አጠቃላይ ጉባኤ
በሁሉም አስተሳሰብ ክርስቶስን እሹ
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በሁሉም አስተሳሰብ ክርስቶስን እሹ

ፈተናን መፋለም ሕይወት ሙሉን የሚፈጅ ታታሪነትን እና ታማኝነትን ይጠይቃል። ነገር ግን እባካችሁን ጌታ ሊረዳን ዝግጁ እንደሆነ አወቁ።

በቅኔያዊ የማክብር መዝሙሩ፣ ዘማሪው እንዲህ አወጀ፤

“አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።

“አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።

“ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ።”1

በቅኔያዊ የፍቺ ትይዩነት፣ ዘማሪው የጌታን ሁሉን አዋቂ መለኮታዊ ባህሪይ ያሞግሳል ምክንያቱም እርሱ በእውነትም የነብሶቻችንን ሁሉም ገጽታ ያውቃልና።2 በዚህ ህይወት ለእኛ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ስለሚያውቅ፣ አዳኝ በሙሉ ሃሳብ እርሱን እንድንሻ እና በሙሉ ልብ እንድንከተለው ይጋብዘናል።3 ይህ ከፊቱ መራመድ እንደምንችል እንዲሁም ምሪቱ በሕይወታችን ውስጥ ከጨለማ ተፅዕኖ እንደሚጠብቀን ቃል ኪዳን ይሰጠናል።4

በሙሉ ሃሳብ እርሱን መሻት እና በሙሉ ልባችን ክርስቶስን መከትል አእምሮአችንን እና ፍላጎቶቻችንን ከእርሱ ጋር ማዛመድን ይጠይቃል።5 ይሄን ዝምድና ቅዱሳን መጽሐፍት “በጌታ [መቆም]“ ይሉታል።6 ይሄ የድርጊት አካሄድ ማለት ህይወታችንን ከክርስቶስ ወንጌል7ጋር አስማምተን በቀጣይነት መምራት እና መልካም በሆኑት ነገሮች ሁሉ ቀን በቀን ማተኮር ነው። ያኔ ብቻ ነው “አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም” እናም “ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ [መጠበቅን]” የምናሳካው።8 አዳኙ እራሱ የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን በጥቅምት 1831 (እ.አ.አ) እንዲህ አዘዘ፤ “እነዚህን ነገሮች በልባችሁ አኑሩዋቸው፣ እናም የዘለአለም ማስተዋልም በአዕምሮዎቻችሁ ላይ ይረፍ።”9

ምንም እንኳን ቀጣይነት ባለው ጥረቶቻችን ጌታን ብንሻምር፣ ተገቢ ያልሆኑ ሃሳቦች አዕምሮአችን ውስጥ ልገቡ ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነት ሃሳቦች እንዲገቡ ሲፈቀድላቸው እና እንዲቆዩ ሲጋበዙ፣ የልቦቻችንን ፍላጎቶች ቅርፅ ያሲዛሉ እናም በዚህ ሕይወት ውስጥ ምን እንደምንሆን እንዲሁም በመጨረሻ ለዘላለም ምን እንደምንወርስ ይመሩናል።10 ሽማግሌ ኔይል ኤ. ማክስዌል በአንድ ወቅት ይህን መርህ እንዲህ ብለው አጉልተዋል፣ “ፍላጎቶች የውጤቶችን ደረጃዎች ይወስናሉ፣ ይህም ‘ብዙዎች ተጠርተዋል፣ ግን ጥቂቶች ብቻ ተመርጥዋል’” ለሚለው ምክንያት ጨምሮ።11

ጥንታዊ እና ዘመናዊ ነብያቶቻችን በሕይውት ውስጥ መንፈሳዊ ስበታችንን ላለማጣት፣ ግራ ላለመጋባት፣ እና ተስፋ ላለመቁረጥ ፈተናን እንድንቋቋም በተደጋጋሚ አስገንዝበውናል።

በምሳሌያዊ አነጋገር፣ ለፈተናዎች መገዛት የብረት እቃ ይዞ ወደ ማግኔት እንድመቅረብ ነው። የማይታየው የማግኔት ሀይል የብረት እቃውን ወደራሱ ይስበዋል እናም አጥብቆ ይይዘዋል። ማግኔቱ ከእቃው ሀይሉን የሚያጣው እቃው እርቆ ሲቀመጥ ብቻ ነው። ስለዚህ፣ ልክ ማግኔት እሩቅ ባለ የብረት እቃ ላይ ሃይሉን መጠቀም እንደማይችለው ሁሉ፣ ፈተናዎችን ስንቋቋም፣ እየጠፉ ይሄዳሉ እና በአእምሮአችን እና በልባችን፣ እናም አልፎ በተግባራችን ላይ ሀይል ያጣሉ።

ይሄ ማነጻጸሪያ ከተወሰነ ጊዜ በፊት የቤተክረስቲያን በጣም ታማኝ የሆነ አባል ያጋራኝን ተሞክሮ ያስታውሰኛል። ይህች አባል በአንድ ጠዋት ስትነቃ፣ ከዚያ በፊት በፍጹም አጋጥሟት የማታውቀው ተገቢ ያልሆነ ሃሳብ ሳይጠበቅ በአእምሮዋ እንደገባ ነገረችኝ። ምንም እንኳን ቢያስገርማትም፣ ለራሷና ለዛ ሃሳብ “አይሆንም” በማለት እና ካልተፈቀደለት ሃሳብ አዕምሮዋን በማዞር መልካም በሆነ ነገር በመተካት ወዲያውኑ በሁኔታው ላይ ተቃራኒ በሆነ መልኩ ተገበረች። የስነ ምግባር ምርጫውን በቅድስና ሲትለማመድ፣ ያ አሉንታዊ የሆነ ያልተፈለገ ሃሳብ ወዲያው እንደጠፋ ነገረችኝ።

ሞሮኒ በክርስቶስ የማያምኑ የነበሩትን ንሰሃ እንዲገቡ ሲጠራቸው፣ በሙሉ ልባቸው፣ ንጹህ ካልሆነ ነገር ሁሉ እራሳቸውን እንዲያስወግዱ አስጠንቅቋቸው ነበር። ከዛም ባለፈ፣ ወደ ፈተና እንዳይወድቁ፣ እግዚአብሔርን በማይሰበር ጽናት እንዲጠይቁ ጋበዛቸው።12 እነዚህን መርሆዎች በህይወታችን መተግበር እነሱን ከማመን በዘለለ፤ አእምሮአችንን እና ልባችንን ወደነዚህ መለኮታዊ መርሆዎች ማቅናት ይጠይቃል። ይሄ ማስተካከያ በአዳኛችን ላይ ከመመካት በተጨማሪ የየለት እና ቋሚ የግል ጥረትን ከእኛ ይጠይቃል፣ ምክንያቱም የእኛ ምድራዊ ዝንባሌዎቻችን በራሳቸው አይሰወሩምና። ፈተናን መፋለም ሕይወት ሙሉን የሚፈጅ ታታሪነትን እና ታማኝነትን ይጠይቃል። ነገር ግን በግል ጥረቶቻችን ውስጥ ጌታ ሊረዳን ዝግጁ እንደሆነ እና እስከመጨረሻ ከጸናን ለየት ላሉ በረከቶች ቃል እንደገባ እባካችሁ እወቁ።

ለየት ባለ ከባድ ጊዜ ወቅት ጆሴፍ ስሚዝ እና በሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ አብረውት ታስረው የነበሩ ሰዎች ከሃሳባቸው በስተቀር በምንም ነገር ነፃነት አልነበራቸውም፣ ጌታ የሚያግዝ ምክርን እንዲሁም ለሁላችንም የተበረከተን ቃል ኪዳንን ሰጠ።

“አንጀትህም ለሁሉም ሰው እና ለእምነት ቤተ ሰዎች በልግስና ይሞላ፣ እና ምግባረ በጎነትም ሳያቋርጥ አስተሳሰብህን ያሳምር፤ ከዚያም ልበ ሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል፤ …

“መንፈስ ቅዱስም የዘወትር ባልንጀራህ ይሆናል፣ እና በትርህም የማይቀየር የፅድቅ እና የእውነት በትር ይሆናል።”13

ይህን በማድረግ ቅዱስ ሃሳቦች ቀጣይነት ባለው መልኩ አዕምሮአችንን ያስውቡታል እንዲሁም ንፁህ ምኞቶች ወደ ጽድቅ ተግባሮች ይመሩናል።

ሞሮኒ ህዝቦቹን በስጋዊ ምኞቶች እራሳቸውን እንዳይዘፍቁ አስታወሰ።14 የስጋ ምኞት የሚለው ቃል ጥልቅ የሆነ ፍላጎት እና ለሆነ ነገር ተገቢ ያልሆነ ምኖት ማለት ነው።15 ግለሰብን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ከመጠበቅ፣ መልካምን ከመስራት፣ ቀና ከመሆን እና ከመሳሰሉት ይልቅ እራስ ወዳድ ተግባራት ላይ ወይም አለማዊ ንብረቶች ላይ እንዲያተኩር የሚያደርጉ ጨለማዊ ሃሳቦች እና ክፉ ፍላጎቶችን ያካትታል። ብዙውን ጊዜ በጣም ስጋዊ በሆነ የነብስ ስሜቶች ይገለጻል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ንፁህ አለመሆን፣ ብልግና፣ ጥላቻ፣ ቁጣ፣ ጠብ፣ ምቀኝነቶች የመሳሰሉ ስሜቶችን ለየ።16 ከሁሉም የስጋዊ ምኞት ክፉ መገለጫዎች ባለፈ፣ ጠላት የተሳሳተ ነገር እንድናደርግ ሲፈትነን እንደ ሚስጥራዊ እና አታላይ መሳሪያ እንደሚጠቀም መርሳት የለብንም።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የነፍሳችን አዳኝ በሆነው በደህንነት አለት ላይ ስንመካ እና የሞሮኒን ምክር ስንከተል ሃሳባችንን የመቆጣጠር ችሎታችን ጎልቶ እንደሚጨምር እመሰክራለው። ልባችን በመቀየር፣ ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንሆን በማድረግ፣ መንፈሳዊ ብስለታችን በፈጠነ ጭማሪ እንደሚያድግ አረጋግጥላችኋለሁ። በተጨማሪም፣ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ በሕይወታችን ውስጥ የበለጠ ኃይለኛ እና ቀጣይነት ያለው ይሆናል። ከዛ የጠላት ፈተናዎች፣ ቀስ በቀስ፣ በኛ ላይ ሀይል ያጣሉ፣ ይበልጥ ደስተኛ እና ንፁህ እና የተቀደሰ ሕይወትን ያስከትላል።

በማንኛውም ምክንያት ወደ ፈተና ለሚገቡ ሰዎች እና ፃድቅ ባልሆነ ተግባሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች፣ የመመለሺያ መንገድ እንዳለ፣ በክርስቶስ ተስፋ እንዳለ አረጋግጣለው። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በሕይወቱ ውስጥ ታላቅ መተላለፍን በመፈፀም በጣም ከባድ የሆነ ጊዜን ባሳለፈ ከውድ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርሰቲያን አባል ጋር ለመጎብኘት እድሉን አግንቼ ነበር። መጀመሪያ ስመለከተው በገፅታው ላይ ብሩህ ተስፋን ጨምሮ በዓይኖቹ ውስጥ ሃዘንን አይ ነበር። የእሱ እያንዳንዱ አገላለፅ ትህትናን እና የተቀየረ ልብን ይገልፃል። ክርስቲያን ሆኖ ነበር እንዲሁም በጌታ በከፍተኛ ተባርኮ ነበር። ይሁን እንጂ ወደ ሌሎች ሊመራ በቻለ ቀላል ተገቢ ያልሆነ ሃሳብ አዕምሮውን እንዲቆጣጠር ፈቅዶ ነበር። እነዚህን ሃሳቦችን የበለጠ እየፈቀደላቸው ሲመጣ፣ በአዕምሮው ውስጥ ስር ሰደዱ እናም በልቡ ውስጥ በጥልቀት ማደግ ጀመሩ። በመጨረሻም በሕይወቱ ውስጥ በጣም ውድ ከሆኑ ከሁሉም ነገሮች በተቃራኒ ውሳኔዎችን እንዲፈፅም ወደመራው በእነዚህ ብቁ ባልሆኑ ፍላጎቶች ላይ ተገበረ። ሲጀመር ለዛ ሞኝ ሃሳብ ቦታ ሰጥቶት ባይሆን ኖሮ፣ ተጠቂ መሆን ባልቸለ እንደነበር እንዲሁም በሕይወቱ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ብዙ ሃዘኖችን ወዳመጡበት—የጠላት ፈተናዎች ተጋላጭ ባልሆነ እንደነበር ነገረኝ።

ልክ በሉቃስ ወንጌል ውስጥ እንደሚገኘው እንደ ታዋቂው የአባካኙ ልጅ ምሳሌ ወደራሱ ተመለሰ እናም ከዛ ቅዠት ነቃ።17 በጌታ ያለውን እምነት አደሰ እናም እውነተኛ ንፅህና ተሰማው እና ወደ ጌታ መንጋ በመጨረሻ ለመመለስ ፍላጎት ነበረው። በዛ ቀን ሁለታችንም የአዳኙን የቤዛነት ፍቅር ተሰማን። በአጭሩ ጉብኝታችን መጨረሻ ላይ ሁለታችንም በስሜት ተዋጥን እናም እስከዚህ ቀን ድረስ ከቢሮዬ ሲሄድ በገፅታው ላይ የነበረውን የሚያንፀባርቅ ደስታ አስታውሳለው።

ውድ ጓደኞቼ፣ በሕይወታችን ውስጥ በድንገት የሚመጡ ትንሽ ፈተናዎችን ስንቋቋም፣ አስከፊ መተላለፎችን ለማስወገድ የበለጠ ዝግጁ እንሆናለን። ፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል እንዳሉት፤ “አንድ ሰው አናሳ ለሆኑት፣ ወደ ታላቁ በር የሚከፍቱትን፣ በመተላለፍ ሳይሸነፍ ጥልቅ ወደ ሆኑት መግባቱ ውስን ነው። … ንጹህ ስፍራ በአንዴ አረም አይወረውም።”18

በምድር ላይ መለኮታዊ ተልኮውን ለመወጣት ሲዘጋጅ፣ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘለአለማዊ አላማችንን ከመገንዘብ የሚያስቱንን ነገሮ ሁሉ በተደጋጋሚ የመከላከልን አስፈላጊነት ምሳሌነት ሰጥቶ ነበር። ከተልኮው ለማሰናከል ከተመኮሩ፣ ከከሸፉት በርካታ የጠላት ጥቃቶች በኋላ፣ አዳኝ እንዲህ በማለት ሴጣንን አሰናበተው፤ “ሂድ፥ አንተ ሰይጣን። … ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።”19

ውድ ወንደሞቼ እና እህቶቼ እኛ ጥንካሬን እና ብርታትን ከአዳኝ አካብተን እናም ንፁህ ያልሆኑ ሃሳቦች ወደ አዕምሮአችን ውስጥ በሚመጡበት ሰዓት “አይሆንም” እና “ሂድ” ብንል ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ትችላላችሁ? በልባችን ፍላጎት ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድን ነው? የኛ የተግባሮች ውጤት እንዴት ወደ አዳኙ እንድንቀርብ ያደርጉናል እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ እንዴት የመንፈስ ቅዱስ ቀጣይነት ያለው ተፅዕኖ እንዲኖረን ይፈቅድልናል? የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል፣ በቤተሰብ ላይ ችግሮችን እና አለመግባባቶችን ይሚያመጡትን ብዙ አሳዛኝ ክስተቶች እና ያልተፈለገ ባህሪያትን፣ አሉታዊ ስሜቶች እና ዝንባሌዎች፣ ግፍ መፈጸምን እና መበደልን፣ እናም ማንኛውም ከጌታ ትእዛዛት የሚቃረኑ ማናቸውንም ነገሮች እናስወግዳለን።

በዚህ አመት ታሪካዊ እና ውስጥ የሚነካ የሚያዝያ መልእክት፣ ውድ ነብያችን ፕሬዘዳንት ረስል ኤም ኔልሰን “እንዲሰሙት”—ኢየሱስ ክርስቶስን ኢንዲሰሙት—እና ለእርሱ ትእዛዛት ለመታዘዝ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ “ፈተናን፣ ችግሮችን፣ እና ድክመትን ለመጋፈጥ በተጨማሪ ሃይል ይባረካሉ” ብለው ቃል ገብተዋል እና በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ባለው ብጥብጥ ወቅት እራሱ ደስታን የመሰማት ችሎታችን ይጨምራል።20

በውድ ነብያችን የተሰጡት ቃል ኪዳኖች በአዳኙ እራሱ የተሰጡ ቃል ኪዳኖች እንደሆኑ እመሰክርላችኋለሁ። በመላው ሃሳብ “ስሙት” እና ወደ ህይወታችን ደስተኛ አለመሆንን የሚያመጡ ነገሮችን ሁሉ “አይሆንም” እና “ሂድ” ለማለት ጥንካሪ እና ብርታት ለማግኘት በመላው ልባችን እንድንከተለው እጋብዛለሁ። ይህን ካደረግን፣ እኛን ለማጠንከር ጌታ የበለጠ መንፈስ ቅዱሱን እንደሚልክልን ቃል እገባለሁ እናም ልክ እንደ ጌታ ልብ ግለሰቦች መሆን እንችላለን።21

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ እመሰክራለው፣ በሃጥያት ክፍያው ምክንያት፣ በጠላት ክፉ ተጽእኖዎች ላይ ድልን እናደርጋለን እና ከጌታ እና ከተወዳጁ የሰማይ አባታችን ጋር ለዘለአለም ለመኖር ብቁ እንሆናለን። እነዚህን እውነታዎች የምመሰክረው ለእናንተ እና ለሚያምረው አዳኛችን ባለኝ ፍቅር፣ ለስሙም ሞገስ፣ ክብር፣ እና ምስጋናን ሁሌም በምሰጠው ነው። እነዚህን ነገሮች የምለው በቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜል።