ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፲፬


ምዕራፍ ፲፬

መልአክ በአህዛብ ላይ ስለሚመጡት በረከቶችና እርግማን ለኔፊ ነገረው—ሁለት ቤተክርስቲያናት ብቻ አሉ፥ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያን እና የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን—በሁሉም ሀገሮች ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱሳን በታላቋና በርኩሰት ቤተክርስቲያን ተሰድደዋል—ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ዓለም መጨረሻ ይፅፋል። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ይሆናል፣ የእግዚአብሔርን በግ የማሰናከያውን ድንጋይ በመውሰድ እራሱን በቃል፣ ደግሞም በሀይል፣ እንዲሁም በስራው፣ ለእነርሱ በሚገልፅበት ጊዜ አህዛብ እርሱን ካዳመጡ—

እናም በአባትህ ዘሮች መካከል እንዲቆጠሩ ዘንድ በእግዚአብሔር በግ ላይ ልባቸውን ካላጠጠሩ፣ አዎን፣ ከእስራኤልም ቤት መካከልም ይቆጠራሉ፤ እነርሱም በቃልኪዳኑ ምድር ለዘለአለም የተባረኩ ህዝቦች ይሆናሉ፤ ከዚህ ወዲያም ወደምርኮ አይመጡም፤ ከዚህም ወዲያ የእስራኤል ቤት ከሌሎች ህዝቦች ጋር አይደባለቁም።

እናም በዲያብሎስና በልጆቹ በተቋቋመው በታላቋና በርኩሰቱ ቤተክርስቲያን የሰዎችን ነፍስ ወደ ሲኦል ይወስድበት ዘንድ የተቆፈረው ትልቁ ጉድጓድ—አዎን፣ ሰዎችን ለማጥፋት የተቆፈረው ታላቁ ጉድጓድ በፍጹም እንዲጠፉ ዘንድ በቆፈሩት ይሞላል ይላል የእግዚአብሔር በግ፤ መጨረሻ ወደሌለው ወደዚያ ሲኦል ካልጣላቸው በሰተቀር፣ የነፍስ መጥፋት አይደለም።

እነሆም ይህ በዲያብሎስ ምርኮ፣ እናም ደግሞ በእግዚአብሔር ፍትህ መሰረት በእርሱ ፊት ኃጢያትንና እርኩሰትን ባደረጉት ላይ ሁሉ ነው።

እናም እንዲህ ሆነ መልአክ እንዲህ ብሎ ለእኔ ለኔፊ ተናገረኝ—አንተ አህዛብ ንስሀ ከገቡ መልካም እንደሚሆንላቸው አይተሀል፣ አንተም ደግሞ ጌታ የእስራኤልን ቤት በተመለከተ የገባውን ቃል ኪዳን ታውቃለህ፣ እናም ማንም ንስሀ የማይገባ መጥፋት እንዳለበት ሰምተሀል።

ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር በግ ላይ ልባቸውን ቢያጠጥሩ ለአህዛብ ወየው

በአንድም መንገድ ይሁን በሌላ ዘለዓለማዊ በሚሆነው ስራ—እነርሱ ሰላምንና ዘለዓለማዊ ህይወትን እንዲመርጡ፣ ወይም እነርሱን ልባቸው በማጣጠርና አዕምሮአቸው በማሳወር ወደ ምርኮ፣ እናም ደግሞ እኔ በተናገርኩት በዲያብሎስ ምርኮ መሰረት እነርሱን ወደጊዜያዊና መንፈሳዊ ጥፋት እንዲሰጡ በሚያደርገው ስራ፣ እኔ ታላቅና ድንቅ ስራን በሰው ልጆች መካከል የምሰራበት ጊዜው ይመጣል፣ ይላል የእግዚአብሔር በግ።

እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ እንዲህ አለኝ፥ አብ ለእስራኤል ቤት የገባውን ቃልኪዳኖች ታስታውሳለህን? እኔም አዎን አልኩት።

እናም እንዲህ ሆነ፣ እንዲህ አለኝ—የኃጢኣት እናትን፣ መስራቿ ዲያብሎስ የሆነውን ታላቋና የርኩሰት እናት የሆነችው የርኩሰት ቤተክርስቲያን ተመልከት።

እርሱም እንዲህ አለኝ—እነሆ ሁለት ቤተክርስቲያናት ብቻ አሉ፤ አንዷ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያን ናት፣ ሌላዋም የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን ናት፤ ስለዚህ ማንኛውም የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያን አባል ያልሆነ የርኩሰት እናት ከሆነችው የታላቂቷ ቤተክርስቲያን አባል ይሆናል፤ እናም እርሷ የምድር ሁሉ ጋለሞታ ነች።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ የምድርን ሁሉ ጋለሞታ አየሁና ተመለከትኩ፣ እርሷም በብዙ ውኃዎች ላይ ተቀምጣ ነበር፤ እናም እርሷ በሁሉም ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝቦች መካከል በምድር ላይ ሁሉ ትገዛለች።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያንን ተመለከትኩ፣ እናም በብዙ ውኃዎች ላይ በተቀመጠችው ጋለሞታ ክፋትና ርኩሰቶች ምክንያት ቁጥሯ ጥቂት ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቅዱሳን የሆኑት የበጉ ቤተክርስቲያን አባላቶቿም ደግሞ በምድር ገፅ ላይ ሁሉ እንደነበሩ ተመለከትኩ፤ እናም በተመለከትኳት ትልቅ ጋለሞታ ክፋት ምክንያት በምድር ገፅ ላይ የሚገዙት ቦታዎች ትንሽ ነበሩ።

፲፫ እናም እንዲህ ሆነ ታላቂቱ የርኩሰት እናት ከእግዚአብሔር በግ ጋር ለመዋጋት በምድር ገፅ ላይ ሁሉ ከሁሉም የአህዛብ ሀገሮች መካከል ብዛትን በአንድ ላይ እንደሰበሰበች ተመለከትኩ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ኔፊ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ የእግዚአብሔር ቁጣ በታላቋና በርኩሰት ቤተክርስቲያን ላይ ፈስሶ በዚያም በምድር ባሉ ሀገሮችና ነገዶች ሁሉ መካከል ጦርነቶችና የጦርነት ወሬዎች እንደነበሩ ተመለከትኩ።

፲፮ እናም ጦርነቶችና የጦርነት ወሬዎች በሁሉም የርኩሰት እናት በሆነችው በሚመሩት ሀገሮች መካከል ሲጀመር መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረኝ—እነሆ የእግዚአብሔር ቁጣ በጋለሞታዎች እናት ላይ ነው፣ እናም እነሆ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትመለከታለህ—

፲፯ እናም የእግዚአብሔር ቁጣ በጋለሞታዎች እናት፣ በምድር ሁሉ ታላቋና በተረኮሰች በዲያብሎስ በተመሰረተች ቤተክርስቲያን ላይ የሚፈስበት ቀን ሲመጣ፣ ከዚያም በእዚያ ቀን የእስራኤል ቤት ለሆኑት ለህዝቦቹ የገባውን ቃል ኪዳኖች ለማሟላት መንገድን በማዘጋጀት የአብ ስራ ይጀምራል።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ተመልከት!

፲፱ እናም ተመለከትኩና፣ አንድ ሰው አየሁ፣ እርሱም ነጭ ካባ ለብሶ ነበር።

እናም መልአኩ አለኝ፥ እነሆ ከበጉ አስራ ሁለት ሐዋርያት አንዱ

፳፩ እነሆ እርሱ ከእነዚህ ነገሮች ቀሪዎቹን ይመለከታል፣ እንዲሁም ይፅፋል፣ አዎን፣ ደግሞም ብዙ ነገሮችን ተመልክቶም ይፅፋል።

፳፪ እናም ደግሞ እርሱ ስለ ዓለም ፍፃሜ ይፅፋል።

፳፫ ስለዚህ እርሱ የሚፅፋቸው ነገሮች ትክክልና እውነት ናቸው፤ እናም እነሆ እነርሱ ከአይሁድ አፍ ሲወጡ በተመለከትካቸው መፅሐፉ ውስጥ የፃፉት ናቸው፣ ከአይሁድም አፍ በወጡበት ጊዜ ወይም መፅሐፉ በአይሁድ አፍ በወጡበት ጊዜ የተፃፉት ነገሮች ግልፅና የጠሩ እንዲሁም እጅግ የከበሩና ለሰዎች ሁሉ ለመረዳት ቀላል ነበሩ።

፳፬ እናም እነሆ ይህ የበጉ ሐዋርያ የሚፅፋቸው ነገሮች አንተ ያየሀቸው ብዙ ነገሮች ናቸው፤ እነሆ ቀሪዎቹን አንተም ትመለከታለህ።

፳፭ ነገር ግን ከዚህ በኋላ የምታያቸውን ነገሮች እንዳትፅፍ፤ የእግዚአብሔር በግ ሐዋርያ የሆነው መፃፍ እንዳለበት ጌታ እግዚአብሔር ሾሞታልና።

፳፮ እናም ደግሞ ለነበሩም ሌሎች ሁሉንም ነገሮች አሳይቶአቸዋል፣ እነርሱም ፅፈዋቸዋል፤ እንዲሁም በጉ ውስጥ ካሉት እውነታ መሰረት፣ ጌታ በፈቀደ ጊዜ ለእስራኤል ቤት በንፅህና ይመጡ ዘንድ ታትመዋል

፳፯ እናም እኔ ኔፊ በመልአኩ ቃል መሰረት የበጉ ሐዋርያ ስም ዮሐንስ መሆኑን ሰምቼአለሁም እመሰክራለሁም።

፳፰ እናም እነሆ እኔ ኔፊ፣ የተቀሩትን ያየሁአቸውንና የሰማሁአቸውን ነገሮች እንዳልፅፍ ተከልክዬአለሁ፣ ስለዚህ እኔ የፃፍኳቸው ነገሮች በቂ ናቸው፤ እናም እኔ ካየሁአቸው ጥቂት ነገሮች ብቻ ጽፌአለሁ።

፳፱ እኔም አባቴ ያያቸውን ነገሮች እንዳየሁ እመሰክራለሁ፣ እናም የጌታ መልአክ እንዳውቃቸው አደረገኝ።

አሁንም እኔ በመንፈስ በተወሰድኩ ጊዜ ስላየኋቸው ነገሮች መናገሬን አቆማለሁ፤ እናም ምንም እንኳን ያየሁአቸው ነገሮች ሁሉ ባይፃፉም የፃፍኳቸው ነገሮች እውነት ናቸው፣ እናም ይህ ነው። አሜን።