የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፮


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፮፥፫–፮። ከማርቆስ ፲፮፥፬–፯፤ ሉቃስ ፳፬፥፪–፬ ጋር አነጻፅሩ

ሁለት መላእክቶች ሴቶችን በአዳኝ መቃብር አጠገብ ሰላም አሏቸው።

፫ ነገር ግን ሲመለከቱ፣ ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ (ይህም እጅግ ትልቅ ነበርና፣) እና ነጭ ልብስ የተጎናጸፉ ሁለት መላእክቶች በዚህ ላይ ተቀምጠው አዩና ደነገጡ።

፬ ነገር ግን መላእክቶቹ አትደንግጡ አሉአቸው፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።

፭ እና ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው።

፮ እና እነርሱ ወደመቃብር ውስጥ በመግባት ኢየሱስን ያኖሩበትን ስፍራ ተመለከቱ።