ምዕራፍ ፫
ንጉስ ቢንያም ንግግሩን ቀጠለ—ሁሉን የሚገዛው ጌታ በጭቃ ሰውነቱ በሰዎች መካከል ያገለግላል—ለዓለም ኃጢአቶች ዋጋን ሲከፍል ደም ከሰውነቱ ቀዳዳ ሁሉ ይፈሳል—ደህንነት የሚመጣበት ብቸኛው ስም የእርሱ ነው—ሰዎች በኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ፍጥረታዊ ሰውነታቸውን መለወጥ እናም ቅዱሳን ለመሆን ይችላሉ—የኃጢአተኞች ስቃይ እንደባህር እሳትና ዲን ይሆናል። ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንደገና ወንድሞቼ፤ ለእናንተ የምናገረው ከዚህ በላይ በመጠኑ ስላለኝ ትኩረታችሁንም እፈልጋለሁ፤ እነሆ የሚመጣውን በተመለከተ የምነግራችሁ ነገሮች አሉኝና።
፪ እናም የምናገራችሁ ነገሮች በእግዚአብሔር ሀመልአክ ተገልፀውልኛል። እርሱም እንዲህ አለኝ፥ ንቃ፤ እናም ነቃሁ፤ እነሆ እርሱም ከፊቴ ቆመ።
፫ እናም እርሱ እንዲህ አለኝ፥ ንቃ፣ የምነግርህን ቃላት ስማ፤ እነሆም የታላቁን ደስታ ሀየምስራች ላበስርልህ መጥቻለሁና።
፬ ጌታ ፀሎትህን ሰምቷልና፣ እናም ፅድቅህንም በሚመለከት ፈርዷልና፤ እናም አንተ ትደሰት ዘንድና፤ ለህዝብህ ትናገር ዘንድ፤ እነርሱም ደግሞ በደስታ ይሞሉ ዘንድ ልኮኛል።
፭ እነሆም፣ በኃይል ሁሉንም የሚገዛው ሀጌታ የነገሰው፣ የነበረው፣ እናም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ሁሉ የሚኖረው፣ ከሰማይ በሰው ልጆች መካከል የሚመጣበት ጊዜ ይመጣል፣ ሩቅም አይደለም፣ ለበጭቃ ሰውነቱ ይኖራልም፤ እናም በሰዎች መካከል፣ በሽተኞችን የመፈወስ፣ ሙታንን የማስነሳት፣ ሽባዎችን እንዲራመዱ የማድረግ፣ እውሮች ማየት እንዲችሉ፣ ደንቆሮዎችም እንዲሰሙ፣ እናም ሁሉንም የበሽታ ዓይነቶችን ለማዳን ሐአስደናቂ ስራዎችን እየሰራ ይሄዳል።
፮ እናም እርሱ ሀዲያብሎስን፣ ወይንም በሰው ልጆች ልብ ውስጥ የሚኖረውን እርኩስ መንፈስ ያስወጣል።
፯ እናም እነሆ፣ ሀበፈተናና በስጋዊ ህመም፣ ለበርሃብ፣ በጥማትና፣ በድካም፤ ከሞት በስተቀር ሰው ሐሊሰቃይበት ከሚችለው የበለጠም ይሰቃያል፤ እነሆም ለህዝቡ ክፋትና እርኩሰት መጭንቀቱ እጅግ ታላቅ ሆኖ፣ ሠደሙም ከእያንዳንዱ የሰውነቱ ቀዳዳ ይፈሳል።
፰ እናም እርሱም ሀኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለየእግዚአብሔር ልጅ፣ የሰማይና የምድር ሐአባት፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሁሉም ነገር ፈጣሪ የነበረ ተብሎ ይጠራል፤ እናም መእናቱ ሠማርያም ተብላ ትጠራለች።
፱ እናም እነሆ፣ በስሙ ሀበማመን ለደህንነት ለሰው ልጆች ይመጣ ዘንድ የእርሱ ወደ ሆኑት መጣ፤ እናም ከዚህ ሁሉ በኋላ እንኳን እንደ ሰው ይቆጥሩታል፣ ሐዲያብሎስ አለው ብለው ይናገራሉም፤ መይገርፉታልም፣ እንዲሁም ሠይሰቅሉታል።
፲ እርሱም ሀበሶስተኛው ቀን ለከሞት ይነሳል፤ እናም እነሆ ዓለምን ሐሊፈርድ ይቆማል፤ እናም እነሆ በሰው ልጆች ላይ ጻድቃዊው ፍርድ ይመጣ ዘንድ እነዚህ ሁሉ ይሆናሉ።
፲፩ እነሆም፣ እናም ደግሞ በአዳም መተላለፍ ሀለወደቁት ኃጢአተኞች፣ እነርሱን በተመለከተ ያለውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳያውቁ ለሞቱት፣ ወይም ለባለማወቅ ኃጢያትን ለፈፀሙት የእርሱ ሐደም መየኃጥያቶች ክፍያ ይሆናል።
፲፪ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ሀማመፁን ለሚያውቅ ወዮ ወዮለት! እንደነዚያ ላሉት ደህንነት በንስሃ እና ለበጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ካልሆነ በቀር አይመጣምና።
፲፫ እናም ጌታ እግዚአብሔር ለሁሉም ወገን፣ ሀገርና፣ ቋንቋ፣ እነዚህን ነገሮች እንዲናገሩ ቅዱሳን ነቢያቱን በሰው ልጆች ሁሉ መካከል ልኳል፤ በዚህም ማንኛውም ክርስቶስ ይመጣል በማለት የሚያምን ለኃጢአቱ ሀስርየትን ያገኛል፣ እርሱም በመካከላቸውም ለእንደመጣም ዓይነት በታላቅ ደስታ ሃሴት ይሆናሉ።
፲፬ ይሁን እንጂ ጌታ እግዚአብሔር ሕዝቡ አንገተ ደንዳና እንደሆኑ ተመልክቷል፣ እናም ህግን፣ እንዲሁም የሙሴንም ሀሕግ መስርቶላቸዋል።
፲፭ እናም የእርሱን መምጣት በተመለከተ ብዙ ምልክቶችንና፣ ተዓምራትንና፣ ሀምሳሌዎችንና ጥላውን አሳይቷቸዋል፤ እናም ደግሞ መምጣቱን በተመለከተ ቅዱሳን ነቢያትም ነግረዋቸዋል፤ ይሁን እንጂ እነርሱ ልባቸውን አጠጥረዋል፣ በደሙ ክፍያም ካልሆነ በቀር የሙሴ ለሕግ ምንም የማይጠቅም መሆኑን አልተገነዘቡትም።
፲፮ እናም ምንም እንኳን ሀህጻናት ኃጢያትን መስራት የሚችሉ ቢሆኑም ሊድኑ አይችሉም ነበር፤ ነገር ግን እነርሱ ለየተባረኩ ናቸው እላችኋለሁ፤ እነሆም፣ በአዳም፣ ወይም በፍጥረት እንደወደቁም፣ የክርስቶስ ደም ለኃጢአታቸው ክፍያ እንዲሁም ያደርጋል።
፲፯ እናም ከዚህ በተጨማሪ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ሁሉን በሚችለው ጌታ ሀበክርስቶስ ስም ካልሆነ በስተቀር ለሰው ልጆች ለደህንነት እንዲመጣ የሚሰጥ ሐምንም ስም ወይም መንገድ፣ ወይም ዘዴ የለም።
፲፰ እነሆም እርሱ ይፈርዳል፣ ፍርዱም ፍፁም ነው፤ እናም በህፃንነቱ የሞተ ህፃን አይጠፋም፤ ነገር ግን ሰዎች እራሳቸውን ትሁትና፣ እንደ ህፃናት ሀካላደረጉ፣ እናም ሁሉን በሚችለው ጌታ በክርስቶስ የደም ለካሣ ውስጥና በኩል ደህንነት እንደነበረ፣ እንደሚሆንና፣ እንደሚመጣ ካላመኑ በቀር ኩነኔን ይጎነጫሉ።
፲፱ ሀተፈጥሮአዊው ሰው ከአዳም ለውድቀት ጀምሮ ለእግዚአብሔር ጠላት ነው፣ እናም እርሱም ሐለመንፈስ ቅዱስ ግብዣ መፈቃደኛ ካልሆነና፣ ተፈጥሮአዊው ሰውነቱን ካልቀየረ እናም በጌታ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ሠቅዱስ ካልሆነና፣ ረእንደልጅ ሁሉን የሚቀበል፣ የዋህ፣ ትሁት፣ ትዕግስተኛ፣ በፍቅር የተሞላ፣ ልጅ ከአባቱ ተቀባይ እንደሚሆን፣ ጌታ ብቁ ነው ብሎ የሚያደርስበትን ሁሉንም ነገሮች ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ እስከመጨረሻው ለዘለዓለም የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል።
፳ እናም ከዚህ በተጨማሪ፣ እላችኋለሁ፣ የአዳኛችን ሀእውቀት በሁሉም ለሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋ እና ህዝብ መካከል የሚሰራጭበት ጊዜ ይመጣል።
፳፩ እናም እነሆ፣ ያ ጊዜ ሲመጣ፣ ሁሉን በሚችለው በጌታ እግዚአብሔር ስም ንስሃ እና እምነት በኩል፣ ትናንሽ ልጆች ካልሆኑ በቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ሀእንከን የሌለበት አይገኝም።
፳፪ እናም በዚህ ጊዜም እንኳን ቢሆን፣ ጌታ አምላክህ ያዘዘህን ነገሮች ለሕዝባችሁ ስታስተምር፣ እኔ በነገርኩህ ቃላት መሰረት ካልሆነ በስተቀር ከእንግዲህ በእግዚአብሔር ፊት ያለ እንከን አይሆኑም።
፳፫ እናም አሁን ጌታ እግዚአብሔር ያዘዘኝን ቃላት ተናግሬአለሁ።
፳፬ እናም ጌታ እንዲህ ይላል፥ እነዚህ በፍርድ ቀን ለዚህ ሕዝብ እንደ ብሩህ ምስክር ሆነው ይቆማሉ፤ ስለዚህ ማንኛውም ሰው በስራው መሰረት፣ መጥፎም ሆነ መልካም፣ ይፈረድበታል።
፳፭ እናም እነርሱ ደግመው ሊመለሱበት በማይችሉበት ሀበስቃይና መጨረሻ በሌለው አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጌታ ፊት እንዲሸማቀቁ በሚያደርጋቸው በራሳቸው ክፋትና እርኩሰት ክፉዎች ለአስተያየት ላይ ይመደባሉ፤ ስለዚህ ለእራሳቸው ነፍስ ኩነኔን ይጎነጫሉ።
፳፮ ስለዚህ፣ ፍርዱ ሀአዳም የተከለከለውን ለፍሬ በመመገቡ መውደቅ እንዳለበት ለመካድ እንደማይችል እነርሱንም ሊክድ ስለማይችሉ፣ ከእግዚአብሔር የቁጣ ዋንጫ ጎንጭተዋል፤ ስለዚህ ሐምህረት ከእንግዲህ ለዘለዓለም በእነርሱ ላይ ጥያቄ ሊኖረው አይችልም።
፳፯ እናም ሀስቃያቸው ነበልባሉ የማይጠፋ፣ እና ጢሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ እንደሚያርገው እንደ እሳቱ ለባህርና ዲን ነው። እንደዚህም ጌታ እኔን አዞኛል። አሜን።