ምዕራፍ ፲፬
ኢሳይያስ ስለመሲሁ ተናገረ—የመሲሁ መዋረድና መሰቃየት ተገልፆአል—ነፍሱን ለኃጢያት መስዋዕት ሰጠ፣ እናም ለተላለፉት አማላጅ ሆነ—ኢሳይያስ ፶፫ን አነጻፅሩ። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።
፩ አዎን፣ ኢሳይያስም እንኳን ይህን አላለምን፤ የእኛን ዜና ማን አምኗል፣ እናም የጌታስ ክንድ ለማን ተገልጧል?
፪ በፊቱ እንደቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደስር አድጓል፣ መልክና ውበት የለውም፣ ባየነውም ጊዜ እንወደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
፫ በሰውም የተጠላና የተናቀ ነው፤ ህማምና ሀዘንን የሚያውቅ ሰው ነው፣ እናም ፊታችንንም ከእርሱ ሰወርን፤ የተጠላ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።
፬ በእውነት ሀስቃያችንን ለተቀበለ፤ እናም ሀዘናችንን ተሸከመ፤ እኛ ግን እንደተቸገረ፣ በእግዚአብሔር እንደተቀሰፈና እንደተመታ ቆጠርነው።
፭ ነገር ግን ሀስለመተላለፋችን እርሱ ቆሰለ፤ ስለበደላችንም ደቀቀ፤ የሰላማችን ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበር፤ እናም በቁስሉ ለተፈወስን።
፮ እኛ ሁላችንም እንደ ሀበጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እናም ጌታ የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
፯ ተጨነቀ፤ እናም ተሰቃየ፣ ሀአፉንም አልከፈተም ነበር፤ እንደበግ ለመታረድ ቀረበ፤ እናም በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል ለበግ አፉን አልከፈተም።
፰ ከወህኒና ከፍርድ ተወሰደ፤ እናም ስለ ትውልዱስ የሚያስተውልስ ማን ነው? እርሱ ከህያዋን ምድር ተወግዶአልና፤ ስለህዝቤም መተላለፍ ተመቷልና።
፱ እናም መቃብሩን ከክፉዎች ጋር አደረገ፤ እናም ሞቱን ሀከባለጠጋዎች ጋር፤ ምንም ለክፉ ነገር አላደረገምና፤ በአንደበቱም ተንኮል አልተገኘበትም።
፲ ይሁን እንጂ ጌታ እርሱን ማቁሰል አስደሰተው፤ በሃዘን ውስጥ ጨመረው፤ ነፍሱን ስለኃጢያት መስዋዕት ካደረገ በኋላ ሀዘሩን ያያል፣ እድሜውን ያረዝማል፣ እናም የጌታ ፈቃድ በእጁ ውጤታማ ይሆናል።
፲፩ የነፍሱን ስቃይ ይመለከታል፣ እናም ደስ ይለዋል፤ ፃድቁ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ሀይሸከማልና።
፲፪ ስለዚህ ከኃያላን ጋር ትልቁን አካፍለዋለሁ፤ እናም ከጠንካሮች ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቷልና፤ ህጉን ከተላለፉት ጋር ተቆጥሯልም፣ እናም የብዙዎችን ኃጢያት ተሸከመ፤ ስለአመፀኞችም ሀማለደ።