አጠቃላይ ጉባኤ
ሆሳዕና እና ሀሌሉያ—ህያው ክርስቶስ፥ የዳግም መመለስ እና የትንሳኤ ልብ
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


ሆሳዕና እና ሀሌሉያ—ህያው ክርስቶስ፥ የዳግም መመለስ እና የትንሳኤ ልብ

በዚህ የሆሳና እና ሃሌሉያ ወቅት፣ ሃሌሉያን ዘምሩ—እርሱ ለዘለአለም ይነግሳልና።

በአለም ዙሪያ ያላችሁ ውድ ወንድሞች እና እህቶች፥ በሆሳዕና እና በሀሌሉያ፣ ህያው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በዚህ ቀጣይ ዳግም መመለስ እና በትንሳኤ ዘመን እናከብራለን። በፍጹም ፍቅር፣ አዳኛችን እንዲህ አረጋገጠልን፣ “በእኔ ሰላም ይኖራችኋል። በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዧችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌአለሁ።”1

ከጥቂት አመታት በፊት፣ እህት ጎንግ እና እኔ ከአንድ ተወዳጅ ቤተሰብ ስንገናኝ፣ ትንሿ ሴት ልጃቸው አይቪ በዓይናፋርነት የቫዮሊን መያዣዋን አወጣች። የቫዮሊኑን ደጋን አውጥታ፣ አጠበቀችው እና በላዩ ላይ ሮዝን[የገመድ ማጠናከሪያ] አደረገችበት። ከዚያም ደጋኑን ወደ መያዢያው አስገባች፣ ፈገግ አለች፣ እና ተቀመጠች። እንደ አዲስ ጀማሪ፣ ስለቫዮሊን የምታውቀውን በሙሉ አካፍላ ነበር። አሁን፣ ከብዙ አመታት በኋላ፣ አይቪ ቫዮሊንን በደንብ መጫወት ትችላለች።

ምስል
አይቪ እና ቫዮሊኗ

በዚህ ስጋዊ ህይወት ዘመን፣ ሁላችንም ትንሽ እንደ አይቪ እና ቫዮሊኗ ነን። ከመጀመሪያ እንጀምራለን። በተግባር እና ጽናት፣ እኛ እናድጋለን እናሻሽለን። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ፣ የምግባረ መልካም ሀላፊነት እና የሟች ልምምዶች በእርሱ የወይን እርሻ2 ውስጥ አብረን ስንሠራ እና የቃል ኪዳኑን መንገድ በምንከተልበት ጊዜ እንደ አዳኛችን እንድንሆን ይረዱናል።

ይህንን የሁለተኛ መቶ ዓመትን ጨምሮ፣ አመታዊ በአሎች የዳግም መመለስ ስርዓትን ያጎላሉ።3 የሚቀጥለውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ በማክበርም፣ ደግሞም ለትንሳኤ እንዘጋጃለን። በሁለቱም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም መመለስ እንደሰታለን። ህያው ነው—በዚያ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንዳንድ ብቻ ሳይሆን፣ ለሁሉም ነው። የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለመፈወስ፣ ምርኮኞችን ለማዳን፣ ዕውሮችን ማየት እንዲችሉ ለማድረግ፣ እና የተጎሳቆሉትን ነፃ ያወጣ ዘንድ መጥቷል እናም ይመጣልም።4 ያም እያንዳንዳችን ነን። የድሮ ድርጊታችን ምንም ቢሆን፣ ወይም ስለወደፊታችን ምንም ሀሳብ ቢኖረንም፣ የእርሱ የቤዛነት የተስፋ ቃል ይከናወናል።

ምስል
ወደ ኢየሩሳሌም የድል አገባብ

ነገ የሆሳዕና ቀን ነው። በተለምዶ ዘንባባ በጌታችን ላይ ደስታን ለመግለጽ ቅዱስ ምልክት ነው፣ ልክ ኢየሱስ በድል ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባ፣ በዚህም “ብዙ ሕዝብ … የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ።”5 (የዚህ የሃሪ አንደርሰን ሥዕል) ከጠረጴዛቸው በስተጀርባ በፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ቢሮ ውስጥ የተንጠለጠለውን ፎቶ የመጀመሪያ ታሪክ ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል።) በዮሀንስ ራዕይ መፅሐፍ ውስጥ፣ እግዚአብሔርን እና ጠቦትን የሚያሞግሱት ይህን የሚያደርጉት “ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው” ነው።6 “ከጻድቅነት ልብሶች” እና “ከክብር ዘውዶች” ጋር፣ የዘንባብ ዝንጣፊዎችም በከርትላንድ ቤተመቅደስ የምርቃት ጸሎት ላይ ተጨማሪዎች ነበሩ።7

በእርግጥም፣ የሆሳዕና ቀን አስፈላጊነት ህዝቦች ኢየሱስን በዘንባባ ሰላምታ ከሰጡት በላይ ነው። በሆሳዕና ቀን፣ ታማኞች ትንቢት እንደተሟላ ባስተዋሉት መልክ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ዘካሪያስ8 እና መዝሙር ጸሀፊው አስቀድመው በትንቢት እንደተናገሩት፣ ህዝቡ “ሆሣዕና በአርያም”9እያሉ ሲጮሁም፣ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም አህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ሆሳዕና ማለት “አሁን አድን”10ማለት ነው። በዚያም፣ እንደ አሁንም፣ እንደሰታለን፣ “በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው”11

ከሆሳዕና ቀን አንድ ሳምንት በኋላም የትንሳኤ ሰንበት ነው። ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት ኢየሱስ ክርስቶስ “የመጣው ያልነበረበትን እዳ ለመክፈል ነው፣ ምክንያቱም እኛ መክፈል የማንችለው እዳ አለብን።”12 በእርግጥም፣ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል፣ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ “የወንጌሉን ህግጋትና ስርዓቶችን በማክበር፣ መዳን ይችላሉ።”13 በትንሳኤም፣ ሀሌሉያን እንዘምራለን። ሀሌሉያ ማለት “ጌታ ይሆዋ አንተን እናሞግሳለን”14ማለት ነው። በሀንድል መሲህ ውስጥ የሚገኘው የሀሌሉያ መዝሙር እርሱ “የነገሥታት ንጉሥ፣ እና የጌቶች ጌታ”15እንደሆነ የሚታወጅበት ነው።

በሆሳዕና ቀን እና በትንሳኤ ሰንበት መካከል ያሉት ቅዱስ ድርጊቶች የሆሳዕና እና የሀሌሉያ ታሪኮች ናቸው። ሆሳዕና እግዚአብሔር እንዲያድነን የምንለምንበት ነው። ሀሌሉያም ለደህንነት እና ለዘለአለማዊነት ተስፋ ያለን ምስጋና የሚገለፅበት ነው። በሆሳዕና እና በሀሌሉያ ውስጥ ህያው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ እና የኋለኛው ቀን ዳግም መመለሻ ማእከላዊ ልብ እንደ ሆነ እናውቃለን።

የኋለኛው ቀናት ዳግም መመለስ የተጀመረው በአምላክ መገለጽ ነው—ለወጣቱ ነቢይ ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሒእር አብ እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በታዪበት ነው። ነቢዩ ጆሴፍ እንዳለው፣ “ወደ ሰማይ ለአምስት ደቂቃ ለማየት ብትችሉ፣ በርእሰ-ጉዳዩ ላይ የተጻፈውን ሁሉ በማንበብ ከምትችሉት በላይ ትችላላችሁ።”16 ሰማያት እንደገና ስለተከፈቱ፣ “በእግዚአብሔር፣ ዘለአለማዊ አባት፣ እና በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ”15—በመለኮታዊ አማልክት፣ እንደምናምን እናውቃለን።

በፋሲካ እሑድ ሚያዝያ 3 ቀን 1836 (እ.አ.አ)፣ በዳግም መመለስ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት፣ የከርትላንድ ቤተመቅደሱ በተመረቀበት ጊዜ ህያው ኢየሱስ ክርስቶስ ታየ። እርሱን ያዩትም እሳት እና ውሀን በማነጻጸር እርሱን ገልጸው ነበር፥ “ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ የራሱ ጠጕርም እንደ ንጹህ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ፊቱም ከብርቱ የጸሀይ ብርሀን በላይ የሚያበራ ነበር፤ ድምፁም እንዲህ የሚል እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ እንዲሁም የያህዌህ ድምፅ ነበር።”18

በእዚያም ጊዜ፣ አዳኛችን እንዲህ አወጀ፥ “እኔ ፊተኛውና ኋለኛው ነኝ፤ እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ፤ እኔም በአብ ዘንድ አማላጃችሁ ነኝ።”19 እንደገናም፣ ተጓዳኝ ተቃርኖዎች—መጀመሪያ እና መጨረሻው፣ ሕያው እና ሟች። እርሱ አልፋ እና ኦሜጋ፣ መጀመሪያ እና መጨረሻ፣20 የእምነታችን ጸሀፊ እና ፈጻሚ21ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከታየ በኋላም፣ ሙሴ፣ ኤልያስ፣ እና ኢልያ መጡ። በመለኮታዊ አመራር፣ እነዚህ የጥንት ታላቅ ነቢያት የክህነት ቁልፎች እና ስልጣንን መለሱ። በዚህም፣ በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆችን በሙሉ ለመባረክ፣ “የዚህ የዘመን ፍጻሜ ቁልፎች በእጆቻችሁ ተሰጥተዋል።22

ኤልያስ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ መምጣቱም “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ”23ኤልያስ ይመለሳል የሚለውን በብሉይ ኪዳን ያለውን የሚልክያስ ትንቢት ያሟላል። ይህን ሲያደርግ፣ የኤልያስ መምጣት በአጋጣሚ የተከሰተ ባይሆንም፣ የኤልያስ መመለስ ይመለከታል በሚለው የአይሁድ ፋሲካ ወቅት በአጋጣሚ የተገኘ ነው።

ብዙ ታማኝ አይሁድ ቤተሰቦች በአይሁድ ፋሲካ ጠረጴዛ ጎን አንድ መቀመጫ ቦታ ያዘጋጃሉ። ብዙዎችም ዋንጫዋን በሙሉ በመሙላት እርሱን ይጋብዙታል። እናም አንዳንዶቹ፣ ባህላዊው የፋሲካ ሰዴድ ወቅት፣ ኤልያስ ለመጋበዝ ከውጭ እየጠበቀ መሆኑን ለማየት ልጅን ወደ በር ይልካሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ በሩ በከፊል ክፍት ነው።24

እንደ ትንቢቱ መፈጸም እና የሁሉም ነገር በዳግም መመለስ ክፍልም፣25 ኤልያስ በትንሳኤ እና በፋሲካ መጀመሪያ ላይ በተስፋ ቃል እንደተነገረው መጥቷል፣ ቤተሰቦችን በምድርም ሆነ በሰማይ ለማሰር የማኅተም ስልጣንንም አመጣ። ሞሮኒ ነቢዩ ጆሴፍን እንዳስተማረው፣ ኤልያስ “ለአባቶች የተገባውን የተስፋ ቃል በልጆች ልብ ይተክላል፣ እናም የልጆቹንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል። እንዲህ ባይሆን ኖሮ፣” በማለት ሞሮኒ ቀጠለ፣ “መላው ምድር በ[ጌታ] ምጽአቱ በጠፋ ነበር።”26 የመንፈስ ቅዱስ መገለጫ የሆነው የኤልያስ መንፈስ፣ በትውልዶቻችን፣ በታሪካችን እና በቤተመቅደስ አገልግሎታችን ወደ ትውልዳችን (ካለፉት፣ ከአሁኑ እና ከወደፊቱ) ጋር ይስባል።

ፋሲካ ምን ምልክት እንዳለውም በአጭር እናስታውስ። ፋሲካ የእስራኤል ልጆች ከ400 ዓመታት ባርነት ነፃ የወጡበትን ቀን ያስታውሳል። እንቁራሪቶች፣ ቅሪቶች፣ ዝንቦች፣ የከብቶች ሞት፣ እባጮች፣ ብጉር፣ በረዶ እና እሳት፣ አንበጣ እና ከባድ የጨለማ ወረርሽኝ ከደረሰ በኋላ እንዴት ይህ ቤዛነት እንደመጣ የዘፀአት መጽሐፍ ይተርካል። የመጨረሻው መቅጸፍት በምድሪቱ የበኩር ልጆችን በሞት አደጋ ላይ ጥሎ ነበር፣ ግን ያልረከሰ የመጀመሪያ የበግ ጠቦት ደም በሮቻቸው መግቢያ ግንድ ላይ ከቀቡ፣ በእስራኤል ቤት ውስጥ አይደርስም ነበር።27

የሞት መልአክ በበጉ ምሳሌያዊ ደሙ ምልክት በተደረገባቸው ቤቶች አልፏል።28 ያ ማለፍ፣ ወይም ፋሲካ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በመጨረሻ ሞትን እንደሚያሸንፍ ይወክላል። በርግጥ የእግዚአብሔር በግ የኃጢያት ክፍያው ደም ጥሩውን እረኛችን ህዝቡን በሁሉም ስፍራ እና ሁኔታ፣ በመጋረጃው ሁለቱም ቦታዎች፣ ለመሰብሰብ ኃይል ይሰጠዋል።

በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይም፣ መፅሐፈ ሞርሞን “ስለ ክርስቶስ ሀይል እና ከሞት መነሳት”፣29—ማለትም ስለ ፋሲካ ምንነት፣ በሁለት ዳግም መመለስ አባባሎች ይገልፃል።

መጀመሪያ፣ ከሞት መነሳት በተጨማሪም “ትክክለኛና ፍጹም የሆነውን” አካላችን መመለስን ያካትታል፣ “እያንዳንዱም መገጣጠሚያ እና አጥንት፣” “እያንዳንዱ የራስ ጸጉርም አይጠፋም።”30 ይህ ተስፋ እግሮቻቸውን ላጡ፣ የማየት፣ የመስማት ወይም የመራመድ አቅም ለሌላቸው ወይም በቀላል ህመም፣ በአእምሮ ህመም ወይም በሌላ አቅም ለተዳከሙ ሰዎች ተስፋ ይሰጣል። ያገኘናል። ሙሉም ያደርገናል።

የትንሳኤ እና የጌታ የኃጢያት ክፍያ ሁለተኛ የተስፋ ቃልም፣ “ሁሉም ነገር ወደ ተገቢው ስርዓት [መመለሱ ነው]።31 ይህም መንፈሳዊ ዳግም መመለስ፣ ሥራችንን እና ምኞታችንን ያንፀባርቃል። በውኃ ላይ እንዳለ ዳቦ “ጥሩ የሆነውን፣”32 “ጻድቅ”፣ “ፍትሐዊ” እና “መሐሪ” ያድሳል።33 አልማ ይመልስልሀል የሚለውን ቃል ለ22 ጊዜ መጠቀሙ አያስገርምም፣34 በዚህም “ለሰዎች ፍትሃዊ ሁን፣ በትክክል ፍረድ፣ እናም ያለማቋረጥ መልካምን ስሩ”35በማለት ገፋፍቶናል።

“እግዚአብሔር እራሱ ለዓለም ኃጥያቶች የኃጥያት ክፍያ”36 ስለሆነ፣ የጌታ የኃጢያት ክፍያ በፊት የነበረውን ብቻ ሳይሆን፣ ሊሆን የሚችለውን የተሟላ ለማድረግ ይችላል። ሥቃያችንን፣ ሕመማችንን፣ ማንኛውንም ዓይነት ፈተናችንን ያውቃልና፣37 እንደ ድክመታችን መጠን በምህረት እኛን ሊረዳን ይችላል።38 “እግዚአብሔርም ደግሞ ፍፁም፣ እውነተኛ አምላክ፣ እናም መሃሪ አምላክ” ስለሆነ፣ የምህረት እቅድ “የፍትህን ፍላጎት አሟልቷል።”39 ንስሀ እንገባለን እናም የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። እስከዘለአለም “በፍቅሩ ክንዶች ውስጥ”40ይጠብቀናል።

ዛሬ ዳግም መመለስን እና ትንሳኤን እናከብራለን። ከእናንተ ጋር የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለሱ እየቀጠለ እንደሆነ እደሰታለሁ። ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት በዚህ የፀደይ ወቅት ብርሃን እና መገለጡ በጌታ ህያው ነብይ እና በስሙ በተጠራው ቤተክርስቲያኑ—የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን—በኩል እናም በድል ራዕይ እና መለኮታዊ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት በኩል መምጣታቸውን ይቀጥላሉ።

ከእናንተ ጋር፣ በዚህ ከትንሳኤ፣ ስለ እግዚአብሔር፣ ዘለአለማዊ አባት፣ እና ስለውድ ልጁ፣ ህያው ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ። ስጋዊ ሰዎች በክፋት ተሰቅለዋል እናም በኋላም ከሞት ተነስተዋል። ነገር ግን ህያው ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ከሞት በተነሳው ቅርጹ ብቻ የተሰቀለበትን ምልክቶች በእጆቹ፣ በእግሮቹ፣ እና በጎኑ ላይ ያሳያል። እርሱ ብቻ ነው እንዲህ ማለት የሚችለው፣ “እነሆ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለው፡፡”41 እርሱ ብቻ ነው እንዲህ የሚመሰክረው፣ “እኔ ከፍ የተደረኩት ነኝ። እኔ የተሰቀለው ክርስቶስ ነኝ። እኔ የእግዚአብሐር ልጅ ነኝ።”42

ልክ እንደ ትንሿ አይቪ እና ቫዮሊኗ፣ እኛም በነገሮች ገና እየጀመርን ነን። በእውነትም፣ “ዓይን ያላየው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።”43 በእነዚህ ጊዜያት እግዚአብሔርን ስንፈልግ እና እርስ በእርሳችን ስንረዳዳ፣ ስለእግዚአብሔር ቸርነት እና የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ለማሳደግ ስላለን ችሎታ ብዙ ለመማር እንችላለን። በአዲስ መንገዶች እና በአዲስ ቦታዎች፣ መስመር ላይ በመስመር፣ ደግነት ላይ በደግነት፣ በግል እና በጋራ በረከቶች ለመሆን እና ለመስጠት እንችላለን።

የትም የምትገኙት ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ አብረን ስንገናኝ እና ስንማር፣ የእናንተ እምነት እና መልካምነት በወንጌል ጀብዱ እና የምስጋና ስሜት ተሞልቻለሁ። የምስክርነትዎ እና የወንጌል ጉዞዎ ምስክሬ እና የወንጌል ጉዞዬን ያበለጽጋሉ። የሚያሳስቧችሁ ነገሮች እና ደስታዎች፣ ለቅዱሳኖቻችን ማህበረሰብ እና ለእግዚአብሔር ቤተሰብ ያላችሁ ፍቅር፣ እና የተመለሰው እውነት እና ብርሃን ያላችሁ መረዳት፣ በመሀከሉ ህያው ኢየሱስ ክርስቶስ እየተገኘበት፣ በዳግም የተመለሰው የወንጌል ሙላቴን ይጨምርለታል። በጋራም እንዲህ እናምናለን፣ “በዳመናም እና በጸሀይ ብርሀን፣ ጌታ ከእኔ ጋር ሁን።”44 በአንድነትም፣ በሸክሞች እና በመተሳሰብ ምክንያት፣ ብዙዎችን በረከቶቻችንን ለመቁጠር እንደምንችል እናውቃለን።45 በዕለት ተዕለት ዝርዝሮች እና ትናንሽ እና በቀላል ነገሮች ውስጥ ታላላቅ ነገሮች በሕይወታችን ውስጥ ሲከናወኑ ማየት እንችላለን።

“እናም እንዲህ ይሆናል ጻድቃን ከእያንዳንዱ ሀገሮች ተሰብሰበው ይወጣሉ፣ እና የዘለአለማዊ ደስታ መዝሙርንም እየዘመሩ ወደ ፅዮን ይመጣሉ።”47 በዚህ የሆሳና እና ሃሌሉያ ወቅት፣ ሃሌሉያ ዘምሩ—እርሱ ለዘለአለም ይነግሳልና። ሆሳዕና፣ ለእግዚያብሄር እና ለበጉ! በማለት ጩሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።