የጥናት እርዳታዎች
2. ከሞራ ኮረብታ እና ማንቸስተር-ፓልማይራ አካባቢ


2. ከሞራ ኮረብታ እና ማንቸስተር-ፓልማይራ አካባቢ

ምስል
ፎቶ ፪

ወደ ሰሜን ሲመለከቱ፣ ይህ ፎቶ በማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ ውስጥ ያለውን የከሞራ ኮረብታ ያሳያል። ኮረብታው በፎቶው ከቀኝ ማዕዘን እስከ ፎቶው መካከል ግማሽ ድረስ እንደሆነ ይታያል። በኮረብታው በስተሰሜን በኩል ያለው ሀውልት መልአኩ ሞሮኒን እና የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣትን የሚያከብር ነው። የከሞራ ኮረብታ ከቅዱስ ጥሻው ፰ ኪሎ ሜትር ወደ ደቡብ ምስራቅ ያለ ነው። በፎቶው ላይ ከፍ ብሎ የሚታየውም ፓልማይራ ነው፣ ይህም ፮ ተኩል ኪሎ ሜትር የሚርቅ ነው። የስሚዝ የእርሻ ቦታ እና ቅዱስ ጥሻው የሚገኙት በፎቶው በከፍተኛው በስተግራ በኩል ነው።

ታላቅ ድርጊቶች፥ የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ በመጀመሪያው ራዕይ ጊዜ በዚህ ቦታ ይኖሩ ነበር (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፫)። በ፵፳፩ ዓ.ም.፣ ሞሮኒ በከሞራ ኮረብታ የህዝቡን ቅዱስ ታሪክ የያዙትን የወርቅ ሰሌዳዎችን ቀበረ (ቃላት ፩፥፩–፲፩ሞር. ፮፥፮ሞሮኒ ፲፥፩–፪)። ይህም ሞሮኒ ሰሌዳዎችን የት እንደሚያገኛቸው ለጆሴፍ። ሞሮኒ እነዚህን ለእርሱ በ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) አሳልፎ አስረከበ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፭፻፳፰፥፳ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፫–፴፭፣ ፶፩–፶፬፣ ፶፱)።