አጠቃላይ ጉባኤ
የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈጸም መቀናጀት
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈጸም መቀናጀት

መለኮታዊ ችሎታችንን ለማሟላት በጣም ውጤታማው መንገድ በክህነት ሀይል እና ስልጣን በመባረክ ተባብሮ መስራት ነው።

ውድ ግሩም እህቶቼ እና ወንድሞቼ፣ ከእናንተ ጋር መሆን አስደሳች ነው፡፡ ከየትም ሆናችሁ ብትሰሙ፣ ለእህቶቼ እቅፍን እና ለወንድሞቼ ከልብ የመነጨ ሰላምታን እሰጣለሁ፡፡ በጌታ ስራ ተባብረናል።

ስለ አዳምና ሔዋን ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ የመጀመሪያ ሃሳባችን በኤደን ገነት ውስጥ አስደሳች ስለሆነው ሕይወት ነው፡፡ የአየሩ ሁኔታ ሁሌም ቢሆን ፍጹም—በጣም ሞቃት እና በጣም ቀዝቃዛ እንዳልሆነ አስባለሁ—እናም ብዙ፣ ጣፋጭ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች በፈለጉት ጊዜ መብላት በሚችሉበት አካባቢ ያድጋሉ፡፡ ይህ ለእነሱ አዲስ ዓለም በመሆኑ፣ ብዙ ነገሮችን መማር ነበረባቸው፣ ስለሆነም ከእንስሳዎች ህይወት ጋር ሲገናኙ እና ቆንጆ አካባቢያቸውን ሲመለከቱ በየቀኑ አስደሳች ነበር፡፡ እነሱ ደግሞ እንዲከተሉ ትዕዛዛት ተሰጥቷቸው ነበር እናም እነዚያ መመሪያዎችን ለመቅረብ የተለያዩ መንገዶች ነበሯቸው፣ ይህም በመጀመሪያ የመነሻ ጭንቀት እና ግራ መጋባት አስከትሏል።1 ነገር ግን ህይወታቸውን ለዘላለም የሚቀይሩ ውሳኔዎችን ሲያደርጉ አብረው መሥራትን ተምረዋል እናም እግዚአብሔር ለእነሱ እና ለሁሉም ለልጆቹ ያለውን ዓላማ ለማሳካት አንድ ሆነዋል፡፡

አሁን እነዚህን ጥንዶች በሟችነት ህይወት በዓይነ ሕሊናችሁ ተመልከቱ። ለምግባቸው ጠንክረው መሥራት ነበረባቸው፣ አንዳንዶቹ እንስሳት እነርሱን እንደ ምግብ ይቆጥሯቸው ነበር፣ እንዲሁም አብረው ሲመክሩ እና ሲፀልዩ ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ አስቸጋሪ ችግሮች ነበሩ፡፡ እነዚያን ተፈታታኝ ችግሮች ለመፍታት ቢያንስ በተለያዩ ጊዜዎች የሃሳብ ልዩነት በመካከላቸው መኖሩን አስባለሁ፡፡ ሆኖም፣ በውድቀት ጊዜ፣ ​​አንድነት እና ፍቅር አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበዋል። ከመለኮታዊ ምንጮች በተሰጣቸው ትምህርት፣ የመዳን እቅድን እና ዕቅዱ እንዲሠራ የሚያደርገውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መሰረታዊ መርሆዎች ተምረዋል። ምድራዊ ዓላማቸው እና ዘላለማዊ ግባቸው ተመሳሳይ መሆናቸውን ስለተገነዘቡ አብረው በፍቅር እና በጽድቅ ለመስራት በመማር እርካታ እና ስኬት አግኝተዋል።

ምስል
አዳም እና ሔዋን ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ

ልጆችን በወለዱ ጊዜ፣ አዳምና ሔዋን ከሰማያዊ መልእክተኞች የተማሩትን ለቤተሰቦቻቸው አስተማሩ፡፡ ልጆቻቸውም በዚህ ሕይወት ደስ የሚያሰኛቸውን እነዛን መሰረታዊ መርሆዎች እንዲገነዘቡ እና እንዲቀበሉ በመርዳት ላይ አተኩረው ነበር፣ እናም ችሎታቸውን ካሳደጉ እና ለእግዚአብሔር ታዛዥነታቸውን ካሳዩ በኋላ ወደ ሰማያዊ ወላጆቻቸው ይመለሳሉ። በሂደቱ ውስጥ አዳምና ሔዋን የጥንካሬ ልዩነታቸውን ማድነቅ ተምረዋል እናም በዘለአለማዊ ጉልህ ሥራቸው እርስ በርስ የሚደጋገፉ ነበሩ፡፡2

ምዕተ ዓመታት እና ከዚያም ሺህ ዓመት እየመጣ እና ሲሄድ፣ የወንዶች እና የሴቶች ምሪታዊ እና ተደጋጋፊ አስተዋጾዎች በተሳሳተ መረጃ እና አለመግባባት እየተሸፈኑ መጡ፡፡ በኤደን ገነት ውስጥ በእዚያ አስደናቂ መጀመሪያ ወቅት እና በአሁን ጊዜ መካከል ባላንጣችን ነፍሳችንን ለማሸነፍ በሚያደርገው ሙከራ ወንዶችና ሴቶችን ለመከፋፈል ባለው ግቡ በጣም ስኬታማ ነበር፡፡ ወንዶች እና ሴቶች የሚሰማቸውን አንድነት ሊያበላሽ ቢችል፣ ስለ መለኮታዊ ዋጋችን እና ቃል ኪዳናዊ ኃላፊነታችንን ግራ የሚያጋባ ከሆነ፣ የዘለአለም አስፈላጊ ክፍሎች የሆኑትን ቤተሰቦችን በማጥፋት እንደሚሳካለት ሉሲፈር ያውቃል።

የሰዎች እና የሴቶች ተፈጥሮአዊ ልዩነቶች ከእግዚአብሔር የተሰጡ እና እኩል ዋጋ ያላቸውን መሆኑን የዘላለማዊ እውነት በመደበቅ የበላይ ወይም የበታች የመሆን ስሜትን ለመፍጠር ሰይጣን እንደ ማነፃፀሪያ ያነሳሳል። በዚህም የመልካም አነቃቂነታቸው ያላቸውን ተጽእኖ ለመቀነስም የሴቶች በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ ውስጥ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ለማቃለል ሞክሯል፡፡ የእሱ ግብ አንዳቸው ሌላውን የሚደግፉበት እና ለአንድነት የሚያበረክቱትን ልዩ አስተዋፅኦ ከማክበር ይልቅ የሥልጣን ሽኩቻን በመካከላቸው ማበረታታት ነበር።

ስለዚህ፣ ባለፉት ዓመታት እና በዓለም ዙሪያ፣ መለኮታዊ እርስ በርስ የሚደጋገፉበት እና ግን የሴቶች እና የወንዶች የአስተዋጾ እና ሃላፊነት የመለየታቸው ግንዛቤ ሙሉ በሙሉ ጠፋ። በብዙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ያሉ ሴቶች ጎን ለጎን አጋር ከመሆን ይልቅ ለወንዶች ተገዥ ነበሩ፣ ተግባሮቻቸውም ወደ ጠባብ አመለካከት ብቻ ተወሰነ፡፡ በእነዚያ የጨለማ ጊዜያት የመንፈሳዊ እድገት ደረጃ ቀነሰ፤ በእርግጥ፣ የበላይነት ባህሎች በሰፈነበት አእምሮ እና ልቦች ያነሰ የመንፈሳዊ ብርሃን ሊገባ ይችል ነበር።

እግዚአብሄር አባት እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ 1820 (እ.አ.አ) ፀደይ መጀመሪያ ላይ በኒው ዮርክ ውስጥ በተቀደሰው ጫካ ውስጥ ለልጅ ጆሴፍ ስሚዝ ከተገለጹለት በኋላ የተመለሰው ወንጌል ብርሃን “ከፀሐይ ብሩህነት በላይ”3 አበራ። ያም ክስተት በዘመናችን ራእይ ከሰማይ እንዲዘንብ አስጀመረ፡፡ ዳግም ከተቋቋመው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ነገሮች ውስጥ አንዱ የእግዚአብሔር ክህነት ስልጣን ነው፡፡ መልሶ መቋቋሙ እየተገለጸ ሲሄድ፣ በእርሱ ቅዱስ ሥራ ፈቃድ እና መመሪያ ወንዶችና ሴቶች እንደ አጋሮች የመሥራት አስፈላጊነት ችሎታ እንደገና መገንዘብ ጀመሩ።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር መቋቋም

በ 1842 (እ.አ.አ)፣ የአዲሱ ያላደገው ቤተክርስቲያን ሴቶች ለሥራው የሚረዳ ቡድን ለማቋቋም ሲፈልጉ፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ስሚዝ “በክህነት ስር እንደ ክህነት ንድፍ ሆኖ”4እነሱን ለማደራጀት ተነሳሽነት ተሰምቶታል። እንዲህም አለ፣ “አሁን ቁልፉን በእግዚአብሄር ስም እሰጣችኋለሁ … —ይህ የተሻሉ ቀናት መጀመሪያ ነው፡፡”5 ያ ቁልፍም ከተሰጠ በኋላ፣ ለሴቶች የትምህርት፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ዕድሎች ቀስ በቀስ በዓለም ዙሪያ መስፋፋት ጀምረዋል፡፡6

ይህም የሴቶች መዋቅር፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ተብሎ የሚጠራው፣ ሌሎች የሴቶች ማህበር የሚስተካከለው የለም፣ ምክንያቱም በክህነት ስልጣን በነቢይ የተቋቋመ ይህ አዲስ የቤተክርስቲያኗ ድርጅት ለሴቶች ስልጣንን፣ ሀላፊነቶችን፣ እና በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ የአስተዳደር ቦታ እንጂ የተገነጠለ አይደለም።7

ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ዘመን እስከ ዘመናችን ድረስ የሁሉም ነገሮች ዳግም መመለስ ወንዶች እና ሴቶች መለኮታዊ ኃላፊነቶቻቸውን እንዲወጡ ለመርዳት የክህነት ስልጣን እና ሀይል አስፈላጊነት ላይ የእውቀት ብርሃን አምጥቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንድ የክህነት ቁልፎች ባለው መሪነት የተቀቡ ሴቶች በጥሪዎቻቸው ውስጥ በክህነት ስልጣን እንደሚሰሩ በቅርብ ጊዜ ተምረዋል።8

በጥቅምት ወር 2019 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት በቤተመቅደስ ውስጥ ቡራኬ ያላቸው ሴቶች የክህነት ሃይል በህይወታቸው እና በቤታቸው ውስጥ የገቡትን ቅዱስ ቃል ኪዳኖች እስከጠበቁ ድረስ እንደሚኖራቸው አስተምረዋል።9 እሳቸውም እንደገለጹት፣ “ሰማያት ልክ የክህነት ተሸካሚ ለሆኑት ወንዶች ክፍት እንደሚሆኑ ሁሉ የእግዚአእሔርን የቡራኬ ሀይል የተቀበሉ ለሴቶችም በተሰጣቸው የክህነት ቃልኪዳናቸው አማካይነት ለነርሱም ክፍት ነው። እናም እሳቸውም እያንዳንዱን እህት፣ “ቤተሰቦቻችሁን እና ሌሎችን የምትወዷቸውን ለመርዳት የአዳኙን ሀይል በነፃነት ወደናንተ እንድታመጡ”10በማለት አበረታቱ።

ይህ ለእናንተ እና ለኔ ምን ትርጉም አለው? የክህነት ስልጣን እና ሀይል መረዳታችን እንዴት ህይወታችንን ይለውጣል? ቁልፍ ከሆኑት ነገሮች መካከል አንዱ ሴቶችና ወንዶች አብረው ሲሠሩ ለየብቻ ከሚሰሩት በላይ ብዙ መሥራት እንደምንችል መገንዘብ ነው፡፡11 የእኛ ሚና ተፎካካሪ ከመሆን ይልቅ ተደጋጋፊ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሴቶች ለክህነት አገልግሎት የተሾሙ ባይሆኑም፣ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ሴቶች ቃል ኪዳኖቻቸውን ሲጠብቁ በክህነት ሀይል ይባረካሉ እናም ለጥሪ በሚቀቡበት ጊዜ በክህነት ስልጣን ይሰራሉ፡፡

በሚያምር በነሐሴ ቀን ውስጥ፣ የአሮን ክህነት እንደገና በተቋቋመበት በፔንስለቫኒያ ሃርመኒ ውስጥ በሚገኘው የጆርጅ እና የኤማ ስሚዝ እንደገና በታደሰው መኖሪያ ቤት ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን ጋር የመቀመጥ እድል አግኝቼ ነበር። በውይይታችን ውስጥ ፕሬዝዳንት ኔልሰን በዳግም መመለስ ውስጥ ሴቶች የተጫወቱትን ወሳኝ ሚና ተናገሩ፡፡

ፕሬዘደንት ኔልሰን፤ “ክህነት ዳግም ወደተመለሰበት ቦታ ስመጣ የማስታውሰው አንድ ነገር ቢኖር በዳግም መመለሱ ላይ ሴቶች ምን አስፈላጊ ሚና እንደነበራቸው ነው።

“ጆሴፍ መፅሐፈ ሞርሞንን ለመተርጎም ለመጀመሪያ ጊዜ በጀመረበት ጊዜ፣ ማን ነበር የሚፅፈው? እርሱ ትንሽ ጽፎ ነበር፣ ግን ብዙም አልጻፈም። ኤማ ለመርዳት ተቀላቀለች።

“እና ከዚያም ጆሴፍ በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ ቤታቸው አጠገብ ወደሚገኘው ጫካ ለመጸለይ እንዴት እንደሄደ አስባለሁ። የት ሄደ? ወደ ቅዱስ ጫካ ሄደ። ለምን ወደ እዛ ሄደ? ምክንያቱም እናቱ ለመጸለይ በምትፈልግበት ጊዜ የምትሄደው ወደ እዚያ ነበርና።

“እነዚያም በክህነት ዳግም መመለስ እና በቤተክርስቲያኗ ዳግም መመለስ ላይ ዋና ክፍል ከነበሯቸው ሴቶች ሁለቱ ነበሩ። ያለጥርጥርም፣ ባለቤቶቻችን በዛ ቀን እንደነበሩት በዚህም ቀን አስፈላጊ ናቸው ለማለት እንችላለን። በእርግጥም፣ ናቸው።”

እንደ ኤማ፣ ሉሲ እና ዮሴፍ፣ አንዳችን ከሌላው ለመማር ፈቃደኞች ስንሆን እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ለመሆን እና በዚያ መንገድ ሌሎችን ለመርዳት ስንል በጣም ውጤታማ እንሆናለን።

“ክህነት ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች የእግዚአብሔርን ልጆች ህይወት እንደሚባርክ ተምረናል። … በ[ቤተክርስቲያን] ጥሪ፣ በቤተመቅደስ ስነስርዓት፣ በቤተሰብ ግንኙነቶች፣ እና በግል አገልግሎት፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች እና ወንዶች በክህነት ሀይል እና ስልጣን ወደ ፊት ይሄዳሉ። የእግዚአብሔርን ስራ በሱ ሃይል ለማከናወን የወንዶች እና የሴቶች እርስ በእርስ መደጋገፍ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለተመለሰው ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ማእከላዊ ነው።”12

ለተሰጠን እና እንድናሟላ ለተጠራነው መለኮታዊ ስራ አንድነት አስፈላጊ ነው፣ ግን እንዲሁ አይከሰትም፡፡ እርስ በእርሱ ለመደማመጥ፣ የሌሎችን አመለካከት ለመረዳት እና ልምዶችን ለማካፈል በእውነት አብሮ ለመምከር ጥረት እና ጊዜ ይጠይቃል፤ ግን ሂደቱ የበለጠ በመንፈስ የተመሩ ውሳኔዎችን ያስከትላል። በቤትም ሆነ በቤተክርስቲያናችን ሃላፊነቶች፣ መለኮታዊ ችሎታችንን ለማሟላት በጣም ውጤታማው መንገድ ብንለያይም እንኳን እርስ በርስ በሚደጋገፍ ሚናችን በክህነት ሀይል እና ስልጣን ተባብሮ አብሮ መስራት ነው።

ይህ አጋርነት ዛሬ በቃል ኪዳን ሴቶች ሕይወት ውስጥ ምን ይመስላል? ምሳሌ ልስጣችሁ።

ምስል
ጥንዶች በባለ ሁለት ሰው ብስክሌት ላይ

አሊሰን እና ጆን ልዩ የሆነ አጋርነት ነበራቸው፡፡ በአጭር እና በረጅም ውድድር ላይ የባለ ሁለት ሰው ብስክሌት ላይ ነዱ፡፡ በዚያ ተሽከርካሪ ላይ በተሳካ ሁኔታ ለመወዳደር ሁለቱ አሽከርካሪዎች አንድ መሆን አለባቸው፡፡ በትክክለኛው ጊዜ በተመሳሳይ አቅጣጫ ዘንበል ማለት አለባቸው። አንዱ ሌላውን መብለጥ አይችልም፣ ግን በግልፅ መግባባት አለባቸው እና እያንዳንዱ የራሱን ወይም የበኩሉን ድርሻ ማከናወን አለበት፡፡ ከፊት ለፊት ያለው ካፒቴን ፍሬኑን እና መቼ መቆም እንዳለበት ይቆጣጠራል፡፡ አሽከርካሪው፣ ከጀርባ ያለው፣ ለሚሆነው ነገር ትኩረት መስጠት እና ወደ ሌሎች ብስክሌተኞች በጣም የሚቀራረቡ ከሆነ ትንሽ ቀዝቀዝ ማድረግ ወይም ዝግ ካሉ ተጨማሪ ኃይል ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ እድገታቸውን እና ግባቸውን ለማሳካት እርስ በእርሱ መደጋገፍ አለባቸው፡፡

አሊሰን አብራራች፣ “ለመጀመሪያ ትንሽ ጊዜ፣ በካፒቴን ቦታ ያለው ሰው መነሳት ሲያስፈልገን ‘ተነሳ’ እና መቆም ሲያስፈልግ ደግሞ ‘ቁም’ ይላል፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኃላ አሽከርካሪው ሰው ካፕቴኑ መቼ እንደሚነሳ ወይም ፍሬኑን መቼ እንደሚይዝ ተማረ፣ ምንም ቃላትም መናገር አያስፈልጉም፡፡ አንዳችን ሌላው እንዴት እንደሚሰራ ተረዳን እናም አንደኛው እየታገለ እንዳለ ማወቅ እና ከዚያ ሌላኛው ሸክሙን ለማንሳት ቻልን፡፡ በእውነቱ ሁሉም ነገር መተማመን እና አብሮ መስራት ነው።”13

ጆን እና አሊሰን ብስክሌታቸውን ሲነዱ ብቻ ሳይሆን በትዳራቸውም አንድ ሆነዋል፡፡ እያንዳንዳቸው ከየራሳቸው ይልቅ የሌላውን ደስታ ፈለጉ፡፡ አንዳቸው የሌላውን መልካም ጎን ይመለከቱ የነበረ ሲሆን በእሱ ወይም በእሷ ውስጥ ያሉትን መልካም ያልሆኑትን ለማሸነፍ ሠርተዋል። አንዱ አጋር ሲታገል ተራዎችን በመውሰድ መርተዋል እና አብልጠው ሰርተዋል፡፡ እያንዳንዳቸው የሌላውን አስተዋፅኦ ያደንቁ ነበር እናም ችሎታቸውን እና ሀብታቸውን በማጣመር ለችግሮቻቸው የተሻሉ መልሶችን አግኝተዋል። በእውነት ልክ እንደ ክርስቶስ በፍቅር እርስ በእርስ የተሳሰሩ ናቸው፡፡

በዚህ ዘመን በዙሪያችን በሚገኙት “ቅድሚያ ለኔ” በሚል መልእክቶች በተከበብንበት ወቅት በመለኮታዊ አንድነት ተባብሮ መስራት ወሳኝ ነው፡፡ ሴቶች ልዩ፣ መለኮታዊ ስጦታ አላቸው14 እናም ልዩ ሀላፊነቶች ተሰጥቷቸዋል፣ ግን እነዚህ ስጦታዎች እና ሀላፊነቶች ከወንዶች በላቀ ወይም ባነሰ መልኩ አስፈላጊ አይደሉም፡፡ እያንዳንዱ ልጆቹ መለኮታዊ አቅማቸውን ለማሟላት የተሻለ እድል ለመስጠት የሰማያዊ አባትን መለኮታዊ እቅድ ለማሟላትሁሉም ነገር የተነደፈ እና አስፈላጊ ነው።

ዛሬ “የእናታችን ሔዋን ድፍረትን እና ራዕይ ያላቸው ሴቶች፣”15 እንዲሁም ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ከወንድሞቻቸው ጋር የሚቀላቀሉትን እንፈልጋለን።16 ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ ሥራቸውን ሲያከናውኑ ሙሉ ኃላፊነቱ የነሱ ነው ከማለት ወይም እንደ አጋር “ከማስመሰል” ይልቅ ወንዶች እውነተኛ አጋሮች መሆን አለባቸው ፡፡ ሴቶች “ትክክለኛ እና አስፈላጊ ቦታቸውን” ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን፣”17 እንዲሁም ሁሉንም በራሳቸው ለማከናወን ከማሰባቸው ወይም ምን ማድረግ እንዳለባቸው እስኪነገራቸው ከማሰብ ይልቅ እንደ አጋር መራመድ አለባቸው፡፡18

ሴቶችን እንደ ወሳኝ ተሳታፊዎች ማየት “ስብዕናን” መፍጠር አይደለም፣ ነገር ግን የመሠረተ-እምነትን እውነት መረዳት ነው፡፡ ያንን ለማምጣት የሚያስችል ፕሮግራም ከማቋቋም ይልቅ፣ ሴቶችን ልክ እግዚአብሔር በሚያያቸው አይነት፣ በደህንነት እና ከፍ ከፍ ለመደረግ እንደ አስፈላጊ አጋሮች እንደሆኑ ለማየት በንቃት መስራት እንችላለን።

ዝግጁዎች ነን? ባህላዊ አድልዎችን በማሸነፍ እና በመሰረታዊ መሠረተ-ትምህርት ላይ የተመሠረተ መለኮታዊ መንገዶችን እና ልምዶችን ለመቀበል እንጥራለን? ፕሬዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለጌታ ዳግም መምጣት ዓለምን ለማዘጋጀት በዚህ ቅዱስ ሥራ ክንድ ለክንድ ተያይዘን እንድንራመድ ጋብዘውናል።”19 ይህንን ስናደርግ፣ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋፅኦ ለማድነቅ እንማራለን እናም መለኮታዊ ሚናችንን የምንፈጽምበትን ውጤታማነት ይጨምራል፡፡ ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡

እያንዳንዳችን ስራው ወደፊት እንዲሄድ ለማገዝ በጌታ ምሪት አንድ ለመሆን እንመርጥ። በምንወደው አዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ዘፍጥረት 3፥1–18ሙሴ 4፥1–19ተመልከቱ።

  2. ሙሴ 5፥1–12ተመልከቱ። እነዚህ ቁጥሮች የአዳምን እና የሔዋንን እውነተኛ አጋርነት ያስተምራሉ፤ አንድ ላይ ልጆች ነበሯቸው (ቁጥር 2)፤ ለራሳቸው እና ለቤተሰባቸው ለማቅረብ አብረው ሠርተዋል (ቁጥር 1)፤ አብረው ጸለዩ ((ቁጥር 4)፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ታዘዙ እንዲሁም አብረው መሥዋዕት አቀረቡ(ቁጥር 5)፣ ተማሩ (ቁጥር 46–11) እና ለልጆቻቸው አንድ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አስተማሩ (ቁጥር 12)።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥16

  4. ዮሴፍ ስሚዝ፣ በሣራ ኤም ኪምባል፣ “የህይወት ታሪክ፣ ” የሴቶች ተንታኝ፣ መስከረም 1፣ 1883(እ.ኤ.አ)፣ 51፤ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፤ ጆሴፍ ስሚዝ (2007)፣ 451 ተመልከቱ።

  5. ጆሴፍ ስሚዝ፣ በ “በናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ደቂቃዎች መጽሐፍ ውስጥ፣” 40፣ josephsmithpapers.org።

  6. ጆርጅ አልበርት ስሚዝ፣ “ለሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላት የሰጡት ንግግር” የሴቶች መረዳጃ ማህበር መጽሔት፣ ታህሳስ 1945(እ.ኤ.አ) 717 የሚለውን ይመልከቱ።

  7. ጆን ቴይለር፣ በናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ደቂቃዎች፣ ህዳር 17 ቀን 1842(እ.ኤ.አ)፣ በ churchhistorianspress.org ይመልከቱ። እንደ ኤሊያዛ አር ስኖው ገለጻ፣ ጆሴፍ ስሚዝ በተጨማሪ ሴቶች በቀደሙት ዘመናት ሴቶች መደበኛ በሆነ መልኩ የተደራጁ መሆናቸውን አስተምረዋል (ኤሊዛ አር. ስኖው ፣ “የሴቶች መረዳጃ ማህበር” ን ይመልከቱ) የዴዘሬት ዜና ሚያዚያ 22፣ 1868 (እ.አ.አ)፣ 1፤ እና ሴት ልጆች በእኔ መንግሥት ውስጥ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪክ እና ስራ 2011 (እ.አ.አ)]፣ 1–7)።

  8. ዳሊን ኤች ኦክስ “የክህነት ቁልፎች እና ስልጣንሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 49–52 ይመልከቱ።

  9. ራስል ኤም ኔልሰን “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 እ.ኤአ፣ 78፣79 ይመልከቱ፡፡

  10. ራስል ኤም. ኔልሰን፣መንፈሳዊ ሀብቶች፣” 77።

  11. “ነገር ግን በዳግም የተመለሰው ወንጌል ባሎች እና ሚስቶች እርስ በራስ የመደጋገፍን ዘላለማዊ ሃሳብን ያስተምራል። እነርሱ እኩል ናቸው። እነሱ አጋር ናቸው “(ብሩስ አር. እና ማሪ ኬ.ሄፈን፣ “ድንበር ማቋረጥ እና እኩል አጋር መሆን፣” ኤንዛይን፣ ነሃሴ 2007 (እ.አ.አ)፣ 28)።

  12. የወንጌል ርዕሰ ጉዳዮች፣ “የዮሴፍ ስሚዝ ትምህርቶች ስለ ክህነት፣ ቤተመቅደስ እና ሴቶች፣” topics.ChurchofJesusChrist.org.

  13. የግል ደብዳቤ።

  14. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 95–97 ይመልከቱ።

  15. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” 97።

  16. ጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል 1.4፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

  17. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” 97።

  18. “ውድ እህቶቼ፣ ጥሪያችሁ ምንም ይሁን፣ ሁኔታዎቻችሁ ምንም ይሁኑ፣ የእናንተ ስሜትን፣ የእናንተ መረዳትን፣ የእናንተን መነሳሳት እኛ እንፈልጋለን። በአጥቢያ እና የካስማ መማክርቶች ድምፃችሁን ከፍ እንድታደርጉ እና እንድታሰሙ እንፈልጋለን። ያገባችሁ እህቶች ሁሉ ቤተሰባችሁን በመምራት ከባላችሁ ጋር አንድ ስትሆኑ ‘አስተዋፅኦ እናዳላችሁ እና እንደ ሙሉ አጋር’ እንድትናገሩ እንፈልጋለን። ያገባችሁ ወይም ያላገባችሁ ብትሆኑ፣ እናንተ እህቶች እንደ ስጦታ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት የተለዩ ችሎታዎች እና ልዩ የማስተዋል ብቃትን ተላብሳችኋል። እኛ ወንድሞች የእናንተን ልዩ አስተዋፅኦ ልናፈራ አንችልም። …

    “… ጥንካሬያችሁን እንፈልጋለን!” (ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” 97)።

  19. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” 97።