የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬፥፪–፭። ከሮሜ ፬፥፪–፭ ጋር አነጻፅሩ

ሰው ለመዳን የሚችለው፣ የሙሴ ህግን ከመከተል ጋር ባለው ስራ ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ብቻ ነው።

፪ አብርሃም በሥራ ህግ ጸድቆ ቢሆን፣ በራሱ ክብር አለው፤ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም።

፫ ቅዱስ መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።

፬ በሥራ ህግ ጸድቆ የሆነው ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤

፭ ነገር ግን በሥራ ህግ ጽድቅ ለመሆን ለማይፈልገው፣ ግን ኃጢአተኛውንም በማያጸድቀው ለሚያምነው፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬፥፲፮። ከሮሜ ፬፥፲፮ ጋር አነጻፅሩ

እምነት እና ስራም፣ በጸጋ በኩል፣ ለደህንነት አስፈላጊ ነው።

፲፮ ስለዚህ እስከመጨረሻ ድረስ በእምነት እና በስራ፣ በጸጋ በኩል ቃል ኪዳን እንዲጸና ዘንድ ጸድቃችኋል፤ ይህም በህግ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን ደግሞ አባታችን ለሆነው ከአብርሃም እምነት ለሆኑት ለዘሩ ሁሉ ነው።