ምዕራፍ ፯
ሞርሞን የኋለኛው ዘመን ላማናውያን በክርስቶስ እንዲያምኑ፤ ወንጌሉን እንዲቀበሉ እናም እንዲድኑ አጥብቆ ጋበዛቸው—መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሁሉ መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲሁ ያምናሉ። በ፫፻፹፭ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ እነሆ፣ የአባቶቻቸውን ነገሮች ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ቃሌን ከሰጣቸው፣ ለነዚህ ለተረፉት የዚህ ሕዝብ ሀቅሪት ለሆኑት ጥቂት እናገራለሁ፤ አዎን፣ የእስራኤል ቤት ቅሪት ለሆናችሁ ለእናንተ እናገራለሁ፤ እናም የምናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፥
፪ እናንተ ሀከእስራኤል ቤት መሆናችሁን እወቁ።
፫ ንሰሃ መግባት እንዳለባችሁ፣ አለበለዚያ ለመዳን እንደማትችሉ እወቁ።
፬ የጦር መሳሪያዎቻችሁን መጣል እንዳለባችሁ እወቁ፣ እናም ከእንግዲህ በደም መፍሰስ በምንም አትደሰቱ፣ እናም ከእንግዲህ እግዚአብሔር ካላዘዛችሁ በስተቀር የጦር መሳሪያዎቻችሁን በድጋሚ አታንሱ።
፭ አባቶቻችሁ ያወቁትን ሀለማወቅና፣ እናም ለኃጢአቶቻችሁ ሁሉና ለክፋቶቻችሁ ንሰሃ መግባት እንዳለባችሁ፣ እናም በአይሁዶች የተገደለው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑንና፣ እርሱም በአብ ኃይል ዳግም እንደተነሳ፣ ስለዚህ በመቃብር ላይ ለድል እንዳደረገ ሐማመን እንዳለባችሁ እወቁ፣ እናም ደግሞ በእርሱም የሞት መውጊያ ተውጣለች።
፮ እናም እርሱም ሰውም ሀበፍርድ ወንበር ፊት ለመቆም የሚነሳበትን የሙታንን ለትንሣኤ ያመጣል።
፯ እናም በእርሱም ፊት በፍርድ ቀን ሀጥፋተኛ ሳይሆን የሚገኝ፣ ለአንድ አምላክ የሆኑትን፣ አብ፣ እናም ወልድ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን መጨረሻ በሌለው ሐደስታ ያለማቋረጥ ከበላይ መዘማሪዎች ጋር ለማወደስ በእግዚአብሔር መንግስት በፊቱ ሠእንዲኖር የሚሰጥበትን ለዓለም ረቤዛነትን አምጥቷል።
፰ ስለዚህ ንሰሃ ግቡና፣ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፣ እናም በዚህ መዝገብ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሀከአይሁዶች ለአህዛብ የሚመጣውን ለመዝገብ ውስጥ የተመሰረተውን የክርስቶስን ሐወንጌል በጥብቅ ያዙ፣ ይህም መዝገብ ከአህዛብ መለእናንተ ይመጣል።
፱ እነሆም፣ ይህም እናንተ ሀእንድታምኑበት ነው ለየተፃፈው፤ እናም ያንን የምታምኑት ከሆነ፣ ይህንንም ደግሞ ታምናላችሁ፤ እናም ይህንን የምታምኑ ከሆነ ስለአባቶቻችሁና፣ ደግሞ በእግዚአብሔር አማካኝነት በመካከላቸው የተሰራውን ድንቅ ሥራዎች ጭምር ታውቃላችሁ።
፲ እናም ደግሞ የያዕቆብ ዘር ቅሪት መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ ስለዚህ ከመጀመሪያዎቹ የቃል ኪዳን ህዝቦች ጋር ተቆጥራችኋል፣ እናም በክርስቶስ የምታምኑ ከሆነ፣ እናም እርሱ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት፣ የአዳኛችንን ሀምሳሌ በመከተል መጀመሪያ በውኃ በኋላም በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ የምትጠመቁ ከሆነ በፍርድ ቀን ለእናንተ መልካም ይሆንላችኋል። አሜን።