አጠቃላይ ጉባኤ
ፍጹም ብሩህ ተስፋ
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


ፍጹም ብሩህ ተስፋ

ዳግም መመለስ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም እንደሚሰራ የመሠረታዊ እውነት ድጋሜ ስላረጋገጠ፣ በጣም ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚያስችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም እንኳ፣ ተስፋ ሊኖረን እንችላለን፣ ተስፋ ማድረግም አለብን።

ባለፈው ጥቅምት ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ዳግም መመለስ የእግዚአብሔርን እጅ ታላቅነት ለማየት እያንዳንዳችን ወደ ሚያዝያ 2020(እ.ኤ.አ) ጉባኤ እንድንመለከት ጋብዘውን ነበር። እህት ሆላንድ እና እኔ ያንን ትንቢታዊ ጥሪ በቁም ነገር ወሰድነው። የጊዜውን የሐይማኖት እምነቶች በመመልከት እራሳችንን (እ.አ.አ) በ1800ዎቹ ዘመን እንደሚኖሩ ሰዎች አሰብን። በዛ ምናባዊ ሁኔታ ውስጥ በመሆን እራሳችንን እንዲህ ብለን ጠየቅን፣ “ምንድን ነው እዚህ የጎደለው? ምን ቢኖረን ተመኘን? ለመንፈሳዊ ፍላጎታችን መልስ ለመስጠት እግዚአብሔር ይሰጠናል ብለን ምን ተስፋ እናደርጋለን?”

እናም፣ ለአንድ ነገር፣ ከሁለት ምእተ አመታት በፊት በመንፈሳዊ ትምህርት ስህተት እና የቤተ ክርስትያን የተሳሳተ መረዳት ጀርባ ለመቶ አመታት የተደበቀውን የበለጠ እውነት የሆነውን የእግዝአብሄር መረዳት እንዲመለስ በጊዜው ከነበሩት የበለጠ ተስፋ እናደርግ እንደነበረ ተገነዘብን። የዘመኑ ታዋቂ የሃይማኖት ሰው ከነበረው ከዊሊያም ኤሌሪ ቻኒንግ ሐረግ በመውሰድ፣ “የመጀመሪያው የክርስትና ታላቅ ትምህርት” ብሎ ያሰበውን “የእግዚአብሔርን የወላጅነት ባሕርይ ” እንፈልግ ነበር።”1 እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት አምላክን ከባድ ፍርድ የሚያስተላልፍ ሃይለኛ ዳኛ ወይም በመሬቱ እንደማይገኝ የመሬት ባለቤት በአንድ ወቅት በምድር ጉዳዮች ውስጥ ተሰማርቶ የነበረ ነገር ግን አሁን ላይ በአጥናፈ ሰማይ ውስጥ ሌላ ቦታ በሃሳብ ተይዞ እንዳለ አድርጎ ከማሰብ ይልቅ እንደ አሳቢ አባት ይቀበለው ነበር።

አዎን፣ በ1820 እ.ኤ.አ ተስፋችን እግዚአብሔርን ልክ እንደበፊቱ እንደ ትክክለኛ አባት አፍቃሪ በሆነ የቃሉ አገላለፅ በአሁን ጊዜ በግልፅ ሲናገር እና ሲመራ ማግኘት ነው። እሱ ፈጽሞ ጥቂት ሰዎችን ለማዳን አስቀድሞ ወስኖ የተቀረውን የሰው ልጅን ወደ ጥፋት የሚያመጣ ጨካኝ የዘፈቀደ አምባገነን አይደለም ። የለም፣ የእርሱ እያንዳንዱ እርምጃ፣ በመለኮታዊ መግለጫ “ለአለም ጥቅም፣” ይሆናል ምክንያቱም፣ “እርሱ ዓለምን ስለሚወድ” በእሷም የሚኖሩትን ሁሉ።2 ያም ፍቅር አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር ለመላክ የመጨረሻው ምክንያት ይሆናል።3

ስለ ኢየሱስ ስናውራ፣ በእነዚያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ ዓመታት ውስጥ ብንኖር ኖሮ፣ ስለ አዳኙ ህይወት እና የትንሳኤ እውነታዎች ጥርጣሬ በሕዝበ ክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ቦታ መያዝ መጀመሩን በታላቅ ፍርሃት እንረዳ ነበር። ስለዚህ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አልፋ እና ኦሜጋ፣ እንዲሁም ይህ ዓለም የምታውቀው ብቸኛ አዳኝ እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ማረጋገጫ ወደ ዓለም ሁሉ እንዲመጣ እንመኛለን። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ምስክርነትን የያዘ፣ ስለ ተአምራዊው ልደቱ፣ ስለ አስደናቂ አገልግሎቱ፣ ስለ ቤዛዊ መስዋእትነቱ እና ስለ ታላቁ ትንሣኤ እውቀታችንን የሚያሰፉና የሚጨምሩ ሌሎች የቅዱሳን መጻሕፍት ማስረጃዎች እንዲመጡ ልባዊ ተስፋዎቻችን መካከል ይሆን ነበር። በእውነቱ እንዲህ ዓይነቱ ሰነድ “ከሰማይ ወደ ምድር የተላከ ጽድቅ እና እውነት” ነው።4

የዚያን ቀን የክርስትናን ዓለም በመመልከት፣ የሚያጠምቀን፣ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታን የሚሰጥ እና ከፍ ለመደረግ የሚያስፈልጉትን የወንጌል ስርዓቶች ሁሉ የሚሰጠን ከእግዚአብሔር የሆነ እውነተኛ የክህነት ስልጣን ያለውን ሰው ለማግኘት ተስፋ እናደርግ ነበር። በ 1820 እ.ኤ.አ ግርማ ሞገስ የተላበሰውን የእግዚአብሔር ቤት መመለስን በተመለከተ የኢሳያስ፣ የሚክያስ እና የሌሎች የጥንት ነቢያት ቃል-ኪዳናዊ ተስፋዎች ሲፈጸሙ ለማየት ተስፋ እናደርግ ነበር።5 የተቀደሱ ቤተመቅደሶችን ክብር፣ ስርዓቶች፣ ዘላለማዊ እውነቶችን የማስተማር ሀይል እና ስልጣን፣ የግል ቁስሎችን ለመፈወስ እና ቤተሰቦችን ለዘላለም በአንድነት ለማሰር በመንፈስ እንደገና ሲቋቋሙ ማየት በመቻላችን እንደሰት ነበር። እኔን እና የምወዳት ፓትሪሻን በዚህ አይነት ቦታ ጋብቻችን ለጊዜው እና ለዘላለም የታተመ እንደሆነ የሚነግረንን ስልጣን ያለውን ሰው ለማግኘት የትም እፈልግ ነበር፤ “ሞት እስኪለያችሁ” የሚለውን አስፈሪ እርግማን እንዳያርፍብን ወይም ፈጽሞ ላለመስማት። “በአባታችን ቤት ውስጥ ብዙ መኖሪያ ቤቶች”6 እንዳሉ አውቃለሁ፣ ነገር ግን በግሌ ለመናገር፣ እኔ ከነዚያ አንዱን ለመውረስ በጣም ዕድለኛ ብሆን ነገር ግን ውርሱን ለመካፈል ፓት እና ልጆቻችን ከእኔ ጋር የማይኖሩ ከሆነ ያ ቦታ ለኔ እየበሰበሰ ካለ ጎጆ የተሻለ አይሆንም። እናም ለቅድመ አያቶቻችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እንኳን ሳይሰሙ ለቀደሙ እና ለሞቱት፣ እጅግ ፍትሃዊ እና በምህረት የተሞሉ የመጽሃፍ ቅዱስ ጽንሰ ሃሳቦች እንዲሁም በህይወት ያሉት ለሞቱት ዘመዶቻቸው የሚያደርጉት የማዳን ስርዓት እንዲመለስ ተስፋ እናደርግ ነበር።7 የትም ኖረው ቢሆን ወይም የትም ቢሞቱ የትኛውም ምድራዊ ልጆቹ ለሆኑት የአፍቃሪ እግዚአብሄር አሳቢነት በበለጠ ግርማ ሞገስ ለማሳየት እንደምችል መገመት እችላለሁ።

እንግዲህ፣ የእኛ የ1820 እ.ኤ.አ ተስፋዎች ዝርዝር ሊቀጥሉ ይችላሉ፣ ምናልባት የዳግም መመለስ በጣም አስፈላጊ መልዕክት እንደዚህ ያሉ ተስፋዎች በከንቱ እንዳልነበሩ ሊሆን ይችላል። ከቅዱሱ ጫካ ጀምሮ እና እስከዚህ ጊዜ ድረስ እነዚህ ምኞቶች በእውነት መሸፈን ጀመሩ እናም ሐዋሪያው ጳውሎስ እና ሌሎች እንዳስተማሩት፣ እርግጠኛ ለሆነው ለጽኑ እውነተኛ መልሕቆች ሆነዋል።8 በአንድ ወቅት ተስፋ የነበረው አሁን ታሪክ ሆኗል።

በዚህ ሁኔታ ለ200 አመታት እግዚአብሄር ለአለም የነበረውን ቸርነት ተመለከትን። ነገር ግን ስለ ወደፊቱ ምን አለ? እስካሁን ያልተፈጸሙ ተስፋዎች አሁንም አሉን። በዚህ ስንነጋገርም፣ በኮቪድ-19 በችታ ላይ ሁሉንም ያሳተፈ ጦርነት እያወጅን ነው፣ ይህም ከአሸዋ9 በ1000 ያህል ያነሰ የሆነው ቫይረስ10 ህዝቦችን እና የአለምን ኢኮኖሚ በሙሉ ለማንበርከክ እንደሚችል በትጋት እንድናስታውስ ያደርገናል። በዚህ ዘመነኛ ወረርሽኝ አማካኝነት የሚያፈቅሩትን ሰዎች ላጡ እና በወረርሽኙ ለተጠቁ ወይም አደጋ ላይ ላሉ ሁሉ እንጸልያለን። እንዲህ ዓይነቱን አስደናቂ የጤና እንክብካቤ ለሚሰጡት ሁሉ በእርግጥ እንጸልያለን። ይህንን ወረርስሽኝ ስናሸንፈው—እንደምናሸንፈው ጥርጥር የለንም—ዓለምን ከረሃብ ቫይረስ እና ጎረቤቶችን እና ሃገራትን ከድህነት ቫይረስ ነፃ ለማድረግ በእኩልነት ቆርጠን እንነሳ። ተማሪዎች በጥይት ይገደላሉ ተብሎ ሳይሆን፣ ተማሪዎች ለሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች እና ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅም በጎሳ ወይም ሐይማኖታዊ ጭፍን ጥላቻ ያሌለው የግል ክብር ስጦታ እንዲኖራቸው ደግሞም ተስፋ አለን። በሁሉም መሰረት ሆኖም፣ ለሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት ሁሉ የሚበልጠው አምልኮት እንዲኖር ተስፋ አለን፥ ምክሩን በመጠበቅ እግዚአብሔርን ማፍቀር እና ደግነት እና ርህራሄን፣ ትዕግሥት እና ይቅርታን በማሳየት ባለንጀራችንን መውደድ።11 እነዚህ ሁለት መለኮታዊ መመሪያዎች አሁንም እና ለዘላለም ለልጆቻችን አሁን ከሚያውቁት የተሻለ ዓለም ለመስጠት ያለን ብቸኛ እውነተኛ ተስፋ ይሆናሉ።12

ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ምኞቶች በተጨማሪ፣ ዛሬ ብዙ አድማጮች ጥልቅ የግል ተስፋዎች አሏቸው፤ ጋብቻ እንዲሻሻል ተስፋ ማድረግ፣ ወይም አንዳንድ ጊዜ ለትዳር ተስፋ ማድረግ፣ ሱስ የማሸነፍ ተስፋ፤ ዓመፀኛ ልጅ ተመልሶ ይመጣ ዘንድ ተስፋ ማድረግ፣ መቶ ዓይነት አካላዊ እና ስሜታዊ ሥቃይ እንዲቆም ተስፋ ማድረግ። ዳግም መመለስ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም እንደሚሰራ የመሠረታዊ እውነት ድጋሜ ስላረጋገጠ፣ በጣም ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚያስችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም እንኳ፣ ተስፋ ሊኖረን እንችላልን፣ ተስፋ ማድረግም አለብን ። ቅዱስ መጽሃፍ አብረሃም ተስፋ ሳይኖር ተስፋ አደረገ ብሎ ሲናገር13—ማለትም ላለማመን በቂ ምክንያት እያለው— ፈጽሞ ሊሆን የሚችል ባይመስልም እሱ እና ሳራ ልጅ እንደሚኖራቸው አመነ። ስለዚህ “ብዙዎቹ የ 1820 ተስፋዎቻችን በኒው ዮርክ በዛፎች መካከል ለተንበረከከው ልጅ በመለኮታዊ ብርሃን መፈጸም ከጀመረ፣ ጻድቅ ምኞቶቻትን እና የክርስቶስ መሰል ጉጉቶቻችን በአስደናቂ እና በተአምራዊ ሁኔታ ይፈጸማሉ ብለን ለምን ተስፋ አናደርግም?” ብዬ እጠይቃለሁ። ሁላችንም በጽድቅ የምንሻው ነገር የሆነ ቀን በሆነ መንገድ እንደምንም ብሎ የእኛ ሊሆን እንደሚችል ሁላችንም ማመን አለብን።

ወንድሞች እና እህቶች፣ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ አንዳንዶች አንዳንድ የሃይማኖት ጉድለቶች ምን እንደነበሩ እናውቃለን። በተጨማሪም፣ የዛሬውን የሃይማኖት ጉድለቶች አሁንም ድረስ የአንዳንዱን ረሃብ እና ተስፋ እንዳይሟሉ እንዳደረጉ እናውቃለን። እነዚህ የተለያዩ እርካታ ማጣቶች ብዙዎችን ከተለመደው የቤተክርስትያን ተቋማት እያራቁ እንደሆነ እናውቃለን። እንደምናውቀው፣ አንድ የተበሳጨ ጸሐፊ እንደጻፈው፣ “በዘመኑ የነበሩ በርካታ የሃይማኖት መሪዎች ይህንን ውድቀት በማቃለል ረገድ ምንም ትርጉም የለሽ የሚመስሉ” እንደሆኑ እናውቃለን፣ በምላሹም “አይምሮን ለማስታገስ የሚሰጥ የሳሳ ትምህርት፣ ርካሽ ተምሳሌታዊ ንቅናቄ፣ በጥንቃቄ የቀረበ መናፍቅነት፣ [ወይም አንዳንድ ጊዜ] የማያነሳሳ እርባና ቢስ የሆነ ”14—እና ዓለም በጣም በሚፈልግበት፣ የሚያድገው ትውልድ በጣም ብዙ የሚገባው በሚሆንበት እና በኢየሱስ ዘመን ደግሞ በጣም ብዙ ነገሮችን አቀረበ። እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት፣ “አጥንታችን ደርቀዋል፣ ተስፋችንም ጠፍቷል”15ብለው ከሚያለቅሱ የጥንት እስራኤላውያን በላይ በዘመናችን መሆን እንችላለን። በእርግጥም፣ በመጨረሻ ተስፋችንን ካጣን፣ የመጨረሻውን የሚደግፈንን ንብረታችንን እናጣለን። ዳንቴ በሲኦል በር ላይ ሆኖ የጻፈውን በዲቪና ኮሜዲያ ውስጥ ለሚጓዙ ሁሉ የሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ “እዚህ የምትገቡ ሁሉ፣” “ሁሉንም ተስፋ ተዉ” አለ።16 በእውነት ተስፋ ሲጠፋ የሚቀረን በሁሉ አቅጣጫ የሚነድ ሰደድ እሳት ነው።

ስለዚህ፣ ጀርባችን ወደ ግድግዳው ሲሆን እና ዝማሬው እንደሚናገረው “ሌሎች ረዳቶች ከንቱ ሲሆኑ እና መጽናናት ሲሸሽ፣”17 በጣም አስፈላጊ ከሆኑት በጎ ምግባሮቻችን ውስጥ፤ በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነት እና ለሌሎች ባለን ልግስና መጨመር ውድ የሆነው የተስፋ ስጦታ ይሆናል።

በዚህ ሁለት መቶኛ ዓመታዊ በአል የተሰጠንን ሁሉ ለማየት ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከት እና በርካታ ተስፋዎች በመፈጸማችን ስንደሰት፣ ከጥቂት ወራት በፊት በጆሃንስበርግ የነገረችን ቆንጆ እህት የሚስዮን ተመላሽ ስሜት እስተጋባለሁ። “እኛ ይህን ያህል ወደዚህ የመጣነው እስከዚህ ድረስ ብቻ እንድንመጣ አይደለም።”18

በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ እስካሁን ከተመዘገቡት በጣም አጓጊ ከሆኑት የትንቢት ጽሑፎች መካከል አንዱን በማብራራት፣ ከነቢዩ ኔፊ እና ከእዚያች ወጣት እህት ጋር እላለሁ፤

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ [እና እህቶቼ]፣ እነዚህን [የዳግም መመለስ ፍሬዎችን ከተቀበሉ] በኋላ፣ ሁሉም ተፈጸመ ወይ ብዬ እጠይቃለሁ? እነሆ፣ እንዲህ እልሃለሁ፣ አይደለም።

“ስለሆነም ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖራችሁ በክርስቶስ ባላችሁ ፅኑነት መቀጠል አለባችሁ። በእውነት ወደ እኔ ከመጣችሁ ዘለዓለማዊ ህይወትን ታገኛላችሁ።”19

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ የመጨረሻ ዘመን እና ወቅት ዳግም ለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስጋናን አቀርባለሁ። ከዛ ወንጌል የሚፈሱ ስጦታዎች እና በረከቶች ለእኔ ሁሉም ነገር ናቸው፣ እናም ለሁሉም የሰማይ አባቴን ለማመስገን በማደርገው ጥረት፣ “የምጠብቃቸው ቃል ኪዳኖች፣ እና ከመተኛቴ በፊት የምሄድባቸው ማይሎች፣ እና ከመተኛቴ በፊት የምሄድባቸው ማይሎች” አሉኝ።20 ስለዚህ፣ አሁን ለ 200 ዓመታት የኖርንበትን የቅዱሳን ተስፋን ጎዳና የሚያበራ መብራት በሚኖረን “በተስፋ ብሩህነት”21 ውስጥ በመራመድ በልባችን በፍቅር ወደፊት እንገፋ። ወደፊቱ ቀድሞ እንደነበረው በተአምር እና በተትረፈረፈ በረከት እንደሚሞላ እመሰክራለሁ። እኛ ከተቀበልነው በላይ ለሚበልጡ በረከቶች ተስፋ የምናደርግበት ምክንያቶች አሉን፣ ምክንያቱም ይህ የሁሉን ቻይ የእግዚአብሔር ሥራ ነው፣ ይህ ቀጣይነት ያለው መገለጥ ያለው ቤተክርስቲያን ነው፣ እና ይህ ወሰን የሌለው የጸጋና እና የበጎነት ወንጌል ነው። ለነዚህ እውነቶች ሁሉ እና ስለተጨማሪዎች የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “The Essence of the Christian Religion,” in The Works of William E. Channing (1888), 1004.

  2. 2 ኔፊ 26፥24

  3. ዮሀንስ 3፥16–17

  4. ሙሴ 7፥62

  5. ኢሳይያስ 2፥1-3ሕዝቀኤል 37፥26ሚክያስ 4፥1–3ሚልኪያስ 3፥1ይመልከቱ።

  6. ዮሀንስ 14፥2

  7. 1 ቆሮንቶስ 15፥29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15-17ይመልከቱ።

  8. ዕብራውያን 6፥19ኤተር 12፥4ተመልከቱ።

  9. ና ዙ እና ሌሎችን ተመልከቱ፣ “በ 2019 እ.ኤ.አ. በቻይና ውስጥ የሳንባ ምች ህመም ካላቸው ህመምተኞች እንግዳ የሆነ ኮሮና ቫይረስ፣ ” የኒው ኢንግላንድ የህክምና ሙያ ጽሁፍ የካቲት 20፣ 2020 እ.ኤ.አ፣ 727–33።

  10. “የአፈር አይነቶች ምርመራ እና መግለጫ፣ ” በ የአፈር ጥናት መምሪያ፣ ed. ሲ ዲተዘለር፣ ኬ ስሸፍ፣ እና ኤች ሲ ሞንገር (2017) (እ.አ.አ)፣ nrcs.usda.gov ተመልከቱ።

  11. ማቴዎስ 22፥36–40ማርቆስ 12፥29–33ሌዋውያን 19፥18ኦሪት ዘዳግም 6፥1–6ይመልከቱ።

  12. ኤተር 12፥4ተመልከቱ።

  13. ሮሜ 4፥18ተመልከቱ።

  14. አር ጄ ስኔል፣ “ጸጥ ያለ ተስፋ፤ የአዲስ ዓመት ውሳኔ፣” የሕዝብ ንግግር፤ የዊዘርስፑን ተቋም ጽሁፍ፣ ታህሳስ 31፣ 2019 (እ.አ.አ)፣ thepublicdiscourse.com።

  15. ሕዝቅኤል 37፥11

  16. ይህ ሀረግ በታዋቂነት እንደተተረጎመ ነው። ሆኖም፣ የበለጠ ቀጥተኛው ትርጉም ው “ወደዚህ የምትገቡ፣ ተስፋ ሁሉ ተውት” (ዳንቴ አልዋንሪ፣ “የሲኦል ራዕይ”፣ Divine Comedy፣ ትራንስ ሄንሪ ፍራንሲስ ካሪ [1892]፣toto III፣ 9)።

  17. “ ከእኔ ጋር ሁን” መዝሙር ቁጥር 166።

  18. ጁዲዝ ማህላንጉ (ከጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ አጠገብ ከሚገኝ የብዙ የካስማዎች ጉባኤ ህዳር 10፣ 2019 (እ.አ.አ))፣ በሲድኒ ዋከር፣ በአስገራሚ የእድገት ጊዜ “ሽማግሌ ሆላንድ የአፍሪካን ደቡብ ምስራቃማ ክፍልን ገበኙ” የቤተክርስቲያን ጋዜጣ፣ ህዳር 27፣ 2019 (እ.አ.አ)፣ thechurchnews.com።

  19. 2 ኔፊ 31፥19–20፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  20. “በበረዷማ ምሽት ላይ በዛፎች አካባቢ መሄድ፣” መስመሮች 14–16, in የሮበርት ፍሮስት ስኑእ ግጥም፤ የተሰበሰቡ ግጥሞች፣ ed. እድዋርድ ኮነሪ ላዘም (1969) (እ.አ.አ)፣ 225።

  21. 2 ኔፊ 31፥20