አጠቃላይ ጉባኤ
እሱ ከፊታችን ይሄዳል
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


እሱ ከፊታችን ይሄዳል

ጌታ የወንጌሉን እና የቤተክርስቲያኑን ዳግም መመልስ እየመራ ነው። እርሱ የወደፊቱን በትክክል ያውቃል። ወደስራው ይጋብዛቸኋል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን ጉባኤ ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። በዚህ የመጨረሻ ዘመን ጌታ ቤተክርስቲያኑን መልሶ ማቋቋሙን በሚመለከትበት መንገድ ላይ እንድናስብ በጋበዙን ጥሪ ላይ ፕሬዝዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እኛንና የምንወዳቸውን ባርከዋል፣ እነዚህም ተሞክሮዎች የማይረሱ ብቻ ሳይሆኑ የሚታወሱ መሆናቸውንም ቃል ገብተዋል።

የእኔ ተሞክሮ የማይረሳ ነው፤ የእርስዎም ተሞክሮ የማይረሳ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። የማይረሳ የመሆኑና ያለመሆኑ ሁኔታ በያንዳንዳችን ላይ የተመካ ነው። ያ ለእኔ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የዚህ ስብሰባ ዝግጅት ልምምድ እኔን እንዲዘልቅልኝ በምፈልገው መንገድ ለውጦኛል። ላብራራ።

የእኔ ዝግጅት በዳግም መመለስ ወቅት ወደነበረ አንድ መዝገብ ወሰደኝ። ስለዚህ ክስተት ብዙ ጊዜ አንብቢያለሁ፤ ነገር ግን ይህ ሁል ጊዜ ለእኔ የመሰለኝ የመልሶ መቋቋም ነብይ ስለሆነው ስለጆሴፍ ስሚዝ የሚናገር የአንድ ጠቃሚ ስብሰባ ዘገባ ነበር። ነገር ግን በዚህ ጊዜ፣ ጌታ እኛን ደቀመዛሙርቱን በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንዴት እንደሚመራን ከዘገባው አየሁ። ሁሉን ነገር፣ ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን በሚያውቀው በአለም አዳኝ በፈጣሪ መመራት ማለት ለእኛ ለሟቾች ምን ማለት እንደሆነ አየሁ። ደረጃ በደረጃ ያስተምረናል፤ ከቶም አያስገድደንም።

እየገለጽኩት ያለሁት ስብሰባ በመልሶ ማቋቋሙ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ወቅት ነበር። ሚያዚያ 3፣ 1836(እ.አ.አ) ኦሃዮ በሚገኘው የከርትላንድ ቤትመቅደስ ውስጥ ቤተመቅደሱ ከተመረቀ ከሰባት ቀናት በኋላ የሰንበት ቀን ስብሰባ የሚካሄድበት ነበር። በዓለም ታሪክ ውስጥ የነበረውን ይህንን ታላቅ ወቅት ጆሴፍ ስሚዝ በቀላል መንገድ ገልጾታል። አብዛኛዎቹ ዘገባዎች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 110 ውስጥ ተመዝግበዋል።

“በዚህ ረፋድ ቀን የጌታን እራት በቅዱስ ጠረጴዛው ላይ ለማስተዳደር ልዩ መብት ከነበራቸው ከአስራ ሁለቱ በመቀበል ለቤተክርስቲያን ለማደል ሌሎቹን ፕሬዘደንቶች ረዳሁ። ይህን አገልግሎት ለወንድሞቼ ካከናወንኩ በኋላ ወደ መስበኪያው ተመለስኩኝ፤ መጋረጃው በመዘጋቱ ከኦሊቨር ካውድሪ ጋር በአክብሮት እና ጸጥተኛ ጸሎት አጎነበስኩኝ። ከጸሎት ከተነሳሁም በኋላ የሚቀጥለው ራዕይ ለሁለታችን ተከፈተልን።”1

መጋረጃው ከአዕምሮዎቻችን ተወገደ እና የመረዳት አይኖቻችንም ተከፈቱ።

“ጌታን በመስበኪያው መደገፊያ ላይም በፊት ለፊታችን አየነው እና ከእግሮቹም በታች የቡናማ ቢጫ ቀለም አይነት የነበረ ንጹህ ወርቅ የተነጠፈበት የሚመስል ስራ ነበር።

ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ የራሱ ጠጕርም እንደ ንጹህ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ፊቱም ከብርቱ የጸሀይ ብርሀን በላይ የሚያበራ ነበር፤ ድምፁም እንዲህ የሚል እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ እንዲሁም የያህዌህ ድምፅ ነበር፣ እንዲህ አለ፤

“እኔ ፊተኛውና ኋለኛው ነኝ፤ እኔ ህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ፤ እኔም በአብ ዘንድ ጠበቃችሁ ነኝ።

እነሆ፣ ኃጢአታችሁ ተሰርየዋል፤ በፊቴም ንጹህ ናችሁ፤ ስለዚህም፣ ራሳችሁን አቅኑ እናም ተደሰቱ።

የወንድሞቻችሁ ልብም ደስ ይበለው፣ እና በሀይላቸው ይህን ቤት በስሜ የሰሩት የህዝቤም ልብ ሁሉ ደስ ይበለው።

“እነሆ፣ ይህን ቤት ተቀብዬዋለሁ፣ እና ስሜም በዚህ ይሆናል፤ እና በምህረትም ራሴን ለህዝቤ አሳያለሁና።

“አዎን ህዝቤ ትእዛዛቴን ቢጠብቁ እና ይህን ቅዱስ ቤት ባያጎድፉ ለአገልጋዮቼ እገለጣለሁ እና በራሴም ድምፅ አናገራቸዋለሁ።

“አዎን በሚፈሱት በረከቶች እና አገልጋዮቼ በዚህ ቤት ውስጥ በተቀበሉት መንፈሳዊ ስጦታዎች ምክንያት የሺዎች እና የአስር ሺዎች ልብ በእጅጉ ይደሰታሉ።

“እና የዚህ ቤት ዝናም በውጪ አገሮች ይስፋፋል፤ እና ይህም በህዝቤ ራሶች ላይ የሚፈሰው የበረከት መጀመሪያም ነው። እንዲሁም ይሁን። አሜን።

ይህ ራዕይ ከተፈጸመ በኋላ ሰማያት ዳግም ተከፈቱልን፤ እና ሙሴ በፊታችን መጣ እና ከምድር አራት ማዕዘናት የእስራኤልን መሰብሰቢያ እና ከሰሜን ምድር የአስሩን ነገዶች መምሪያ ቁልፎችን ሰጠን።

“ከዚህ በኋላ ኤልያስ መጣ እና በእኛና በዘራችን ከእኛም በኋላ የሚመጡ ትውልዶች ሁሉ ይባረካሉ በማለት የአብርሐም ወንጌል የዘመን ፍጻሜን ሰጠን።

“ይህ ራዕይ ከተፈጸመ በኋላ ሌላ ታላቅ እና የክብር ራዕይ ተከፈተልን፤ ሞትን ሳይቀምስ ወደሰማይ የተወሰደው ነቢዩ ኤልያስ በፊት ለፊታችን ቆመና እንዲህ አለ፥

እነሆ በሚልክያስ አንደበት በመመስከር ተነግሮ የነበረው ጊዜ በሙላት መጥቷል—ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ እርሱ [ኤልያስ] እንደሚላክ—

“ይህም ምድር በእርግማን እንዳትመታ፣ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ለመመለስ።

“ስለዚህ፣ የዚህ የዘመን ቁልፎች በእጆቻችሁ ተሰጥተዋል፤ እና ይህም ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ቅርብ እንደሆነ፣ እንዲሁም በበር ላይ እንዳለም፣ ታውቃላችሁ።2

አሁን ያንን ታሪክ ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ። ታሪኩ እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ አረጋግጦልኛል። ነገር ግን ለዚህ ስብሰባ ለመዘጋጀት ሳጠና እና ስጸልይ ጌታ በስራው ውስጥ ደቀመዛሙርቱን በዝርዝር የመምራት ሀይልን የበለጠ በግልጽ ለማየት ቻልኩ።

ሙሴ በከርትላንድ ቤተ መቅደስ እስራኤልን የመሰብሰብ ቁልፎች ለጆሴፍ ከማስተላለፉ ከሰባት ዓመት በፊት “ጆሴፍ ከመጽሃፈ ሞርሞን የአርእስት ገጾች ‘ለቀሪዎቹ የእስራኤል ቤት … ለዘላለም እንዳይጣሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳኖች እንዲያውቁ ማሳየት አላማው እንደነበር አወቀ።‘ በ1831(እ.ኤ.አ.) ጌታ እስራኤልን መሰብሰብ በከርትላንድ እንደሚጀምር ለዮሴፍ ነገረው፤ እናም ከዚያ ስፍራ ፍቃዴ የሆነላቸው በሁሉም ሀዝብ መካከል ይሄዳሉ…እስራኤልም ትድናለችና ና ወደምፈልግበት ስፍራ እመራቸዋለሁ’”3

እስራኤልን ለመሰብሰብ የሚስዮናዊ ስራ ያስፈልግ የነበረ ቢሆንም ቀዳሚ ሚስዮናውያን የሆኑትን የተወሰኑትን አስራ ሁለቱን “አስታውሱ የቤተመቅደስ በረከቶችን እስክትቀበሉ ድረስ ወደ ሌሎቸ አገራት እንዳትሄዱ ”ሲል አስተማራቸው።”4

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ቢያንስ ለሁለት ምክንያቶች በጌታ የደረጃ-በደረጃ እቅድ ውስጥ አስፈላጊ የነበረ ይመስላል፤ በመጀመሪያ ሙሴ የእስራኤልን መሰብሰቢያ ቁልፎች ዳግም ለመመለስ ቤተመቅደሱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጠበቀ። እና ሁለተኛ ጌታ “የስልጣንን ቁልፎች ለመግለጥ እና ሐዋርያት የቤተመቅደስ ቡራኬን የሚቀበሉበት እና የወይን ቦታውን ለመጨረሻ ጊዜ ለመግረዝ ለመዘጋጀት ቤተመቅደስ (የከርትላንድ ቤተመቅደስን) ቅዱሳን እንዲገነቡ አዞዋቸዋል። ” ሲሉ አስተምረዋል ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ።5 ምንም እንኳን እኛ ዛሬ እንደምናውቀው የቤተመቅደስ ቡራኬ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ያልተሰጠ ቢሆንም ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ወደ ሚስዮን የተጠሩትን በሚስዮናዊ አገልግሎት ወደ ታላቅ መሰብሰብ ወዳመራው ከመንፈሳዊ መገለጥ መፍሰስ ጋር ቃል በተገባው “ከላይ በመጣ ሃይል“6 ቡራኬ በማስታጠቅ የዝግጅት የቤተመቅደስ ስርዓቶች እዚያ መሰጠት ጀመሩ።

የእስራኤል መሰብሰቢያ ቁልፎች ለጆሴፍ ከተሰጡ በኋላ የአስራ ሁለቱን አባላት ወደሚስዮናዊ አገልግሎት እንዲልክ ጌታ ነቢዩን አነሳሳው። በጥናት ላይ ሳለሁ ሰዎች አስራ ሁለቱን ሊያምኑዋችው እና ሊደግፉዋችው ወደሚችሉባችው ሚስዮን የሚሄዱበትን መንገድ ጌታ በዝርዝር አዘጋጅቶ እንደነበረ ለእኔ ግልፅ ሆነልኝ። በጊዜ ሂደት በእነሱ አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ ወደተመለሰው የጌታ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ።

እንደ መዛግብቶቻችን ዘገባ ከሆነ ከ7,500 እስከ 8,000 የሚሆኑ በነዚህ ሁለት የአስራ ሁለቱ የብሪቲሽ ደሴቶች ሚስዮናዊ ጉዞዎች እንደተጠመቁ ይገመታል። ይህም በአውሮፓ ለሚስዮናዊነት ሥራ መሠረት ጥሏል፡፡ በ19ነኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ብዙዎቹ ከብሪቲሽ ደሴቶች እና ከስካንዲኔቪያ የመጡ 90,000 ያህል የሚሆኑ ወደ አሜሪካ ተሰብስበው ነበር።7 ጌታ ጆሴፍን እና ከአቅማቸው በላይ የሚመስለውን መከር ለማግኘት የሄዱትን እነዛን ታማኝ ሚስዮናውያን አነሳስቷቸው ነበር። ነገር ግን ጌታ በፍጹም የወደፊቱን የመመልከት ችሎታው እና ዝግጅቱ እውን አድርጎታል።

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 110 የሚገኘውን ግልፅ እና ግጥማዊ ቋንቋ ታስታውሳላችሁ፤

“እነሆ በሚልክያስ አንደበት በመመስከር ተነግሮ የነበረው ጊዜ በሙላት መጥቷል—ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ እርሱ [ኤልያስ] እንደሚላክ—

“ይህም ምድር በእርግማን እንዳትመታ፣ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ለመመለስ።

”ስለዚህ፣ የዚህ የዘመን ፍጻሜ ቁልፎች በእጆቻችሁ ተሰጥተዋል፤ እና ይህም ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ቅርብ እንደሆነ፣ እንዲሁም በበር ላይ እንዳለም፣ ታውቃላችሁ።”8

ጌታ የሩቅ የወደፊቱን እንዳየ እንዲሁም በመጨረሻዎቹ ቀናት ዓላማዎቹን እንዲፈጽም እንዴት እንደምንረዳው እንደሚመራን እመሰክራለሁ።

ከብዙ አመታት በፊት በኤጲስ ቆጶስነት እያገለገልኩ በነበረበት ወቅት FamilySearch ብለን የሰየምነውን የፈጠረውን የንድፍ እና የልማት ቡድን በበላይነት እንድቆጣጠር ታዘዤ ነበር። እኔ “መራሁት” ከማለት ይልቅ ፈጠራውን “በበላይነት ተመለከትኩት” በማለት እጠነቀቃለሁ። ብዙ ባለብሩህ አእምሮ ሰዎች ሌሎች ስራዎችን ትተው ጌታ የሚፈልገውን ለመገንባት መጡ።

የቀዳሚ አመራሩ የስርአቶች መደጋገምን ለመቀነስ ግብ አውጥተው ነበር። የእነሱ ዋና ጉዳይ የግለሰቦች ስርዓቶች ተከናውነው እንደነበረ ማወቅ አለመቻላችን ነበር። ለአመታት—ወይም ዓመታት ለሚመስሉ ጊዜያት—የቀዳሚ አመራሩ “ተሰርቶ እንዲጨረስ የምታደርገው መቼ ነው ?” ሲሉ ጠየቀውኛል።

በጸሎት፣ በትጋት እና ከፍተኛ ችሎታ ባላቸው ሰዎች የግል መስዋትነት ስራው ተጠናቀቀ። ይህም ደረጃ በደረጃ መጣ። የመጀመሪያው ሥራ በኮምፒተር መስራት ለማይመቻቸው FamilySearchን ለተጠቃሚዎች ተስማሚ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ተጨማሪ ለውጦች መጡ፣ መምጣታቸውን እንደሚቀጥሉ አውቃለሁ ምክንያቱም አንድ በመንፈስ መሪነት የታየ ችግርን ለመፍታት በጀመርን ቁጥር ቢያንስ በእኩል ደረጃ አስፈላጊ ለሆኑ ነገር ግን ገና እይታ ውስጥ ላልገቡ እድገቶች ለበለጠ መገለጥ በር እንከፍታለን። ዛሬው ቢሆን FamilySearch ጌታ ለዳግም መመለሱ አንድ ክፍል የሚፈልገው አካል እየሆነ ነው — እናም የስርዓቶች መደጋገምን ለማስቀረት ብቻም አይደለም።

ሰዎች አያቶቻቸውን የማወቅ ስሜት እንዲኖራቸው እንዲሁም ፍቅርም እንዲኖራቸው እና የቤተመቅደስ ስርዓታችውን እንዲያከናውኑ ጌታ ማሻሻያዎችን እንድናደርግ ያደርገናል። አሁን ወጣቶች ለወላጆቻቸው እና ለአጥቢያ አባሎቻቸው የኮምፒተር አማካሪዎች እንደሚሆኑ ጌታ በእርግጥ ያውቅ ነበር። በዚህ አገልግሎት ሁሉም ታላቅ ደስታ አግኝተዋል።

የኤልያስ መንፈስ የወጣትን እና የአዛውንትን፣ የልጆችንና የወላጆችን፣ የልጅ ልጆችን እና የቅድመ አያቶችን ልብ እየለወጠ ነው። ቤተመቅደሶች የጥምቀት እድሎችን እና ሌሎች የተቀደሱ ስርዓቶችን ለማከናወን በደስታ ቀጠሮ የሚይዙ ይሆናሉ። የቀድሞ አባቶቻችንን የማገልገል እና ወላጆችን እና ልጆችን የማስተሳሰር ፍላጎት እያደገ ነው።

ጌታ ይህ ሁሉ እንደሚመጣ አይቷል። በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንዳደረጋቸው ሌሎች ለውጦች ለእሱም በደረጃ በደረጃ አቅዶ ነበር። ከባድ ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ ለመስራት የሚመርጡ ታማኝ ሰዎችን አስነስቷል እንዲሁም አዘጋጀቷል። “በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርአት ላይ ስርአት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” እንድንማር ሊረዳን ሁል ጊዜ በፍቅር ተነሳስቶ ይታገሳል።”9 እርሱ እቅዱን ሊያከናውን የሚፈልግበት ጊዜ ዝንፍ አይልም ሆኖም መስዋትነት ብዙ ጊዜ እኛ ያልጠበቅነውን በረከት እንደሚያመጣ ያረጋግጣል፡፡

ለዚህ ጉባኤ ለመዘጋጀት መስዋእትነት እንድከፍል ፕሬዘዳንት ኔልሰን እንዲጋብዙኝ ላነሳሳው ለጌታ ምስጋናዬን በመግለጽ እዘጋለሁ። በዝግጅቴ ወቅት እያንዳንዱ ሰዓት እና እያንዳንዱ ጸሎት አንድ በረከት ያመጣ ነበር።

ይህንን መልእክት የሚሰሙትን ወይም እነዚህን ቃላት የሚያነቡትን ሁሉ ጌታ የወንጌሉን እና የቤተክርስቲያኑን ዳግም መመለስ እየመራ እንደሆነ እምነት እንዲኖራቸው እጋብዛለሁ። እርሱ ከፊታችን ይሄዳል። እርሱ የወደፊቱን በትክክል ያውቀዋል። ወደስራው ይጋብዛቸኋል። በውስጡም ይቀላቀላል። ለአገልግሎታችሁ እቅድ አለው። እናም መስዋእትነት በምትከፍሉበት ጊዜም እንኳ ሌሎች ለሱ ዳግም መምጣት እንዲዘጋጁ እንዲነሱ በመርዳት ደስታ ይሰማችኋል።

እግዜአብሄር አብ ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። እናንተን ያውቃችኋል እናም ያፈቅራችኋል። ይመራችኋል። ለእናንተ መንገዱን አዘጋጅቷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።