የጥናት እርዳታዎች
13. የናቩ አዳራሽ ቤት


13. የናቩ አዳራሽ ቤት

ምስል
ፎቶ ፲፫

ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ቤተሰቡ ወደ አዳራሽ ቤት በነሀሴ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) ገቡ። በኋላም በቤቱ በስተምስራቅ በኩል ተጨማሪ ክፍሎች ተሰርተው በአጠቃላይ ፳፪ ክፍሎች ነበሩት። ከጥር ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) መጀመሪያ ጀምሮ፣ ኤበነዝር ሮቢንሰን ቤቱን እንደ ሆቴል አስተዳደረው፣ እናም ነቢዩ ስድስት ክፍሎችን ለቤተሰቡ ጠበቀ። ቤቱ እንደ ናቩ ማህበራዊ ማእከል ያገለግል ነበር። አስፈላጊ ታላቅ ሹመቶችን ነቢዩ በእዚህ ይቀበላቸው ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ በሰኔ ፳፯፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ነቢዩ ጆሴፍ እና ወንድሙ ሀይረም በካርቴጅ፣ ኢለኖይ በጥይት ተገደሉ፣ እናም ከመቀበራቸው በፊት ሰውነቶቻቸው ወደ እዚህ ቤት ለለቅሶ መጥተው ነበር። ወደ ናቩ ከመምጣቱ በፊት ጆሴፍ ይኖርበት ከነበረው የፍልጥ እንጨት ቤት በስተምስራቅ በኩል በሜይን ስትሪት ተሻግሮ በሚገኘው በቤተሰብ የመቃብር ቦታ ውስጥ ተቀበሩ። ኤማ ስሚዝ በአዳራሽ ቤት ውስጥ እስከ ፲፰፻፸፩ (እ.አ.አ.) ድረስ ኖረች። ከእዚያም ወደ ናቩ ቤት ገባች፣ በእዚያም በ፲፰፻፸፰ (እ.አ.አ.) ሞተች።