አጠቃላይ ጉባኤ
ተጣሩ፣ አትውደቁ!
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ተጣሩ፣ አትውደቁ!

ወደ እግዚአብሔር ከጠራን፣ እንደማንወድቅ እመሰክራለሁ።

ዛሬ እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደሚሰማ እና ለግል በተበጀ መንገድ እንደሚመልስ በልቤ ያለውን ሙሉ እርግጠኝነት መመስከር እፈልጋለሁ።

እርግጠኛ አለመሆን፣ ሥቃይ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የልብ ስብራት ተንሠራፍተው ባሉለበት ዓለም ውስጥ፣ በግል ችሎታዎች እና ምርጫዎች እንዲሁም ከዓለም በሚገኝ እውቀት እና ደህንነት ላይ የበለጠ የመታመን ፍላጎት ሊያድርብን ይችላል። ይህ የዚህን ምድራዊ ህይወት ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችለውን እውነተኛውን የድጋፍ እና የእርዳታ ምንጭ ትኩረት እንዳንሠጠው ሊያደርገን ይችላል።

ምስል
የሆስፒታል ክፍል።

በህመም ምክንያት ሆስፒታል የገባሁበትን እና እንቅልፍም እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ የነበረበትን አንድ አጋጣሚ አስታውሳለሁ። መብራቱን ሳጠፋ እና ክፍሉ ሲጨልም፣ በኮርኒሱ ላይ “ጥሩን፣ አትውደቁ” የሚል አንጸባራቂ ምልክት አየሁ። የገረመኝ፣ በማግስቱ ያንኑ መልእክት በተለያዩ የክፍሉ ብዙ ቦታዎች ላይ ተደጋግመው ተመለከትኩ።

ምስል
ተጣሩ፣ አትውደቁ።

ይህ መልእክት በጣም አስፈላጊ የነበረው ለምንድነው? ነርሷን ስለሱ ስጠይቃት፣ “ያለብህን ህመም ከሚያብስ ተጨማሪ ጉዳት አንተን ለመከላከል ነው” አለችኝ።

ይህ ህይወት፣ በተፈጥሮው፣ አንዳንዶቹ በእኛ ድክመቶች ወይም መከራዎች፣ አንዳንዶቹ ሌሎች የመምረጥ ነፃነታቸውን በሚጠቀሙበት መንገድ ሣቢያ፣ እንዲሁም አንዳንዶቹ በእኛ የመምረጥ ነፃነት አጠቃቀም ምክንያት ከሥጋዊ አካላችን ጋር የተቆራኙ የሚያሠቃዩ ገጠመኞችን ያስከትላል።

አዳኙ እራሱ “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣” ወይም ጥሩ፣ “እና ይከፈትላችኋል” ሲል በተናገረ ጊዜ ከገባው የተሥፋ ቃል የበለጠ ሃይለኛ የሆነ ተስፋ አለ?1

ጸሎት የሰማይ አባታችንን “ለመጥራት እና እንዳንወድቅ” ለማድረድ የሚፈቅድልን የመገናኛ ዘዴ ነው። ነገር ግን፣ አፋጣኝ የሆነ ወይም የጠበቅነውን ዓይነት ምላሽ ባለማግኘታችን፣ ጥሪው እንዳልተሠማ የምናስብባቸው ሁኔታዎች አሉ።

ይህ አንዳንድ ጊዜ ወደ ጭንቀት፣ ሀዘን ወይም ብስጭት ይመራል። ነገር ግን ኔፊ “እኔም መርከቡን መስራት እንድችል ማስተማር እንዴት አይቻለውም?”2 በማለት በጌታ ያለውን እምነት የገለጠበትን አታውሱ። አሁንም ይህን እጠይቃችኋለሁ፣ እንዳትወድቁ እግዚአብሔር እናንተን ማስተማር እንዴት አይቻለውም?

በእግዚአብሔር መልሶች ላይ እምነት መጣል የእርሱ መንገዶች የእኛ መንገዶች እንዳልሆኑ3 እና “ሁሉም ነገሮች በጊዜአቸው ይከናወኑ ዘንድ ግድ [እንደሆነ]”4 መቀበልን ያመለክታል።

የአፍቃሪ እና የመሐሪ የሰማይ አባት ልጆች መሆናችንን የማወቅ እርግጠኝነት፣ “[ያለመታከት] ዘወትር መጸለይ እንዳለ[ብን]፤ … [በዚህም] ስራች[ንን] ለነፍሳች[ን] ደህንነት እን[ዲሆን]”5 ለማድረግ በጸሎት “የምንጠራበት” መነሳሻ መሆን ይገባዋል። በእያንዳንዱ ጸሎት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስንለምን የሰማይ አባትን ምን ስሜት እንደሚኖረው አስቡ። ይህን ስናደርግ ኃይል እና ርኅራኄ እንደሚገለጥ አምናለሁ!

ቅዱሳት መጻህፍት እንዳይወድቁ እግዚአብሔርን በጠሩ ምሳሌዎች የተሞሉ ናቸው። ሔለማን እና ሠራዊቱ፣ መከራ በገጠማቸው ጊዜ፣ ነፍሳቸውን በጸሎት አፍስሰው፣ እግዚአብሔርን ጠሩ። ግባቸውን እስካሳኩበት ጊዜ ድረስ ድፍረት እና ቁርጠኝነት በማግኘት፣ ማረጋገጫን፣ ሰላምን፣ እምነትን እና ተስፋን ተቀብለዋል።6

ሙሴ በቀይ ባህርና ሊሚያጠቁት እየቀረቡ በነበሩት ግብፃውያን መካከል በነበረበት ጊዜ እንዴት ወደ እግዚአብሔር ተጣርቶ እና ጮሆ ሊሆን እንደሚችል ወይም አብርሃም ልጁን ይስሐቅን እንዲሠዋ የተሰጠውን ትዕዛዝ በታዘዘ ጊዜ እንዴት ወደ እግዚአብሄር “ተጣርቶ” እና ጮሆ ሊሆን እንደሚችል አስቡ።

እያንዳንዳችሁ፣ መጥራት፣ ላለመውደቅ መልስ የነበረበት እና የሚሆንበት ልምዶች እንደነበሯችሁ እና እንደሚኖሯችሁ እርግጠኛ ነኝ።

ከሠላሳ ዓመት በፊት፣ እኔና ባለቤቴ በመዘጋጃ ቤት እና በቤተመቅደስ ለሚፈፀመው ጋብቻችን እየተዘጋጀን ሳለን፣ በአድማ ምክንያት የመዘጋጃ ቤት ጋብቻዎች መሰረዛቸውን የሚገልጽ የስልክ ጥሪ ደረሰን። የሥልክ ጥሪው የደረሰን ሥነ ሥርዓቱ እንዲፈፀም ከተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ነበር። ያልተያዙ የቀጠሮ ቀናትን ለማግኘት በሌሎች ቢሮዎች በርካታ ሙከራዎችን ካደረግን በኋላ፣ በታቀደው መሠረት መጋባት ስለመቻላችን መጨነቅ እና መጠራጠር ጀመርን።

እጮኛዬ እና እኔ ነፍሳችንን በጸሎት በማፍሰስ ወደእግዚአብሔር “ተጣራን”። በመጨረሻም፣ አንድ ሰው ከከተማው ወጣ ብላ በምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ ውስጥ የምታውቀው ሠው ከንቲባዋ ስለሆነበት ስለ አንድ ቢሮ ነገረችን። ሳናመነታ፣ ልንጎበኘው ሄድን እንዲሁም እኛን ማጋባት ይችል እንደሆነ ጠየቅነው። ደስ ይበላችሁ ሲለን፣ እሱ ተስማማ። የእርሱ ፀሐፊ የከተማዋን የምሥክር ወረቀት ማግኘት እና ሁሉንም ሰነዶች በማግስቱ ከቀትር በፊት ማስገባት እንዳለብን ቀጠሮ በመሥጠት ነገረችን።

በማግስቱ፣ ወደ ትንሿ ከተማ ሄድን ከዚያም አስፈላጊውን ሰነድ እንዲሠጡን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄድን። ይግረማችሁ ብሎ፣ ባለሥልጣኑ ይህን አልሰጣችሁም አለን፣ ምክያቱም ብዙ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተደብቀው በዚያች ከተማ ለመጋባት ይመጡ ስለነበር ነው በእርግጥ እኛ የመጣነው በዚያ መልኩ አልነበረም። እንደገና፣ ፍርሃትና ሀዘን አጠላብን።

ላለመውደቅ እንዴት በጸጥታ የሰማይ አባቴን ጠርቼው እንደነበረ አስታውሳለሁ። በአእምሮዬ ውስጥ ጥርት ያለ፣ “የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ።” የሚል ሥሜት በተደጋጋሚ ተሠማኝ። እጮኛዬን ግራ ቢያጋባትም፣ ወዲያውኑ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዴን አውጥቼ ለባለሥልጣኑ ሰጠሁት።

ባለስልጣኑ፣ “ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደመጣችሁ ለምን አልነገራችሁኝም? ቤተክርስቲያናችሁን በደንብ አውቃታለሁ።” ባለን ጊዜ ምንኛ እንደተደነቅን። ወዲያውኑ ሰነዱን ማዘጋጀት ጀመረ። ባለስልጣኑ ምንም ሳይለን ከጣቢያውወጥቶ ሲሄድ የበለጠ ተደነቅን።

ሃምሳ ደቂቃዎች አለፉ፣ ሆኖም አልተመለሰም ነበር። ከጠዋቱ 5፡55 ሆኗል፣ ስለዚህም ወረቀቶቹን ለማስገባት ያለን ጊዜ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ብቻ ነበር። በድንገት አንድ ቆንጆ ቡችላ ይዞ ብቅ አለ ከዚያም የሰርግ ስጦታ መሆኑን ነገረን እና ከሰነዱ ጋር አብሮ ሰጠን።

ሰነዳችንን እና አዲሱን ውሻችንን ይዘን ወደ ከንቲባው ቢሮ ሮጥን። ከዚያም አንድ የዚያ ቢሮ የሆነ መኪና ወደ እኛ ሲመጣ አየን። ከፊት ለፊቱ ቆምኩኝ። መኪናውም ቆመ፣ እና በውስጡ ያለችውን ጸሐፊ አየናት። እርሷም እያየችን፣ “ይቅርታ፣ በእኩለ ቀን ብያችኋለሁ ነበር። ወደ ሌላ ሥራ መሄድ አለብኝ” አለች።

“ላለመውደቅ” እንደገና እርዳታ አገኝ ዘንድ በሙሉ ልቤ ወደ ሰማይ አባቴ በመጣራት፣ በጸጥታ ራሴን ዝቅ አደረኩኝ። በድንገትም፣ ተዓምር ተከሰተ። ጸሃፊዋ እንዲህ አለችን፣ “እንዴት ያለ የሚያምር ውሻ አላችሁ። ለልጄ ያለ የት ማግኘት እችላለሁ?”

እኛም፣ ወዲያው “ይህ ለአንቺ ነው” ስንል መለስንላት።

ፀሐፊዋ በመገረም ተመለከተችን ከዚያም “እሺ ወደ ቢሮ እንሂድና ይህን እናመቻች” አለች።

ከሁለት ቀናት በኋላ፣ ካሮል እና እኔ እንደታቀደው የመዘጋጃ ቤት ጋብቻ ፈፀምን፣ ከዚያም በሊማ ፔሩ ቤተመቅደስ ውስጥ ታተምን።

እርግጥ ነው፣ መጣራት የእምነት እና የተግባር ጉዳይ መሆኑን—ማለቂያ በሌለው ጥበቡ መሰረት ጸሎታችንን የሚመልስ የሰማይ አባት እንዳለን ማመን እና ከዚያም ከጠየቅነው ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማስታወስ ያስፈልገናል። መጸለይ—መጣራት—የተስፋችን ምልክት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ከጸሎት በኋላ እርምጃ መውሰድ እምነታችን፣ በህመም፣ በፍርሃት ወይም በብስጭት ጊዜ የሚፈተን እውነተኛ እምነት መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው።

የሚከተሉትን እንድታስቡበት እመክራችኋለሁ፦

  1. እርዳታ ለመጠየቅ ጌታ የመጀመሪያ ምርጫችሁ እንደሆነ ሁልጊዜ አስቡ።

  2. ጥሩ፣ አትውደቁ። በእውነተኛ ጸሎት እግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቁት።

  3. ከጸለያችሁ በኋላ፣ የጸለያችሁበትን በረከት ለማግኘት የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።

  4. መልሱን በእርሱ ጊዜ እና መንገድ ለመቀበል ትሁት ሁኑ።

  5. አታቁሙ! መልስ እየጠበቃችሁ በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ወደፊት ቀጥሉ።

ምናልባት አሁን በሁኔታዎች ምክንያት፣ እንደሚወድቅ የሚሰማው እና እንደ ጆሴፍ ስሚዝ “እግዚአብሔር ሆይ የት ነህ? … እጅህስ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?”7 በማለት ለመጣራት የሚፈልግ ሰው ይኖር ይሆናል።

እንደእነዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን፣ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት “በመንፈሳዊ ፍጥነት”7 ጸልዩ፣ ምክንያቱም ጸሎቶቻችሁ ሁል ጊዜ ይሰማሉና!

ይህን መዝሙር አስታውሱ፦

ዛሬ ጠዋት ከክፍልህ ስትወጣ

ለመጸለይ አስበሀል?

በመድኃኒታችን በክርስቶስ ስም፣

ለፍቅር ውለታ ለመንክ

ይህን ዛሬ እንደ ጋሻ?

አቤቱ ፣ ጸሎት የደከመውን እንዴት ያሳርፋል!

ጸሎት ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣል።

ስለዚህ፣ ህይወት ሲጨልም እና አስፈሪ ሲሆን፣

መጸለይን አትርሳ።9

በምንጸልይበት ጊዜ፣ ሸክማችንን ያቃልልን ዘንድ አንድያ ልጁን የላከው የሰማይ አባታችን እቅፍ ሊሰማን ይችላል፣ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ከጮህን እንደማንወድቅ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።