Scripture Stories
የወይራ ዛፎች


“የወይራ ዛፎች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ያዕቆብ 5–6

የወይራ ዛፎች

እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለው ፍቅር

ምስል
ያዕቆብ ሲናገር የወይራ ዛፍ ምስል ይታያል

ያዕቆብ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። እግዚአብሔር ህዝቡን ምን ያህል እንደሚወድ ኔፋውያንን ሊያስተምራቸው ፈለገ። ያዕቆብም የወይራ ዛፍ ስለነበሩበት የወይን ስፍራ አንድ ታሪክ ነገራቸው። የወይኑ ስፍራ ጌታ እና አገልጋዩ የወይኑን ቦታ ተባብረው ተንከባከቡ።

ያዕቆብ 5፥1–4፣ 76፥4–5

ምስል
የወይኑ ስፍራ ጌታ ከወይራ ዛፍ አጠገብ በአካፋ ይቆፍራል

ጌታ መልካም ፍሬ የሚያፈራ አንድ ልዩ የወይራ ዛፍ ነበረው። ያዕቆብ ይህ ዛፍ እንደ እግዚአብሔር ህዝብ ወይም እንደ እስራኤል ቤት እንደሆነ ተናገረ። ፍሬውም እንደ ሰዎች ድርጊቶች ነበር። ጌታ ይህን ዛፍ በጣም ይንከባከበው ነበር። ሥሩን በመመገብና ቅርንጫፎቹን በመግረዝ እንዲያድግ ረድቶታል። ለመኖር የሚያስፈልገውን ሰጠው።

ያዕቆብ 5፥1–3፣ 56፥1፣ 7

ምስል
የወይራ ዛፉ መሞት ጀመረ

ከጊዜ በኋላ፣ የእርሱ ልዩ ዛፍ መሞት ጀመረ። ጥቂት ብቻ ጤናማ ቅርንጫፎች ነበሩ። ይህም ጌታ እንዲያዝን አደረገው። መልካም ፍሬ ማፍራቱን እንዲቀጥል ፈልጎ ነበር።

ያዕቆብ 5፥3፣ 6–8

ምስል
የወይኑ ስፍራ ጌታ ጤናማ ቅርንጫፎቹን ቆረጠና አስወገደ

ጤናማ የሆኑትን ቅርንጫፎች ለማዳን፣ ጌታ ቆረጣቸው ከዚያም ከሌሎች ዛፎች ጋር አዳቀላቸው። ከዚያም ከሌሎች ዛፎች በተገኙ ጤናማ በሆኑ ቅርንጫፎች ተካቸው።

ያዕቆብ 5፥7–14

ምስል
ወይኑ ስፍራ ጌታ እና ሰራተኞች የወይራ ዛፎችን ተንከባከቡ

ብዙ ጊዜ አለፈ። ጌታ እና አገልጋዩ ወደ ወይኑ ስፍራ በየጊዜው ይመጡ ነበር። የጌታን ልዩ ዛፍ ይንከባከቡት ነበር። እንዲሁም በመላው የወይኑ ስፍራ ባሉ ዛፎች ላይ ተበታትነው የነበሩትን ልዩ ቅርንጫፎች ተንከባከቡ። አብዛኛው ያፈራው ፍሬ ጥሩ ነበር። መልካሙ ፍሬ ጌታ እና አገጋዩ እንዲደሰቱ አደረገ።

ያዕቆብ 5፥15–29፣ 31

ምስል
የወይኑ ስፍራ ጌታ ከሰራተኛው ጋር ስለ ወይራ ዛፎች ተነጋገረ

ከትንሽ ጊዜ በኋላ፣ እያንዳንዱ ዛፎች ተጨማሪ ፍሬ አፈሩ። ነገር ግን አሁን ሁሉም ፍሬዎች መጥፎዎች ነበሩ። ጌታም አዘነ። የወይን ስፍራውን ወይም የዚህን ፍሬዎች ማጣት አይፈልግም ነበር። ዛፎቹን ለመርዳት በጣም ይሰራ ነበር። ሌላ ምን ማድረግ ይችል እንደነበርም አሰላሰለ። ከአገልጋዩ ጋር ተነጋገረ እንዲሁም፣ በጥረቱ ለመቀጠል መረጠ።

ያዕቆብ 5፥29–51

ምስል
ሰራተኛ ጤናማ ቅርንጫፍን ቆረጠ እና አስወገደ

የወይን ስፍራውን ለማዳን፣ ጌታ ከልዩ ዛፉ የቆረጣቸውን ቅርንጫፎች ይሰብሰቡ አለ። ከልዩ ዛፉ ጋር እንደገና ይዳቀሉ አለ።

ያዕቆብ 5፥51–60

ምስል
ጤናማ ቅርንጫፎች ከሌላ የወይራ ዛፍ ጋር ተዳቅለዋል

ይህም ጌታ በወይን ስፍራው የሚሰራበት የመጨረሻ ጊዜው ነበር። እንዲረዱም ሌሎች አገልጋዮችን ጠራ። ሁሉም ቅርንጫፎችን በመሰብሰበና በማዳቀልበጋራ ሰሩ።

ያዕቆብ 5፥61–72

ምስል
ጤናማ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች ፍሬ ይዘው

ሁሉንም ዛፎች ተንከባከቡ። መልካም ያልሆኑ ቅርንጫፎችን አስወገዱ እንዲሁም መልካሞቹን አስቀሩ። ከጊዜ በኋላ፣ የጌታ ልዩ ዛፍ አድጎ እንደገና መልካም ፍሬ አፈራ። ሌሎቹ ዛፎችም እንደ ልዩ ዛፉ ፍሬ አይነት መልካም የሆነ ፍሬ አፈሩ። ጌታ ተደሰተ። ዛፎቹ ድነው ነበር! ሁሉም እርሱ እንዲኖራቸው የፈለገውን ፍሬ አፈሩ።

ያዕቆብ 5፥73–75

ምስል
የወይኑ ስፍራ ጌታ እና ሰራተኞች ትልቅ ጤናማ የወይራ ዛፍን ሲመለከቱ

ጌታ አገልጋዮቹን አመሰገነ። ተግተው ስለሰሩ እና ትእዛዛቱን ስላከበሩ እንደተባረኩ ነገራቸው። ፍሬውን ከእነርሱ ጋር ተካፈለ፣ ይህም እነርሱን ደስተኛ አደረገ። ጌታ ለብዙ ጊዜ በፍሬው ተደሰተ።

ያዕቆብ 5፥75–77

ምስል
ያዕቆብ ሲናገር የኢየሱስ ክርስቶስ ምስል ይታያል

ያዕቆብ የወይራ ዛፎች ታሪኩን ፈጸመ። የወይኑ ስፍራ ጌታ ዛፎቹን እንደሚንከባከ ሁለ እግዚአብሔርም ህዝቡን እንደሚንከባከብ አስተማራቸው። ያዕቆብ ሁሉም ሰው ንስሀ እንዲገባና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ጠየቀ። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እነርሱን ለመርዳት ፍላጎት ስላለው፣ እግዚአብሔርን እንዲወዱት እና እንዲያገለግሉት አስተማራቸው።

ያዕቆብ 6፥1–5፣ 7፣ 11