የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱፥፫። ከማርቆስ ፱፥፬ ጋር አነጻፅሩ

መጥምቁ ዮሐንስ በመለወጫ ተራራ ላይ ነው።

፫ እና ኤልያስ ከሙሴም ጋር ታዩአቸው፣ ወይም በሌላ ቃላት፣ መጥምቁ ዮሐንስ እና ሙሴ፤ እና ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።

ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱፥፵–፵፰። ከማርቆስ ፱፥፵፫–፵፰ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ የሚያሰናክል እጅን ወይም እግርን መቁረጥ ወደ ተሳሳተው መንገድ ከሚመራ ሰው ጓደኝነት ማስወገድ ጋር አነጻፅሯል።

፵ ስለዚህ፣ እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ወይም ወንድምህ ካሰናከለህ እና ካልተናዘዘ እና ካልተወው፣ እርሱም ይቆረጣል። ሁለት እጅ ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።

፵፩ አንተ እና ወንድምህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄዳችሁ፣ አንተ ወደ ህይወት ካለወንድምህ መግባት ይሻላልና።

፵፪ እንደገናም፣ እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ መሰረትህ የሆነው፣ የምትራመድበት፣ ተላላፊ ከሆነ፣ እርሱም ይቆረጣል።

፵፫ ሁለት እግር ኖሮህ እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

፵፬ ስለዚህ እያንዳንዱም ሰው ለሌላ፣ ወይም ሌላን በማመን ሳይሆን፣ ለእራሱ ይቁም ወይም ይውደቅ።

፵፭ አባቴን ጠይቁ፣ እና እንደምትቀበሉ እምነት ኖሮአችሁ፣ በእምነት ከጠየቃችሁ በምትጠይቁበት ወዲያው ይደረግላችኋል።

፵፮ የሚያይላችሁ አይናችሁ፣ ብርሀን እንዲያሳያችሁ እንዲጠብቃችሁ የተመደበላችሁ፣ ተላላፊ ሆኖ ካሰናከላችሁ፣ አውጡት።

፵፯ ሁለት አይኖች ኖሮህ ወደ ገሃነም እሳት ከመጣል በአንድ አይን ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት ይሻልሃል።

፵፰ አንተ ከወንድምህ ጋር ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመሄዳችሁ፣ አንተ ብትድን ይሻላልና።