የጥናት እርዳታዎች
5. ሰስኮሀና ወንዝ


5. ሰስኮሀና ወንዝ

ምስል
ፎቶ ፭

ይህ ፎቶ በሀርመኒ ከተማ፣ ፔንስልቬኒያ ውስጥ ያለውን የሰስኮሀና ወንዝ ያሳያል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ወደ ሀርመኒ ለመጀመሪያ ጊዜ በ፲፰፻፳፭ (እ.አ.አ.) የመጣው ስራ ለማግኘት ነበር። እርሱ እና አባቱ በዚህ አጠገብ፣ ከወደፊት ባለቤቱ ኤማ ሄል በተገናኘበት በአይዛክ ሄል ቤት ውስጥ በመክፈል ይኖሩ ነበር (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፶፮–፶፯)። ጆሴፍ እና ኤማ በጥር ፲፰፣ ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) ተጋቡ። ነቢዩ በማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ ውስጥ በመስከረም ፳፪ ቀን ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) የወርቅ ሰሌዳዎችን ተቀበለ፣ እናም ወዲያውም ከኤማ ጋር ወደ ሀርመኒ ሄዶ ሰሌዳዎችን መተርጎም ጀመረ። መፅሐፈ ሞርሞን በሚተረጉምበት ጊዜ፣ ጆሴፍ እና ኦሊቨር ካውደሪ ስለጥምቀት ተጨማሪ ነገሮችን ለማወቅ ፈለጉ እናም ስለእዚህ ርዕስ ለማወቅ ወደ ጌታ ለመጸለይ በዚህ አጠገብ ወደነበረ ጫካ ሄዱ። ለዚህ ጸሎትም መልስ፣ በግንቦት ፲፭፣ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) መጥምቁ ዮሐንስን አዩ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፮–፸፬ት. እና ቃ. ፲፫)። እርሱም ጆሴፍን እና ኦሊቨርን በአሮናዊ የክህነት ስልጣን ሾማቸው። ከእዚያም ወደ ወንዙ ገቡ እናም እርስ በርስ ለኃጢያት ስርየት በመነከር ተጠመቁ። ጆሴፍ እና ኦሊቨር ከእዚያም በኋላ እርስ በራስ በአሮናዊ የክህነት ስልጣን እንዲሾሙ መመሪያ ሰጣቸው። ከእዚህ ትንሽ ጊዜ በኋላ፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ በሀርመኒ እና በኮልስቪል መካከል ታይተው ጆሴፍን እና ኦሊቨርን በመልከ ጼዴቅ የክህነትሹመት ሰጧቸው (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪–፲፫፻፳፰፥፳)።