ምዕራፍ ፲፱
ኔፊ ሰሌዳዎችን ከብረት አፈር ሠርቶ የህዝቡን ታሪክ መዘገበ—የእስራኤል አምላክ ሌሂ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀበት ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ይመጣል—ስለእርሱ መከራና ስቅለት ኔፊ ተናገረ—አይሁዶች ይጠላሉ፣ እናም ወደጌታ እስከሚመለሱ እስከ ኋለኞቹ ቀናት ድረስ ይበተናሉ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ አዘዘኝ፣ ስለዚህ የህዝቤን ታሪክ እፅፍባቸው ዘንድ ሀሰሌዳዎችን ከብረት አፈር ሰራሁ። እናም በሰሌዳዎቹ ላይ ለየአባቴን ታሪክ፣ ደግሞም የምድረበዳ ጉዞአችንንና የአባቴን ትንቢቶች ፃፍኩባቸው፤ ደግሞም ብዙዎቹን የእኔን ትንቢቶች ፃፍኩባቸው።
፪ እናም እነርሱንም በሰራሁ ጊዜ ሀእነዚህን ሰሌዳዎች እንድሰራ ከጌታ እንደምታዘዝ አላወቅሁም ነበር፤ ስለዚህ የአባቴን ታሪክና የአባቶቹን የትውልድ ሐረግ፣ እናም በምድረበዳ የነበሩትን አብዛኞች ገጠመኞቻችን የተፃፉት በእነዚያ እኔ ባልኳቸው የመጀመሪያ ሰሌዳዎች ላይ ነው፤ ስለዚህ እኔ ለእነዚህን ሰሌዳዎች ከመስራቴ በፊት የተከሰቱት ነገሮች በይበልጥም በመጀመሪያዎቹ ሰሌዳዎች በእውነትም ተጠቅሰዋል።
፫ እናም እነዚህን ሰሌዳዎች በትዕዛዝ ከሰራሁ በኋላ፣ እኔ ኔፊ፣ አገልግሎትና ትንቢቶችን ግልፅና አስፈላጊ የሆኑትን ክፍሎች፣ ሀበእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ እንድፅፍ ትዕዛዝ ተቀበልኩ፤ እና የሚፃፉት ነገሮች ይህችን ምድር ለሚይዙት ህዝቦቼ መመሪያ ይሆኑ ዘንድ፣ ደግሞም እኔ ለማላውቀው፣ ጌታ ለሚያውቀው፣ ለለመልካም ዓላማው ይሆኑ ዘንድ ይጠበቃሉ።
፬ ስለዚህ እኔ ኔፊ፣ በሌሎች ሰሌዳዎች ላይ የህዝቦቼን ጦርነት፣ ፀብ፣ እና ጥፋትን ታሪክ፣ ወይም የተዘረዘረ ታሪክ መዘገብኩ። እናም ይህን አደረኩ፣ ህዝቤንም እኔ ስሄድ ምን ማድረግ እንዳለባቸውና፣ ከጌታ ተጨማሪ ትዕዛዝ እስከሚመጣ ድረስ፣ እነዚህ ሰሌዳዎች ከአንዱ ትውልድ ወደሌላው ወይም ከአንዱ ነቢይ ወደሌላው መተላለፍ እንደሚገባቸው አዘዝኩኝ።
፭ እነዚህን ሰሌዳዎች እንዴት ሀእንደሰራሁ ከዚህ በኋላ ይነገራል፣ እናም እነሆ እንደተናገርኩት እቀጥላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እጅግ የተቀደሱትን ነገሮች ህዝቦቼ ያውቁት ዘንድ ለእንዲጠብቁ ነው።
፮ ይሁን እንጂ ሀቅዱስ ናቸው ብዬ የማስባቸውን ካልሆነ በስተቀር ምንም ነገር በሰሌዳዎቹ ላይ አልፅፍም። እና አሁን ስህተት ብሰራ፣ የጥንቶቹም ቢሆኑ ስህተት ሰርተዋል፤ በሌሎች ሰዎች ስህተት ግን ራሴን አላመካኝም፣ ነገር ግን በስጋ መሰረት በውስጤ ባለው ለደካማነት ራሴ አመካኛለሁ።
፯ አንዳንድ ሰዎች ለስጋም፣ ለነፍስም ታላቅ ዋጋ አለው ብለው የሚያስቡትን ነገሮች ሌሎች ሀይንቁታል፣ በእግራቸውም ይረግጡታል። አዎን የእስራኤልንም አምላክ እንኳን ሰዎች በእግራቸው ለይረግጡታል፤ በእግራቸው ይረግጡታል እላለሁ ነገር ግን በሌላ አባባል እናገረዋለሁ—ንቀውታል፣ እናም የምክሩን ድምፅ አላዳመጡም።
፰ እናም እነሆ እንደመልአኩ ቃላት፣ አባቴ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀበት ሀከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ፣ እርሱ ለይመጣል።
፱ እናም በኃጢኣታቸው ምክንያት ዓለም ሁሉ ዋጋ እንደሌለው ነገር ይፈርዱበታል፤ ስለዚህ ይገርፉታል፣ እርሱም ይህን ይቀበላል፤ እናም ይመቱታል፣ እርሱም ይህን ይቀበላል። አዎን ሀይተፉበታል፣ እና በቸርነቱና ለሰው ልጆች ባለው ፅናት ምክንያት ይህንንም ይቀበለዋል።
፲ እናም ከግብፅ ከባርነት ሀየወጡትና ደግሞም በምድረበዳ ውስጥ በእርሱ የተጠበቁት አባቶቻችን ለአምላክ፣ አዎን ሐየአብርሃም አምላክ፣ የይስሀቅም፣ እና የያዕቆብ አምላክ መእንደዜኖቅ ቃላት መሰረት ሠእንዲሰቀል፣ እና እንደ ኔዩም ቃላት መሰረት ረእንዲሰዋና፣ በባህር ደሴቶች ለሚኖሩ በተለይም ሰለእስራኤል ቤት የሞቱ ምልክት ስለሚሰጠው የሶስት ቀን ሸጨለማ እንደተናገረው እንደ ቀዜኖስ ቃል በበመቃብር እንዲቀበር፣ በመልአኩ ቃላት መሰረት፣ እራሱን እንደሰው በኃጢኣተኞች እጅ ተአሳልፎ ይሰጣል።
፲፩ ነቢዩ እንዲህ ተናገረ—ጌታ እግዚአብሔር በዚያ ቀን የእስራኤልን ቤት ሁሉ አንዳንዶቹን በቅንነታቸው የተነሳ፣ ለታላቅ ደስታቸው፣ ለደህንነታቸው በድምፁ፣ ሌሎቹን ሀበነጎድጓድና በወጀብ ኃይሉ መብረቅ፣ በማዕበል በእሳትና በጭስና፣ ለበጨለማ ጭጋግ፣ እንዲሁም ሐምድርን በመክፈትና በሚነሱት መተራሮች ሠይጎበኛቸዋል።
፲፪ እናም ነቢዩ ሀዜኖስ እነዚህ ነገሮች ለሁሉ መሆን አለባቸው ብሏል። የምድርም ሐዓለቶች መከፈል አለባቸው፤ እና በምድር ሁከት ምክንያት፣ በባህር ደሴቶች የሚገኙት ንጉሶች እንዲህ እንዲጮሁ በእግዚአብሔር መንፈስ ተፅዕኖ ይሰማቸዋል፣ የፍጥረት አምላክ ይሰቃያል ይላሉ።
፲፫ እናም ነቢዩ፣ በኢየሩሳሌም ስላሉት እንዲህ ይላል፥ የእስራኤልን አምላክ ሀስለሰቀሉና፣ ምልክቶቹን፣ ድንቆቹን በማስወገድና፣ የእስራኤልን አምላክ ክብርና ኃይል በመቃወም ልቦቻቸው ስለሳቱ፣ በሁሉም ህዝቦች ለይሰቃያሉ።
፲፬ እናም ልባቸው ስለሳቱና፣ የእስራኤልን ቅዱስ ሀስለናቁ በስጋ ይንከራተታሉ፣ እናም ይጠፋሉ፣ እናም ለየሚፏጭባቸውና ሐየተራቁም ይሆናሉ፣ በሁሉም ሀገሮች የተጠሉም ይሆናሉ ይላል ነቢዩ።
፲፭ ይሁን እንጂ በእስራኤሉ ቅዱስ ላይ ልባቸውን ሀየማይስቱበት ቀን ሲመጣ፣ ያኔም ከአባታቸው ጋር የገባውን ለቃል ኪዳን ያስታውሳሉ፣ ይላል ነቢዩ።
፲፮ አዎን በዚያን ጊዜ የባህር ሀደሴቶችንም ያስታውሳል፤ በነቢዩ ዜኖስ ቃል መሰረት፣ አዎን የእስራኤልንም ቤት በሙሉ ከአራቱም የምድር ማዕዘናት ለእሰበስባቸዋለሁ አለ ጌታ።
፲፯ አዎን እናም ምድር በሙሉ የጌታን መድኃኒት ሀያያሉ፣ አለ ነቢዩ፤ እያንዳንዱ ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ህዝብም ይባረካል።
፲፰ እናም እኔ ኔፊ እነዚህን ነገሮች ለህዝቤ የፃፍኩት ምናልባት ጌታ መድኃኒታቸውን እንዲያስታውሱ ለማስረዳት ነው።
፲፱ ስለዚህ ሀእነዚህን ነገሮች ያገኟቸው እንደሆነ ለሁሉም ለእስራኤል ቤት እናገራለሁ።
፳ እነሆ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መገጣጠሚያዬ እስከሚደክም ድረስ የሚያስጨንቀኝ የመንፈስ ስራ አለኝ፤ እነሆ ጌታ እንደጥንት ነቢያት ስለእነርሱ በማሳየት መሀሪ ባይሆንልኝ ኖሮ እኔም ደግሞ በጠፋሁ ነበር።
፳፩ እናም እርሱ በእርግጥ ለጥንት ሀነቢያት ለስለእነርሱ ገልጦላቸዋል፤ ደግሞም ለብዙዎች ስለእኛ አሳይቷቸዋል፣ ስለዚህ እኛም ደግሞ በነሀስ ሰሌዳዎች ላይ ተፅፈዋልና ልናውቃቸው ያስፈልገናል።
፳፪ አሁን እንዲህ ሆነ፣ እኔ ኔፊ ለወንድሞቼ እነዚህን ነገሮች አስተማርኳቸው፤ እና እንዲህ ሆነ ጌታ በጥንት ሰዎች መካከል በሌሎች ምድር ውስጥ ያደረጋቸውን ነገሮች በተመለከተ ያውቁ ዘንድ ሀበነሀስ ሰሌዳዎች ላይ የተቀረፁትን ብዙ ነገሮች አነበብኩላቸው።
፳፫ እናም ሀበሙሴ መፅሐፍት ላይ ከተፃፉት ብዙ ነገሮችን አነበብኩላቸው፤ ነገር ግን በይበልጥ ስለጌታ ስለመድኃኒታቸው እንዲያምኑ አስረዳቸው ዘንድ በነቢዩ ለኢሳይያስ የተፃፉትን አነበብኩላቸው፤ እነሆ ለእኛ ሐጥቅምና ትምህርት ይሆኑ ዘንድ ሁሉንም ጥቅሶች ከእኛ ጋር መአመሳሰልኩ።
፳፬ ስለዚህ ለእነርሱ እንዲህ ስል ተናገርኩ—እናንተ የተገነጠላችሁ ሀቅርንጫፎች የሆናችሁ የእስራኤል ቤት ቅሪቶች የተፃፉትን የነቢዩን ቃል አድምጡ፤ እናንተም ተገንጥላችሁ እንደመጣችሁባቸው ወንድሞቻችሁ አይነት ተስፋ ይኖራችሁ ዘንድ ለመላው ለእስራኤል ቤት የተፃፉትን የነቢዩን ቃል አድምጡ፣ ከእናንተም ጋር አመሳስሏቸው፤ እንደዚህም ነቢያት ፅፈዋልና።