የጥናት እርዳታዎች
10. አዳም-ኦንዳይ-አማን


10. አዳም-ኦንዳይ-አማን

ምስል
ፎቶ ፲

በጋላቲን ማህብረሰብ አጠገብ፣ በሰሜን ምዙሪ የሚገኘውን ጸጥተኛ፣ አስደሳች፣ ሸለቆ፣ ከአዳም-ኦንዳይ-አማን ሸለቆ ወደ ምስራቅ የሚመለከት።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ከመሞቱ ሶስት አመት በፊት፣ አዳም ጻድቅ ትውልዱን በዚህ ሸለቆ ውስጥ ሰበሰበ እናም በእነርሱም ላይ የመጨረሻ በረከቱን ሰጠ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፶፫–፶፮)። በ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) አዳም-ኦንዳይ-አማን በ፭፻ እስከ ፩ ሺህ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የሰፈሩበት ቦታ ነበር። ቅዱሳን ይህን ስፍራ ከምዙሪ በግድ ሲወጡ ጥለውት ሄዱ። ክርስቶስ በግርማ ዳግም ከመምጣቱ በፊት፣ አዳም እና ከዘመናት ሁሉ ቅዱሳን የሆኑትን የሚጨምሩት ጻድቅ ትውልዱ እንደገና በዚህ ሸለቆ ውስጥ ከአዳኝ ጋር ለመገናኘት ይሰበሰባሉ (ዳን. ፯፥፱–፲፣ ፲፫–፲፬ት. እና ቃ. ፳፯፻፯፥፶፫–፶፯፻፲፮)።