የጥናት እርዳታዎች
12. ልብርቲ እስር ቤት


12. ልብርቲ እስር ቤት

ምስል
ፎቶ ፲፪

በልብርቲ፣ ምዙሪ ውስጥ የነበረ እስር ቤት፣ በ፲፰፻፸፱ (እ.አ.አ.) አካባቢ። ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች አምስት ወንድሞች ፩ ነጥብ ፪ ሜትር ውፍረት ያለው ግድግዳዎች ባለው እስር ቤት ውስጥ ከታህሳስ ፩፣ ፲፰፻፴፰ እስከ ሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ድረስ ታስረው ነበር። (ስድኒ ሪግደን በየካቲት መጨረሻ ላይ ተለቀቀ።) በህንጻው በታች ክፍል ወይም ወህኒ ቤት ውስጥ ታስረው እያሉ፣ ብዙ ብርሀን ሳይኖራቸውና ከብርድ መጠበቂያም ብዙ ሳይኖራቸው በቀዝቃዛ፣ ሳር በተበተነበት መሬት ላይ ይተኙ ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ነቢዩ ጆሴፍ፣ ከምዙሪ ስለሚሰደዱት ብዙ ሺህ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሲለምን፣ በደብዳቤ ለቅዱሳን የጻፈውን የጸሎት መልስ ተቀበለ (ት. እና ቃ. ፻፳፩–፻፳፫)።