አጠቃላይ ጉባኤ
ክህነት ወጣትነትን እንዴት ይባርካል
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


ክህነት ወጣትነትን እንዴት ይባርካል

ልክ እንደ መላእክት የማገልገል፣ በሁሉም የምድር አህጉራት ወንጌልን የመስበክ እና ነፍሳት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ የመርዳት እድል ተሰጠን።

ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ ታሪካዊ ምሽት ስለ ክህነት አገልግሎት ስጦታው እና በዚህ ወቅት ወጣቶችን ለመባረክ ስላለው አስደናቂ ኃይል እናገራለሁ። ፍጹምነት የጎደለኝ ቢሆንም፣ መንፈስ ቅዱስ በማስተማር እንዲረዳኝ እፀልያለሁ።

የቀዳሚ አመራር የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች እንዲህ እንዲያስታወሱ አድርገዋል፣ “እናንተ የምትኖሩት ክህነት በተመለሰበት፣ በታላቅ ዕድሎች እና ፈተናዎች ቀን ውስጥ ነው። የአሮን ክህነት ስርዓቶችን የማስተዳደር ስልጣን አላችሁ። በጸሎት እና በትክክል ይህንን ስልጣን ስትጠቀሙ፣ በአካባቢያችሁ ያሉትን ሰዎች ሕይወት በእጅጉ ትባርካላችሁ።”1 እንደ ቤተክርስቲያኗ ወጣት ወንዶች፣ እኛም “የተወደድን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ እናም እርሱ እኛ የምንሠራው አንድ ሥራ አለው” የሚል ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል፣2 እናም “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ለማምጣት” ስራው ውስጥ እንረዳለን (ሙሴ 1፥39)።

ክህነት የአዳኙን ወንጌል ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ለመቀበል ብቁ ለሆኑት የማስተዳደሪያ ስልጣን ነው። በእነዚህ የክህነት ስርዓቶች እና ቅዱስ ቃል ኪዳኖች መለኮታዊ እጣ ፈንታችንን እንድንደርስ የሚረዳን የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ሙሉ በረከቶች ይመጣሉ።

ዮሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንደገና እንዲመልስ በእግዚአብሔር የተጠራ ወጣት ነበር፣ እና ለዚሁ አላማ መላውን የሰው ዘር ለመባረክ የሚጠቀም ክህነት ተሰጠው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135 ውስጥ፣ ዮሴፍ ለዚህ ዘመን ወጣቶች የሰጣቸውን በርካታ በረከቶች አብራራ። እናነባለን፤ “ዮሴፍ ስሚዝ፣ ከኢየሱስ በስተቀር፣ በዚህ አለም ውስጥ ለሰዎች ደህንነት ከኖሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ አድርጎታል። … መፅሐፈ ሞርሞንን አምጥቷል፣ … የዘለአለም ወንጌል ሙላት ወደ ምድር አራቱ ማዕዘናት ልኳል፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የተጻፉ መገለጦች እና ትእዛዛት አመጣ፣ … እና ብዙ ሺህ የኋለኛ ቀን ቅዱሳንን ሰብስቧል፣… ሊሞት የማይችል ታዋቂነትን እና ስምን ትቷል።” (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 135፥3)።

እንደ ዮሴፍ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማገልገል፣ የጌታን የክህነት ሀይል ለመጠቀም ብቁ መሆን አለብን። መፅሐፈ ሞርሞንን በሚተረጉሙበት ጊዜ ዮሴፍ እና ኦሊቨር ካውዲሪ ለመጠመቅ ፈለጉ፣ ነገር ግን ትክክለኛውን ስልጣን አጡ። በግንቦት 15 ቀን 1829 (እ.አ.አ) በጸሎት ተንበርክከው በመጥምቁ ዮሐንስ ተጎብኝተው ነበር፣ እርሱም የአሮናዊ ክህነት ቁልፍን እና ስልጣንን እንዲህ በማለት ሰጣቸው፣ “አገልጋይ ባልንጀሮቼ፣ የመላእክትን፣ እና የንስሀን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት ቁልፎች የያዘውን የአሮንን ክህነት በመሲሁ ስም ለእናንተ እሰጣችኋለሁ” (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13)።

ልክ እንደ መላእክት የማገልገል፣ በሁሉም የምድር አህጉራት ወንጌልን የመስበክ እና ነፍሳት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ የመርዳት እድል ተሰጠን። ይህ አገልግሎት ከመጥምቁ ዮሐንስ፣ ከሞሮኒ፣ ከጆሴፍ ስሚዝ፣ ከፕሬዚዳንት ኔልሰን እና ከሌሎች ትጉ የጌታ አገልጋዮች ጋር በጋራ እንድንሠራ ያደርገናል።

የእርሱ እና የክህነት አገልግሎታችን የጌታን ትምህርቶች በትክክል ለመከተል እና ለመኖር የወሰኑትን ወጣቶች ያመጣቸዋል፣ እኔ በግሌ የወጣትነትን ፈተናዎች ስንጋፈጥ ከባድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሥራውን ለማከናወን ከነዚህ ሌሎች የእግዚአብሔር ባሪያዎች ጋር መቀላቀል የጠላትን ፈተናዎችና ማታለያዎችን እንድንቋቋም ይረዳናል። ስለራሳቸው እርግጠኛ ላልሆኑ ሁሉ የብርሃን አምድ መሆን ትችላላችሁ። በውስጣችሁ ያለው ብርሃን በጣም ያበራል እናም አብረዋቹ የሚሳተፉ ሰዎች ሁሉ ካጠገባችሁ በመሆናቸው ይባረካሉ። የመንፈሳዊ ጓደኞቻችን መኖራቸውን ለመቀበል አንዳንድ ጊዜ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ወደ ክርስቶስ ይበልጥ ለመቀጠል የምችልበት የታማኝ የክህነት ቡድን አባል መሆኔን በማወቄ አመስጋኝ ነኝ።

ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰቦቻችን ጋር፣ መንፈስ ቅዱስ በጣም ታማኝ እና መመካት የሚቻልበት ጓደኞቻችን አንዱ ነው። ነገር ግን የእርሱን ቀጣይ ጓደኝነት ለመጋበዝ፣ እራሳችንን በተገኘባቸው ሁኔታዎች እና ቦታዎች ማስቀመጥ አለብን። በእለታዊ የቅዱስ መጻህፍት ጥናት እና በቤተሰብ ውስጥ ጸሎትን በመሳተፍ እና ከሁሉም በላይ፣ በግል ቅዱሳት መጻህፍትን በማጥናት እና በራሳችን ስንፀልይ ቅዱስ ቦታ ለማድረግ በመጣር ይህ በገዛ ቤታችን ውስጥ ሊጀመር ይችላል።

ምስል
ኤንዞ እና እህቱ
ምስል
ኤንዞ እና ቤተሰቡ

በዚህ አመት መጀመሪያ፣ ታናሽ እህቴን ኦሽንን ለማጥመቅ የቀረበውን ግብዣ በመቀበል እና ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ለማሟላት የቃል ኪዳኑን ጎዳና ላይ እድገት እንድረዳ አስደሳች እና የትህትና አጋጣሚ ተሰጠኝ። ይህንን ስነ-ስርዓት የማከናወን እድል አገኝ ዘንድ ቄስ ሆኜ እስክሾም ድረስ ለአንድ ወር ጥምቀቷን አስተላልፋለች፣ ሌሎቹ እህቶቻችንም እንዲሁ በክህነት ስራ ለመስራት እና እንደ ምስክሮች ሆነው ለመቆም እድል ተሰጣቸው። ከማጥመቂያው ተቃራኒ ጎኖች ላይ ቆመን እና ወደ ውሀው ለመግባት ስንዘጋጅ፣ እኔን የሚሰማኝን ያህል ደስታዋን አስተዋልኩ። እናም ትክክለኛውን ውሳኔ እያደረገች ስመለከት፣ ከእሷ ጋር አንድ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ይህ የክህነት ስልጣንን የመጠቀም አጋጣሚ በወንጌል አኗኗሬ የበለጠ ጠንቃቃ እና ግድየለሽነት መቀነስ አስፈልጎኛል። ለመዘጋጀት፣ በእዚያ ሳምንት በእናቴ፣ በአያቴ እና በእህቴ ድጋፍ ለሙታን ጥምቀት ለማከናወን ወደ ቤተመቅደስ እሄድ ነበር።

ይህ ተሞክሮ ስለ ክህነት እና እንዴት በተገቢ ሁኔታ መለማመድ እንዳለብኝ ብዙ አስተምሮኛል። “እንድሄድ እና እንዳደርግ” የኔፊን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ሁሉም የክህነት ተሸካሚዎች እኔ እንደተሰማኝ ዓይነት ስሜት ሊሰማቸው እንደሚችሉ አውቃለሁ ( 1 ኔፊ 3፥7)ተመልከቱ። በስራ ፈችነት ሁኔታ ላይ ተቀምጠን ጌታ በታላቅ ሥራው እኛን እንዲጠቀምብን መጠበቅ አንችልም። የእኛን እርዳታ የሚፈልጉት ወደኛ እስኪመጡ መጠበቅ የለብንም፤ እንደ የክህነት ተሸካሚዎች ምሳሌ መሆን እና እንደ የእግዚአብሔር ምስክሮች መቆም የእኛ ሀላፊነት ነው። ከዘላለማዊ እድገታችን የሚከለክሉ ውሳኔዎችን የምንወስን ከሆነ አሁን መለወጥ አለብን። ቀላል ነገሮችን በመፈለግ በሥጋዊ ሁኔታ ውስጥ እንድንሆን ለማድረግ ሰይጣን እጅግ በጣም ይሞክራል። ነገር ግን ጥረት ካደረግን፣ የሚደግፉንን ፈልገን ካገኘን፣ እና በየቀኑ ንስሐ ከገባን የበረከት ውጤቱ አስገራሚ እንደሚሆን እና ህይወታችንም በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ወደፊት በምንገፋበት ጊዜ ለዘላለም እንደሚለወጥ አውቃለሁ።

ይህች ቤተክርስቲያን አዳኛችን በሆነው እና በተለይ በዚህ አስቸጋሪ ቀናት እኛን ሊመሩን እና ዓለምን ለዳግም ምጣቱ እንዲያዘጋጁ ለሐዋርያቶቹ የክህነትን ቁልፎችን የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን እንደሆነች አውቃለው።

ዮሴፍ ስሚዝ የመልሶ መቋቋም ነብይ እንደነበር እና ፕሬዘደንት ኔልሰን ዛሬ ህያው ነቢያችን እንደሆኑ አውቃለሁ። እነዚህን ታላቅ የክህነት ተሸካሚዎች ህይወት እንድንመረምር እና ፈጣሪያችንን ለመገናኘት ዝግጁ እንድንሆን በየዕለቱ እራሳችንን እንድናሻሽል እጋብዛለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. የቀዳሚ አመራር፣ በ ለእግዚአብሔር ያለብኝን ግዴታ መወጣት (መጽሃፍ፣ 2010 (እ.አ.አ))፣ 5።

  2. የአሮናዊ የክህነት ቡድን ጭብጠ ሃሳብ፣ ጠቅላይ መምሪያ መጽሐፍ ውስጥ፤ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ 10.1.2፣ ChurchofJesusChrist.org።