አጠቃላይ ጉባኤ
ክህነት ወጣቶችን እንዴት እንደሚባርክ
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


ክህነት ወጣትነትን እንዴት ይባርካል

በክህነት አማካኝነት ከፍ ልንደረግ እንችላለን። ክህነት ብርሃንን ወደአለማችን ያመጣል።

አዚህ በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። ለእናንተ ዛሬ ለመናገር እድል አንደማገኝ በመጀመሪያ ያወቅኩኝ ጊዜ አጅግ ተደስቻለሁ ነገር ግን በዚያኑ ቅጽበት በጣም ትህትና ተሰማኝ። ምን ላካፍል አንደምችል በማሰብ ብዙ ጊዜ አሳልፌአለሁ እናም መንፈስ በመልእክቴ ውስጥ በቀጥታ እንዲያናግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

በመጽሃፈ ሞርሞን ውስጥ ሌሂ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ለእያንዳንዱ ወንዶች ልጆቹ ጥንካሬያችውን አና ዘላለማዊ አቅማቸውን ማየት አንዲችሉ የረዳቸውን በረከት ሰጣቸው። ከስምንት ልጆች እኔ የመጨረሻው ነኝ፣ አንዲሁም በዚህ ባለፈው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በቤት የቀረሁት ብቸኛው ልጅ ነበርኩኝ። ወንድም አና አህቶቼ በአቀራቢያዬ አለመኖራቸው ወይም ሁልጊዜ ላናግረው የምችለው ሰው ካጠገቤ አለመኖሩ ለአኔ አስቸጋሪ ነበር። በጣም ብቸኘነት አንዲሰማኝ ያደረጉኝ ምሽቶቸም ነበሩ። አኔን ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ላደረጉት ወላጆቼ አጅግ አመስጋኝ ነኝ። የዚህ አንድ ምሳሌ የሚሆነው የተለየ አስቸጋሪ ጊዜ ባጋጠመኝ ጊዜ አባቴ የመጽናናት የክህነት በረከት በሰጠኝ ጊዜ ነው። ከበረከቱ በኋላ ነገሮች ወዲያው አልተለወጡም ነበር ነገር ግን ከሰማያዊ አባቴ እና ከአባቴ ሰላም እና ፍቅር ተሰምቶኛል። የክህነት በረከቶችን በፈለኩኝ ጊዜ ሁሉ መስጠት የሚቸል ብቁ የሆነ አንዲሁም ልክ ሌሂ ልጆቹን ሲባርክ እንዳደረገው ጥንካሬዬን እና ዘላለማዊ አቅሜን ማየት አንድችል የሚረዳኝ አባት ስላለኝ የተባረኩኝ አንደሆንኩኝ ይሰማኛል።

ምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆኑ ሁልጊዜ የክህነት በረከቶችን ማግኘት ትችላላችሁ። በአባላት፣ በጓደኞች፣ በአገልጋይ ወንድሞች፣ በክህነት መሪዎች እና በማይተዋችሁ ሰማያዊ አባት በኩል የክህነት በረከቶችን ልተቀበሉ ትችላላችሁ። ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን እንዲህ ብለዋል፥ “የክህነት በረከቶች ይህን ስጦታ እንዲሰጥ ከተጠየቀው ሰው በላይ በጣም ታላቅ የሆኑ ናቸው። … ብቁ ስንሆን የክህነት ስርዐቶች ህይወታችንን ያበለጽጉታል።”1

ተጨማሪ አመራር በምትፈልጉበት ጊዜ በረከቶችን ከመጠየቅ ወደኋላ አትበሉ። አስቸጋሪ በሆነው የህይወታችን ጊዜ ነው መንፈሱ ይበልጥ አንዲረዳን የምንፈልገው። ማንም ፍጹም አይደለም እናም ሁላችንም አስቸጋሪ ጊዜ ይገጥመናል። አንዳንዶቻችን በውጥረት፣ በጭንቀት፣ በሱስ ወይም ብቁ አይደለሁም በሚል ስሜት ልንስቃይ እንችላለን። የክህነት በረከቶች እነዚህን አስችጋሪ ጊዜያት እንድንቋቋም እና ወደፊት ስንጓዝ ሰላምን አንድናገኝ ሊረዱን ይችላሉ። በረከቶችን ለመቀበል ብቁ ሆነን ለመኖር እንደምንጥር ተስፋ አደርጋለሁ።

ሌላኛው ክህነት የሚባርከን መንገድ በፓትርያርክ በረከቶች በኩል ነው። ሃዘን ወይም ብቸኝነት በሚሰማኝ ጊዜ ሁሉ ፊቴን ወደ ፓትርያርክ በረከት ማዞርን ተምሪያለሁ። በረከቴ አቅሜን እና እግዚአብሔር ለእኔ ያለውን ልዩ እቅድ እንድመለከት ይረዳኛል። ከምድራዊ እይታዬ ባሻገር ማየት እንድችል ይረዳኛል እንዲሁም ያጽናናኛል። ስጦታዎቼን እና ብቁ ሆኜ ብኖር የምቅበላቸውን በረከቶች ያስታውሰኛል። ይበልጥ በምፈልግበት በእርግጠኛ ጊዜ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጥ እና በሮችን አንደሚከፍትልኝ ለማስታወስ እና ሰላም እንዲሰማኝ በማድረግ ይረዳኛል።

የፓትርያርክ በረከቶች ተመልሰን ከሰማያዊ አባታችን ጋር ለመኖር እንድንዘጋጅ ይረዱናል። የፓትርያርክ በረከቶች ከእግዚአብሔር እንደሚመጡ እና ድካማችንን ወደ ጥንካሬ ለመለወጥ ሊረዱን እንደሚችሉ አውቃለሁ። እነዚህ “ከእድል ነጋሪ“ የመጣ መልእክት አይደለም፤ እነዚህ በረከቶች መስማት የሚያስፈልገንን ይነግሩናል። ለያንዳንዳችን እንደ ሊያሆና ናቸው። እግዚአብሔርን ስናስቀድም እና በእርሱ እምነት ሲኖረን፣ በራሳችን ምድረበዳ ውስጥ ይመራናል።

የወንጌል በረከቶች ዳግም መመለስ እንዲችል እግዚአብሔር ዮሴፍ ስሚዝን በክህነት እንደባረከው፣ የወንጌልን በረከቶች በክህነት አማካኝነት በህይወታችን ልንቀበል እንችላለን። በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባን የመውሰድ መብት እና እድል ተሰጥቶናል። በዚህ የክህነት ስርአት የሚያነጻን እና የሚያጠራን መንፈሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንዲሆን ያስችለናል። ከህይወታችሁ አንድን ነገር የማስወገድ አስፈላጊነት ሲሰማችሁ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድትገቡ ሊረዳችሁ ወደሚችል ታማኝ መሪ ቅረቡ። መሪዎቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ ሃይል እንድታግኙ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

በክህነት ምክንያትም የቤተመቅደስ ስርአቶች በረከቶችንም ልንቀበል እንችላለን። ቤተመቅደስ መግባት ከቻልኩኝ ጊዜ ጀምሮ በየወቅቱ ወደዚያ መሄድን ግቤ እና ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር አድርጌዋለሁ። ጊዜን በመውሰድ እና በቅዱስ ቤቱ ውስጥ ወደ ሰማያዊ አባቴ ለመቅረብ አስፈላጊ የሆነውን መስዋእትነት በመክፈል ህይወቴን ሙሉ በእርግጥ የረዳኝን ራእይን አና መነሳሳትን በመቀበል ተባርኬአለሁ።

በክህነቱ አማካኝነት ከፍ ልንደረግ እንችላለን። ክህነቱ ብርሃንን ወደአለማችን ያመጣል። ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ እንዲህ ብለዋል፤ “ያለክህነት ስልጣን ሃይል መላው ምድር በጽኑ ይባክናል“ ( ት.&.እና ቃ. 2፥1–3) ይመልከቱ። ምንም ብርሃን ምንም ተስፋ አይኖርም—ጨለማ ብቻ።”2

እግዚአብሔር እያበረታታን ነው። ወደ እርሱ እንድንመለስ ይፈልጋል። በግለሰብ ደረጃ ያውቀናል። ያውቃችኋል።። ይወደናል። ሁልጊዜ ስለእኛ ያውቃል እናም እንደማይገባን ሲሰማን እንኳን ይባርከናል። ምን እንደምንፈልግ እና መቼ እንደሚያስፈልገን ያውቃል።

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል፤

“የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፣ እናም የሚፈልግም ያገኛል፤ እናም ለሚያንኳኩ ይከፈትላቸዋል።“ (ማቴዎስ 7፥7–8)።

ስለክህነት አሁን ምስክርነት ከሌላችሁ፣ እንድትጸልዩ እና ራሳችሁ ሃይሉን ማወቅ ትችሉ ዘንድ እንድትጠይቁ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቃላት ለመስማት ቅዱሳት መጽሃፍትን እንድታነቡ አበረታታችኋለሁ። የእግዚአብሔርን የክህነት ሃይል በህይወታችን ለመለማመድ ጥረት ብናደርግ አንደምንባረክ አውቃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ኒል ኤል. አንደርሰን፣ ““ሃይል በክህነት ስልጣን ውስጥ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013(እ.ኤ.አ)፣ 92።

  2. ሮበርት ዲ. ሄልስ፣ “የክህነት በረከቶች፣” ኤንዛይን ህዳር 1995(እ.ኤ.አ)፣ 32።