኖ ከኔፋውያን ሠራዊት ጋር ሲዋጋ

አማሊቅያ ከሞተ በኋላ፣ ወንድሙ አሞሮን የላማናውያን ንጉስ ሆነ። አሞሮን ከኔፋውያን ጋር መዋጋቱን ቀጠለ። ጦርነቱ ለዓመታት ዘለቀ። ኔፋውያን ማሸነፍ ጀመሩ፣ ስለዚህ ሁሉም የላማናውያን ሰራዊት ወደ አንዲት ከተማ ሸሸ። ሞሮኒ፣ ቴአንኩም፣ እና ሌላ ኔፋዊ ሻምበል ሠራዊታቸውን በመያዝ የላማናውያን ሠራዊቶችን አሣደዷቸው።

አልማ 52፥3–454፥16–2462፥12–35

ምስል
ቴአንኩም የጦር መሣሪያ ይዞ በሌሊት ወደ ከተማ እየቀረበ

አማሊቅያ እና አሞሮን የዚህ ትልቅ፣ ረጅም ጦርነት ምክንያት በመሆናቸው ቴአንኩም ተናድዶ ነበር። በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ሰዎች ሞተዋል በተጨማሪም የምግብ እጥረት ነበር። ቴአንኩም ጦርነቱን ለማቆም ፈለገ። አሞሮንን ለመፈለግ በሌሊት ወደ ከተማው ገባ።

አልማ 62፥35–36

ምስል
ቴአንኩም መንጠቆ ያለውን ገመድ በመያዝ ከግንብ ላይ እየዘለለ

ቴአንኩም የከተማዋን ግንብ ዘሎ ገባ። አሞሮን የተኛበትን እስኪያገኝ ድረስ በከተማው ውስጥ ከቦታ ወደ ቦታ ሄደ።

አልማ 62፥36

ምስል
ቴአንኩም በድንኳን መግቢያ ላይ ጦር እና ገመድ ይዞ ቆሞ

ቴአንኩም በአሞሮን ላይ ጦር ወረወረ። ልቡ አጠገብ ወጋው። ነገር ግን አሞሮን ከመሞቱ በፊት አገልጋዮቹን ቀሰቀሳቸው።

አልማ 62፥36

ምስል
ቴአንኩም የላማናውያን ወታደሮችን በጦር ገጠማቸው

የአሞሮን አገልጋዮች ቴአንኩምን አሳደው ገደሉት። ሌሎቹ የኔፋውያን መሪዎች ቴአንኩም በመሞቱ በጣም አዘኑ። ለህዝቡ ነፃነት ሲል በጀግንነት ታግሎ ነበር።

አልማ 62፥36–37

ምስል
የኔፋውያን ወታደሮች የላማናውያን ወታደሮችን ማርከው

ምንም እንኳን ቢሞትም፣ ቴአንኩም ኔፋውያን ጦርነቱን እንዲያሸንፉ ረድቷቸው ነበር። እሱ ላማናውያን መሪያቸውን እንዲያጡ አድርጓል። በማግስቱ ጠዋት፣ ሞሮኒ ላማናውያንን ተዋግቶ አሸነፈ። ላማናውያን የኔፋውያንን ምድር ለቀው ወጡ፣ ጦርነቱም አበቃ።

አልማ 62፥37–38

ምስል
ሻምበል ሞሮኒ መንደር የሚገነቡ ሰዎችን እየመራ እንዲሁም ቤተሰቦች እየተመለከቱ

በስተመጨረሻ ሰላም ሰፈነ። ሞሮኒ የኔፋውያን ምድር ከላማናውያን ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ ለማድረግ ጠንክሮ ሰርቷል። ከዚያም ሞሮኒ በሰላም ለመኖር ወደ ቤቱ ሄደ። ነቢያት ወንጌልን አስተማሩ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን መሩ። ህዝቡም በጌታ ታመነ፣ እርሱም ባረካቸው።

አልማ 62፥39–51