ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፲፰


ምዕራፍ ፲፰

አልማ በድብቅ ሰበከ—የጥምቀትን ቃል ኪዳን ገለፀ እናም በሞርሞን ውሃ አጠመቀ—የክርስቶስን ቤተክርስቲያን አዋቀረ እናም ካህናትን ሾመ—እነርሱም ራሳቸውን ረዱ እናም ህዝቡን አስተማሩ—አልማና ህዝቡ ከንጉስ ኖህ ወደ ምድረበዳው ሸሹ። ከ፻፵፯–፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ ከንጉስ ኖህ አገልጋዮች የሸሸው አልማ፣ ለኃጢአቱና ለጥፋቱ ንስሃ ገባ፣ እናም በድብቅ ከህዝቡ መካከል ሄደና፣ የአቢናዲን ቃላት ማስተማር ጀመረ—

አዎን፣ ወደፊት የሚመጣውን በተመለከተ፣ ደግሞም የሙታን ትንሳኤን በተመለከተና፣ በክርስቶስ ሃይል፣ ስቃይና፣ ሞት ስለሚመጣው የህዝቦች ቤዛነት፣ እናም ትንሳኤውና ወደሰማይ ማረጉን ማስተማር ጀመረ።

እናም ቃሉን ለሚሰሙት ሁሉ አስተማረ። ንጉሱ እንዳያውቅም በድብቅ አስተማራቸው። እናም ብዙዎች ቃሉን አመኑት።

እናም እንዲህ ሆነ ብዙዎች ስላመኑት ስሙን ከንጉሱ በመቀበል ሞርሞን ወደሚባል፣ በምድሪቱ ዳርቻ በመሆን በጊዜው ወይም በወቅቱ በዱር አራዊቶች ተወርሮ ወደነበር ስፍራ ሄዱ።

አሁን፣ የንፁህ ውሃ ምንጭ በሞርሞን ነበር፣ እናም አልማ ወደ ቦታው ሄደ፤ በውሃውም አጠገብ በቀን እራሱን ንጉሱ እንዳያገኘው የሚደብቅበት ጥቅጥቅ ያሉ አጫጭር ዛፎች ነበሩ።

እናም እንዲህ ሆነ የሚያምኑት ሁሉ ቃሉን ለመስማት ወደ እርሱ ሄዱ።

እናም እንዲህ ሆነ ከብዙ ቀናት በኋላ የአልማን ቃል ለመስማት ሞርሞን በተባለ ስፍራ የተሰባሰቡ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ነበሩ። አዎን፣ በቃሉ ያመኑት ሁሉ ሊሰሙት ተሰበሰቡ። እናም አስተማራቸው፣ ንስሃና፣ ቤዛነትን፣ እንዲሁም በጌታ ማመንንም ሰበከላቸው።

እናም እንዲህ ሆነ እንዲህም አላቸው፥ እነሆ፣ የሞርሞን ውሃ ይህ ነው፣ (እንደዚህም ነበር የተጠሩት) እናም አሁን፣ እናንተ ወደ እግዚአብሔር በረት ለመምጣትና፣ ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እንዲሁም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን እንደፈለጋችሁ

አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን ለሚፈልጉም ካፅናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ በምትኖሩበት ቦታዎች ሁሉ፣ እስከሞት ድረስ፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድና፣ በጌታ ትድኑ ዘንድ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትም ይኖራችሁ ዘንድና የመጀመሪያውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋርም ለመቆጠር ፈቃደኞች ከሆናችሁ—

አሁን እላችኋለሁ፣ ይህ የልባችሁ ፍላጎት ከሆነ፣ እርሱን እንደምታገለግሉ እናም ትዕዛዛቱን እንደምትጠብቁ፣ እርሱም በእናንተ ላይ መንፈሱን በብዛት ያፈስባችሁ ዘንድ በፊቱ እንደምስክርነት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት በጌታ ስም ለመጠመቅ የሚያስቸግራችሁ ምንድን ነው?

፲፩ እናም አሁን ህዝቡ ይህንን አባባሉን በሰሙ ጊዜ፣ በደስታ አጨበጨቡ፣ እናም በደስታ ይህ የልባችን ፍላጎት ነው ብለው ጮኹ።

፲፪ እናም አሁን እንዲህ ሆነ አልማ ሔላምን ወሰደ፤ የመጀመሪያውም ሆኖና፣ ሄዶ በውሃው ውስጥ ቆመና እንዲህ ሲል ጮኸ፥ ጌታ ሆይ፣ በተቀደሰ ልብ ይህን ስራ ይሰራ ዘንድ፣ መንፈስህን በአገልጋይህ ላይ አፍስ።

፲፫ እናም እነዚህን ቃላት ሲናገር፣ የጌታ መንፈስ በእርሱ ላይ ነበር፣ እናም እንዲህ አለ፥ ሄላም፣ ሁሉን ከሚገዛ አምላክ በተሰጠኝ ስልጣን፣ እስከሞት ድረስ እርሱን ለማገልገል ቃል ኪዳን እንደገባህ ምስክርነት አጠምቅሀለሁ፤ እናም የጌታ መንፈስ በአንተ ላይ ይፍሰስ፤ እርሱንም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ባዘጋጀው በክርስቶስ ቤዛነት ዘለዓለማዊ ህይወት ይስጥህ።

፲፬ እናም አልማ ይህንን ቃል ከተናገረ በኋላ፣ አልማና ሄላም ሁለቱም በውሃው ውስጥ ጠለቁ፤ እናም ተነሱና በመንፈስ ተሞልተው እየተደሰቱ ከውሃው ውስጥ ወጡ።

፲፭ እናም እንደገና፣ አልማ ሌላውን ወስዶ፣ ለሁለተኛ ጊዜም ወደ ውሃው ገባ፣ እናም ይኼኛውንም እንደመጀመሪያው አጠመቀው፤ ነገር ግን ራሱ በድጋሚ ውኃ ውስጥ አልጠለቀም ነበር።

፲፮ እናም ወደ ሞርሞን ስፍራ የሄዱትን ማናቸውንም በዚህ ሁኔታ ያጠምቅ ነበር፣ በቁጥርም ወደ ሁለት መቶ አራት ነፍስ ገደማ ነበሩ፤ አዎን፣ እናም በሞርሞን ውሃ ተጠምቀው በእግዚአብሔርም ፀጋ ተሞልተው ነበር።

፲፯ እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን፣ ወይንም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብለው ተጠሩ። እናም እንዲህ ሆነ በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን የተጠመቀ ማንኛውም ወደ እርሱ ቤተክርስቲያን ይጨመራል።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ አልማ፣ ከእግዚአብሔር ስልጣንን ኖሮት ካህናትን ሾመ፤ እንዲያውም አንድ ካህንም ቢሆን ሀምሳዎችን እንዲያስተምሩና፣ ስለእግዚአብሔር መንግስት ተገቢ የሆኑትን ነገሮች እንዲያስተምሩ ሾማቸው።

፲፱ እናም እርሱ ካስተማራቸውና በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ ከተናገራቸው ነገሮች በቀር ምንም እንዳያስተምሩ አዘዛቸው።

አዎን፣ ህዝቡን ስላዳነው ጌታ ንስሃንና እምነትን ካልሆነ በቀር ምንም እንዳይሰብኩ አዘዛቸው።

፳፩ እናም አንዱ ከሌላኛው እንዳይጣላ፣ ነገር ግን አንድ እምነትና፣ አንድ ጥምቀት ይዘው፣ በአንድ ዓይን እንዲተያዩ፣ ልባቸው በአንድ ላይ በአንድነትና፣ አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር እንዲጣበቁ አዘዛቸው።

፳፪ እና እንደዚህም እንዲሰብኩ አዘዛቸው። እንደዚህም የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ።

፳፫ እናም የሰንበትን ቀን እንዲያከብሩና፣ እንዲቀድሱት፣ ደግሞም ለጌታ ለአምላካቸው በየቀኑ ምስጋናን እንዲያቀርቡ አዘዛቸው።

፳፬ እናም ደግሞ እርሱ የሾማቸው ካህናት እራሳቸውን ለመርዳት በእጃቸው እንዲሰሩ አዘዛቸው።

፳፭ እናም ህዝቡን በአንድ ላይ በመሰብሰብ ለማስተማርና፣ ጌታ አምላካቸውን ለማምለክ ከሳምንቱ አንዱ ቀን መርጠዋል፣ ደግሞም እንደቻሉ፣ ሁልጊዜም እራሳቸውን ይሰበስባሉ።

፳፮ እናም ካህናቱ ለኑሮአቸው ድጋፍን ለማግኘት በህዝቡ ላይ ጥገኛ አልነበሩም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ዕውቀት በማግኘት በመንፈስ ጠንክረው ያድጉ ዘንድ፣ በእግዚአብሔር ኃይልና ሥልጣን ለማስተማር የእግዚአብሔርን ፀጋ ይቀበሉ ነበር።

፳፯ እናም በድጋሚ አልማ የቤተክርስቲያኑ አባላት እያንዳንዳቸው ባላቸው መጠን እንዲያካፍሉ አዘዘ፤ በብዛት ካለው በብዛት ያካፍል፤ ትንሽ ያለውም ግን ትንሽ ይፈለግበታል፣ የሌለውም ይሰጠዋል።

፳፰ እናም ወደ እግዚአብሔርና፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ካህናት፣ አዎን፣ እናም ለማንኛውም ችግረኛ ለሆነ፣ ለተራቆተ ነፍስ ባላቸው መልካም ፍላጎት ሀብታቸውን በነፃ ፈቃዳቸው እንደዚህም ማካፈል ይገባቸዋል።

፳፱ እናም በእግዚአብሔር በመታዘዝ እንዲህ አላቸው፥ እናም እንደፍላጎታቸውና ፈቃዳቸው አንዱ ለሌላው በአለማዊና መንፈሳዊ አመለካከት ያላቸውን በመካፈል በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት ተራመዱ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ ይህ ሁሉ የሆነው በሞርሞን ነው፣ አዎን፣ በሞርሞን ውኃ አጠገብ ባለው ጫካ በሞርሞን ውኃ አጠገብ ነበር፤ አዎን፣ የሞርሞን ስፍራ፣ የሞርሞን ውኃ፣ የሞርሞን ጫካ፣ ቤዛቸውን ለማወቅ በመጡበት ዐይን እንዴት ውብ ናቸው፤ አዎን፣ እናም እንዴት የተባረኩ ናቸው፣ ለዘለዓለም እርሱን ለማመስገን ይዘምራሉና።

፴፩ እናም እነዚህ ሁሉ የተደረጉት ንጉሱ እንዳያውቃቸው በምድሪቱ ዳርቻ ነው።

፴፪ ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ ሆነ ንጉሱ፣ በህዝቡ መካከል እንቅስቃሴ በመመልከት፣ አገልጋዮቹን እንዲመለከቷቸው ላከ። ስለዚህ የጌታን ቃል ለመስማት አብረው በተሰበሰቡበት ቀን በንጉሱ ተገኙ።

፴፫ እናም አሁን ንጉሱ አልማ ህዝቡ በእርሱ ላይ እንዲያምፅ ያውካል አለ፤ ስለዚህ እነርሱን እንዲያጠፉአቸው ወታደሮቹን ላከ።

፴፬ እናም እንዲህ ሆነ አልማና የጌታ ህዝብ የንጉሱን ወታደሮች መምጣት አወቁ፤ ስለዚህ ድንኳናቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ወሰዱና፣ ወደ ምድረበዳው ሸሹ።

፴፭ እናም በቁጥር አራት መቶ ሀምሳ ነፍስ ገደማ ነበሩ።