የጥናት እርዳታዎች
11. የፋር ዌስት የቤተመቅደስ መገንቢያ ቦታ


11. የፋር ዌስት የቤተመቅደስ መገንቢያ ቦታ

ምስል
ፎቶ ፲፩

የፋር ዌስት፣ ምዙሪ ስፍራ በጃክሰን እና ክሌይ ግዛት ውስጥ ለተሰደዱት ለ፫ ሺህ እስከ ፭ ሺህ ቅዱሳን መሸሸጊያ ነበር። በ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) ጌታ ቅዱሳን ቤተመቅደስ በዚህ እንዲገነቡ አዘዘ (ት. እና ቃ. ፻፲፭፥፯–፰)። በአመጽ የተነሳሱ ሰዎች በማሳደዳቸው ምክንያት ይህን ከማድረግ ተወግደው ነበር። በዚያ አመት ጥቅምት ፴፩ (እ.አ.አ.) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ታሰሩ፣ እናም በሪችመንድ በፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በልብርቲ እስር ቤት ውስጥ ታሰሩ። በ፲፰፻፴፰–፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.)፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ከፋር ዌስትና ከምዙሪ ሌሎች ቦታዎች ተገደው ወጡ እናም ወደ ኢለኖይ ሄዱ።

ታላቅ ድርጊቶች፥ የቤተመቅደስ ቦታ ተቀደሰ እናም የማዕዘን ድንጋይ ተነጠፈ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የታተሙ ሰባት ራዕዮች ተቀበለበት (ክፍሎች ፻፲፫–፻፲፭፻፲፯–፻፳)። የቤተክርስቲያኗ ስድስተኛ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ በፋር ዌስት ውስት በህዳር ፲፫፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) ተወለዱ። ፋር ዌስት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ስር እንደ ቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ ለአጭር ጊዜ አገለገለ።